Home በአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር በመሬት ይዞታ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር በመሬት ይዞታ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ

የኤጀንሲው ስልጣንና ተግባር

በምዝገባ ህግ መሠረት የማይንቀሳቀስ (መሬትና መሬት ነክ) ንብረትን በተመሇከተ የካዳስተር፣ የመብትና ገደቦች መረጃን ይመዘግባል፣ ያድሳል፣ ያስተካክላል፡ ይሰርዛል፤
በምዝገባ ህግ መሠረት የመብት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ይሰጣል፣ ይሰርዛል
ሀገራዊ ደረጃን መሰረት ያደረገ የቁራሽ መሬት ልዩ መሇያ ኮድ ይሰጣል፣
የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ዋና መዝገብ ይይዛል፣ ዳታ ያደራጃል፣ ይተነትናል፣ ወቅታዊ ያደርጋል፣ መረጃ ይጠቀማል፣ መረጃ ይሰጣል፤
ከሚመሇከተው ባሇድርሻ አካላት ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ከተማ ህጋዊ ካዳስተር መረጃ ሥርዓት ላይ መደበኛ የሆነ የስጋት እና የደህንነት ቁጥጥር ያደርጋል፣
የህጋዊ ካዳስተር ቴክኖሎጂ ስርዓትን እና የኔትወርክ መሰረተ-
ልማትን ያሻሽላል፣ ወቅታዊ ያደርጋል፣ ያስተዳድራል::
መሻሻል ያሇባቸውን ህጎችና አሠራሮች እንዲሻሻለ ሃሳብ ያቀርባል፣ ሲፀድቁም ተግባራዊ ያደርጋል፣
ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ፕሮጀክቶችን እንዲቋቋሙና እንዲደራጁ ጥናት ያደርጋል፣ ሲፀድቅም ስራውን በበላይነት ይመራል፣
በአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ህግ መሰረት ሠራተኞችን ይቀጥራል፤ ያስተዳድራል፤ ያሰናብታል
በየክፍሇ ከተማው መዝጋቢ ተቋም በሰው ኃይልና በሌሎች አስፈላጊ በሆኑ ግብዓቶች እንዲደራጅ ያደርጋል፣
በስሙ የንብረት ባሇቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ ይከሳል፣ ይከሰሳል
የአዲስ አበባ ከተማ ካዳስተር መረጃ ሥርዓት መረጃ ይይዛል፣ ያስተዳድራል፣ ወቅታዊ ያደርጋል፤
የማይንቀሳቀስ (መሬትና መሬት ነክ) ንብረት መዛግብት ሇሕዝብ ክፍት እንዲሆኑ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡
በኤጀንሲዉ የሚሰጡ አገልግሎቶች፣ ስታንዳርዶች፣ ቅድመ ሁኔታዎች፣ ዳፊ ማስረጃዎችእና ፈጻሚ አካላት

አዲስ የባለ መብትነት ምዝገባ

ይሄ አገልግሎት ከይዞታ ማረጋገጥ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚመዘገብ ይዞታዎች ነው፡፡
አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
 o የቀበሌ መታወቂያ ካርድ፣ ፓስፖርት፤ መንጃ ፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ መታወቂያ፡-እና በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ፣
o የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት
o መብቱን ያገኘበት ውል፣ ካርታ ኦሪጅናል እና ኮፒ፣
o የአገልግሎት ክፍያ መክፈያ

ይዞታን ማካፈል

አንድን ይዞታ ከአንድ በላይ ወደ ሆኑ ይዞታዎች ለመክፈል ሲፈለግ የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡
አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
o የቀበሌ መታወቂያ ካርድ፣ ፓስፖርት፤ መንጃ ፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ መታወቂያ፡- እና በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ፣
o የየአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት፣
o የይዞታ ማረጋገጫ ኦሪጅናልና ኮፒ፣
o የፕላን አስተያየት ከሚመለከተው አካል
o የአገለግሎት ክፍያ መክፈያ፣
o የሊዝይዞታከሆነየተሻሻለየሊዝዉልኦርጅናል፣

ይዞታን መቀላቀል

ከአንድ በላይ የሆኑ አዋሳኝ ይዞታዎችን ቀላቅሎ ወደ አንድ ይዞታ ለመለወጥ ሲፈለግ የሚጠየቅ የአገልግሎት አይነት ነው፡፡
አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
o የቀበሌ መታወቂያ ካርድ፣ ፓስፖርት፤ መንጃ ፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ መታወቂያ፡- እና በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ፣
o የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት፣
o የሚቀላቀሉ ይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ኦሪጅናልና ኮፒ፣
o የፕላን አስተያየት ከሚመለከተው አካል
o የአገለግሎት ክፍያ መክፈያ፣
o የሊዝ ይዞታ ከሆነ የተሻሻለ የሊዝ ዉል ኦርጅናል፣

