Home በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን

የተሽከርካሪ አገልግሎቶና የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች

ጊዜያዊ /ተላላፊ/ ሠሌዳ የመስጠት አገልግሎት

 • የአገልግሎት መጠየቂያ /ማመልከቻ/ ፎርም
 • ባለንብረቱን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ /መንጃ ፈቃድ/ ወይም የትዉልደ ኢትዮጲያዊ መታወቂያ ከፓስፖርት ጋር እንዲሁም ፓስፖርት፡
 • ዉክልና የተሰጠዉ ግለሰብ ከዋናዉ ጋር የተገናዘበ ህጋዊ ዉክልና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ፣መንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት
 • ከመስሪያ ቤት ወይም ከድርጅት የተወከለ ከሆነ የድርጅቱ የዉክልና ደብዳቤና የደርጅቱን መታወቂያ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 • ኦርጅናል የጉምሩክ ዲክለራሲዮን
 • ከጉምሩክ ዲክለራሲዮን ጋር የተገናዘበ የVDD print out(C-number)
 • የታደሰ የተሸከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ እና የአስመጭነት ፈቃድ ኮፒ
 • ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገቡ የተሸከርካሪ መመርመሪያ ቅጽ /ሮዝ ወረቀት
 • የተቆረጠ ደረሰኝ /Invoice/ በባለንብረቱ ስም ከአታችመንት ጋር ማቅረብ ሲኖርባቸዉ ደረሰኝ/Invoice/ ማቅረብ ለማይችሉ የእጅ በእጅ የደረሰኝ ህትመት እና የማሳተሚያ ፍቃድ ከገቢዎችና ጉምሩክ በደረሰኙ መነሻ ቁጥር የተፈቀደበት ደብዳቤ፡፡

በተላላፊ ሰሌዳ ዕድሳት

 • ተላለፊ ሰሌዳ ለሦስት ቀን (3 ቀን) የሚያገለግል ሲሆን ከሦስት ቀናት በላይ ካስፈለገ ለአንድ ጊዜ ብቻ የሚታደሰ ሆኖ ከአንድ ጊዜ በላይ ዕድሳት ለሚፈልጉ ባለጉዳይ ተላላፊ ሰሌዳዉ ለአላስፈላጊ ተግባር ሊውል ስለሚችል በተሽከርካሪ የምዝገባ ሲስተሙ መሰረት በቅጣት የሚስተናገድ ይሆናል፡፡