የንብረት መያዣ መመዝገብ

ይህ አገልግሎት የሚሰጠው በመብቶች መዝገባ ውስጥ ለተመዘገበ ይዞታ እግድን ለመመዝገብ ነው፡፡ይህ የሚመዘገበው የፍርድ ቤት እና ሌሎች ለማገድ ስልጣን የተሰጣቸው ተቋማት በተለያየ ምክንያት ይዞታው እንዲታገድ ሲያዝ ነው፡፡
አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
o የቀበሌ መታወቂያ ካርድ፣ ፓስፖርት፤ መንጃ ፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ መታወቂያ፡- እና በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ፣
o የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት፣
o የእግድ ትእዛዙ የተላለፈበት ደብዳቤ
o የአገለግሎት ክፍያ መክፈያ፣

የንብረት መያዣ እግድ ስረዛ

ይህ አገልግሎት የሚሰጠው በመብቶች ምዝገባ ውስጥ ለተመዘገበ ይዞታ እግድን ለመሰረዝ ነው፡፡ይህ የሚመዘገበው ፍርድ ቤት እና ሌሎች ለማገድ ስልጣን የተሰጣቸው ተቋማት የተመዘገበ እግድ እንዲሰረዝ ሲታዘዝ ነው፡፡ አገልግሎቱን ለመስጠት
የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
o የቀበሌ መታወቂያ ካርድ፣ ፓስፖርት፤ መንጃ ፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ መታወቂያ፡- እና በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ፣
o የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት፣
o የእግድ ትእዛዙ የተላለፈበት ደብዳቤ
o የአገለግሎት ክፍያ መክፈያ፣

የፍርድ ቤት እግድ መመዝገብ

ይህ አገልግሎት የሚሰጠው በመብቶች መዝገባ ውስጥ ለተመዘገበ ይዞታ እግድን ለመሰረዝ ነው፡፡ይህ የሚመዘገበው ፍርድ ቤት እና ሌሎች ለማገድ ስልጣን የተሰጣቸው ተቋማት የተመዘገበ እግድ እንዲሰረዝ ሲታዘዝ ነው፡፡
አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
o የቀበሌ መታወቂያ ካርድ፣ ፓስፖርት፤ መንጃ ፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ መታወቂያ፡- /በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ፣
o የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት፣
o ዕገዳውን ካደረገው ወይም እንዲታገድለት ከሚፈልገው ህጋዊ አካል ደብዳቤ ማቅረብ፣
o ለዋስትና ምዝገባ ካርታ ኦሪጅናልና ኮፒ፣
o የአገልግሎትክፍያመክፈል፣

የስም ዝውውር

አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
o የቀበሌ መታወቂያ ካርድ፣ ፓስፖርት፤መንጃ ፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ መታወቂያ፡-
እና በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ
o የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት፣
o ካርታ ኦሪጅናልና ኮፒ፣
o የአገለግሎት ክፍያ መክፈያ . . . በተጨማሪም
በሽያጭ ወይም በስጦታ ሲሆን
o በህግ ስልጣን በተሰጠው አካል የፀደቀ ውል፣
o በሊዝ የተያዘ ከሆነ በዉሉ መሰረት መከፈል ያለባቸው ክፍያዎች ከፍሎ ማጠናቀቅ ወይንም የሚዛወርለት ወገን ክፍያውን ለመፈጸም እንዲሁም አስተላለፊው ቀደም ሲል በገባው ውል ላይ የተቀመጡትን ግዴታዎች ገዥ ሙሉ
o በሙሉ በመቀበል ውል መግባት፣
o በቦታዉ ላይ የተደረገዉ ግንባታ ከ50 ከመቶ ያነሰ ከሆነ የተሻሻለ የሊዝ ዉል፣
በባንክ በሐራጅ የሚሸጥ/የሚወረስ ሲሆ
o ከባንክ አሸናፊው ያሸነፈበት ዋጋ፣ የተፈጸመ ውልና ሸኚ ደብዳቤ ማቅረብ
o ከሚመለከተው የመሬት ተቋም የተፈጸመ ውል
በፍርድ አፈጻጸም የተሸጠ ሲሆን
o የፍ/ቤት ትዕዛዝ ኦርጅናል፣
o በሊዝ የተያዘ ይዞታ ከሆነ ሻጩ የገባውን የሊዝ ግዴታዎችን ገዥ ሙሉ በሙሉ የሚቀበል መሆኑን እንዲሁም ዕዳ ያለበት ከሆነ ዕዳውን ለመክፈል ስምምነት ማቅረብ፣
በፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የተላለፈ ሲሆን
o ከኤጀንሲው ያሸነፉበትን ዋጋና የሽያጭ ውል የሚገልጽ ሰነድ
o የመኖሪያ ቤት ሕ/ስራ ማህበራት አባላት መተካካት ሲሆን ወይም ግንባታቸው ያልተጠናቀቀ ከማህበራት ማደራጃ የማህበሩና የመተካካት ሂደቱ ህጋዊነት የተረጋገጠበት ደብዳቤ ፣
የጋራ ሕንጻ/ኮንደሚኒየም ሲሆን
o የባንክ እዳ ተከፍሎ መጠናቀቁን የሚገልጽ መረጃ
o የመኖሪያ ቤት የ5 አመት የጊዜ ገደቡ ማብቃቱ የሚያስረዳ መረጃ ፣ የንግድ ቤት ከሆነ የ5 አመት የጊዜ ገደብ መጠበቅ አያስፈልግም፣
በውርስ የተገኘ ሲሆን
o የውርስ ባለመብትነትን የሚያረጋግጥ የፍ/ቤት ውሳኔ፣
o ከአንድ በላይ ወራሾች ካሉ በፍ/ቤት የፀደቀ የውርስ አጣሪ የድርሻ መጠን ማስረጃና ስምምነት ማቅረብ
o ያልተከፈለ የሊዝ ክፍያና የህንጻ ግብር ካለ ክፍያው መፈፀሙን የሚያስረዳ መረጃ፣ ወይም ለመክፈል የገቡት ስምምነት፣

ለተበላሸ ካርታ ምትክ መስጠት

ለጠፋ ፣ለተበላሸ እና በጊዜያዊነት የተሰጠን ሰርተፊኬት ምትክ ሰርተፍኬት የሚሰጥበት አገልግሎት ነው፡፡ አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
o የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ካርድ፣ ፓስፖርት፤ መንጃ ፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ መታወቂያ፡- እና በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ፣
o የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት፣
o የተበላሸው የይዞታ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት
o የይዞታ ማረጋገጫ ስለለመበላሸቱ የታወጀበት ጋዜጣ
o የአገልግሎት ክፍያ መክፈያ፣

ለጠፋ ካርታ ምትክ መስጠት

ለጠፋ ፣ለተበላሸ እና በጊዜያዊነት የተሰጠን ሰርተፊኬት ምትክ ሰርተፍኬት የሚሰጥበት አገልግሎት ነው፡፡
አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
o የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ካርድ ፣ፓስፖርት፤መንጃ ፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ መታወቂያ፡-
እና በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ፣
o የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት፣
o የይዞታ ማረጋገጫ ስለመጥፋቱ የታወጀበት ጋዜጣ
o የአገለግሎት ክፍያ መክፈያ፣

የወስን ድንጋይ መትከል

ጥያቄ መቀበል እና ሰነድ ማጣራት::
አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
o የቀበሌ መታወቂያ ካርድ፣ ፓስፖርት፤ መንጃ ፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ መታወቂያ፡- እና በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ፣
o የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት፣
o መብቱን ያገኘበት ውል፣ ካርታ ኦሪጅናል እና ኮፒ፣
o የአገልግሎት ክፍያ መክፍል፣

የድንጋይ ክርክር መፍታት

ጥያቄ መቀበል እና ሰነድ ማጣራት እንዲሁም ሰርተፊኬት መስጠት አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
o የቀበሌ መታወቂያ ካርድ፣ ፓስፖርት፤ መንጃ ፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ መታወቂያ፡-/ በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ፣
o የይዞታ ማረጋገጫ ሰርትፊኬት ኦሪጅናልና ኮፒ፣
o አቤቱታውን የሚገልጽ ማመልከቻ ማቅረብ፣
o የአገልግሎት ክፍያ መክፍል፣

የይዞታ ቅርጽ ለውጥ መመዝገብ

ጥያቄ መቀበል እና ሰነድ ማጣራት:: አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
oየቀበሌ መታወቂያ ካርድ፣ ፓስፖርት፤ መንጃ ፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ መታወቂያ፡- እና በወኪል ከሆነ የውክልና ማስረጃ
o የአገልግሎት መጠየቂያ ፎርም መሙላት፣
o ካርታ ኦሪጅናልና ኮፒ፣
o የድንበር ለውጡን የሚያስከትለው ጉዳይ የሚያሳይ ህጋዊ ማስረጃ
o የአገልግሎት ክፍያ መክፈያ