የአዲስ ተሽከርካሪ ምርመራና ምዝገባ አገልግሎት

የቤት ተሽከርካሪ ምዝገባ
 • የአገልግሎት መጠየቂያ /ማመልከቻፎርም
 • ተላላፊ ሰሌዳ መመለስ
 • ተሽከርካሪ ለጭነት አወሳሰን የነጠላ ክብደት መመዘን የሚገባው ከሆነ የተመዘነበት ማረጋገጫ ሰነድ /የሚዛን ወረቀት/፡፡
 • የአገልግሎት ዘርፍ በዲካላረሲዮን ላይ ከተገለጸና ዲክላራሲዮኑ ላይ የአገልግሎት ዘርፉ ካልተገደበ በተገለጸው የአገልግሎት ዘርፍ አገልግሎቱ ይሰጠዋል፡፡
 • ወደ ምርመራ ቦታ እንዲገባ የተፈቀደበት የማስገቢያ ቅጽ
 • ተሽከርካሪውን በአካል ለምርመራ ማቅረብ
 • የአዲስ ተሸከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ምርመራ ማረጋገጫ /Specification/
 • ተሸከርካሪው ዋጋ ካሽ ሪጅስተር ደረሰኝ/Invoice/ ከዲክላራሲዮን ዋጋ በማነፃፀር ከፍተኛ በሆነዉ የቴምብር ቀረጡን 2% ማስከፈል፡፡
 • የ3ተኛ ወገን የጸና የመድን ዋስትና
 • 6 ወር ወዲህ የተነሱት 2 ጉርድ ፎቶ፤ ቴምብር
 • ተሽከርካሪው ከቀረጥ ነፃ የገባ መሆን አለመሆኑን ከዲክለራሲዮን ላይ በማረጋገጥ ሊብሬ ላይ ቀረጥ የከፈለ ወይም ቀረጥ ያልከፈለ መሆኑን መግለፅ
 • የአገልግሎት ክፍያ በማስከፈል ሰሌዳ፣ ሊብሬ፣ ቦሎ መስጠት፡፡
 • ተወካይ ከሆነ ሊብሬዉ በቴምብር ይሰራል፡፡
 • በሀገር ውስጥ ለተመረቱ እና ለተገጣጠሙተሽከርካሪዎች ምዝገባ ከመሰረታዊ ሰነዶች በተጨማሪ ከባለስልጣኑ የተሰጠ የተሽከርካሪ አካል ማምረቻና መገጣጠሚያ ብቃት ማረጋገጫ የታደሰ ፈቃድ፣ የተሽከርካሪው የስታንዳርድ የወንበር/የጭነት ልክዝርዝር መግለጫ ሲቀርብ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
ለንግድ እና የግል ንግድ ተሸከርካሪ
ከላይ ለቤት ተሸከርካሪ የተገለጹትን መሰረታዊ ሰነዶች አሟልተው በተጨማሪ
 • ለንግድ ተሽከርካሪዎች በምዝገባ ወቅት የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አይጠበቅባቸውም
 • ለግል ንግድ የተሽከርካሪ ምዝገባ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርበታል ይሁን እንጅ ንግድ ፈቃድ ለማውጣት የተሽከርካሪ ሊብሬ ለሚያስፈልጋቸው በግል ንግድ ለሚሰማሩ ድርጅቶች የንግድ ስያሜ ማጸደቂያ ሰርተፊኬት ሲያቀርቡ ይስተናገዳሉ
 • ለግል ንግድ ምዝገባ ስያሜያቸው በግለሰቡ ስም ከሆነ ንግድ ፈቃዱ ላይ ከግለሰቡ ስም በመቀጠል የተፈቀደለትን የንግድ ዘርፍ ሊብሬው ግርጌ ላይ በመፃፍ የተፈቀደለትን የግል ንግድ በማለት አገልግሎቱን መስጠት፡፡
 • በግል ንግድ የተመዘገበ ተሽከርካሪ ከኮድ-03 ወደ ኮድ-02 የአገልግሎት ለውጥ ለማድረግ የባለንብረትነት ስም ማስመዝገቢያ የቴምብር ቀረጥ 2% እና የአገልግሎት ክፍያ ሲከፍል አገልግሎቱ ይሰጠዋል
 • ተሽከርካሪው ከቀረጥ ነፃ የገባ መሆን አለመሆኑን ከዲክለራሲዮን ላይ በማረጋገጥ ሊብሬ ላይ ቀረጥ የከፈለ ወይም ቀረጥ ያልከፈለ መሆኑን መግለፅ
ለእርዳታ እና በጎ አድራጎት ለተሰማሩ ድርጅቶች የተሽከርካሪ ምዝገባ
ለበጎ አድራጎት ወይም ለእርዳታ ድርጅቶች ከመሰረታዊ ሰነዶች በተጨማሪ
 • ፈቃድ ከሚሰጥ አካል ፈቃድ ሲያመጡ
 • ለቀይ መስቀል፣ ቀይ ጨረቃ፣ ለኃይማኖት ተቋማትና ትርፋማ ላልሆኑት ማህበራት፣ ለህዝባዊ ማህበራትና ለመሳሰሉት ተቋማት አገልግሎት እንዲዉሉ ኮድ 5 ሰሌዳ እና
 • ለዓለም አቀፍ/ ለሀገር በቀል እርዳታ ድርጅቶች በነጭ መደብ ከብርቱካናማ ፊደላትና ቁጥሮች ጋር እንደ ሀገራቱ መለያ ቁጥር የሚሰየም ሰሌዳ ይሰጣቸዋል፡፡
 • ተሽከርካሪው ከቀረጥ ነፃ የገባ መሆን አለመሆኑን ከዲክለራሲዮን ላይ በማረጋገጥ ሊብሬ ላይ ቀረጥ የከፈለ ወይም ቀረጥ ያልከፈለ መሆኑን መግለፅ
ለኮር ዲፕሎማት ሠሌዳ ምዝገባ
መሰረታዊ የተሽከርካሪ ሰነዶችመሟላታቸው እንደተጠበቁ ሆነው፡-
 • የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፈቀደበት ማስረጃ
 • ከቴምብር ቀረጥ 2% ክፍያ ነጻ ከሆነ ከገንዘብና ኢኮኖሚና ትብብር ሚኒስቴር ማስረጃ በማቅረብ አገልግሎት ያገኛሉ
 • ተሽከርካሪው ከቀረጥ ነፃ የገባ መሆን አለመሆኑን ከዲክለራሲዮን ላይ በማረጋገጥ ሊብሬ ላይ ቀረጥ የከፈለ ወይም ቀረጥ ያልከፈለ መሆኑን መግለፅ
ለዕጣ ባለዕድሎች የተሽከርካሪ ምዝገባ
መሠረታዊ የተሸከርካሪ ሰነድማሟላት እንደተጠበቀ ሆኖ፡-
 • ዕጣ አውጥቶ ለእድለኞች እንዲያስተላልፍ በአዋጅ ስልጣን ከተሰጠዉ አካል ህጋዊ ፈቃድ እና
 • ለአሸናፊዎቹ ከአሸነፉበት የዕጣ ቁጥር ጋር የተሽከርካሪውን ሻንሲና ሞተርቁጥር በመጥቀስ ለባለእድለኛዉ ምዝገባ እንዲደረግ ከሚመለከተው አካልየተፃፈ ደብዳቤ ሲቀርብ አገልግሎት ይሰጠዋል
አስመጪ ድርጅት ተሽከርካሪ አስመጥቶ በራሱ በድርጅቱ ስም ለማስመዝገብ
መሰረታዊ ሰነዶች መሟላታቸው እንደተጠበቁ ሆኖ፡-
 • Invoice/ደረሰኝ መቁረጥ አይጠበቅበትም
 • አንድ አስመጪ ተሸከርካሪውን ሲገዛ ሰነዶቹ በድርጅቱ ስም የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጥ
 • 2% የቴምብር ቀረጥ ማስከፈል
 • ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ በማስከፈል ኮድ 03 ሰሌዳ ብቻ ይሰጠዋል
ከጅምላ ገዥ ተሸከርካሪ በችርቻሮ የተገዛ ተሽከርካሪ ምዝገባ
መሰረታዊ ሰነዶች መሟላታቸው እንደተጠበቁ ሆኖ፡-
 • ቸርቻሪዉ ከጅምላ ሻጭ የገዛበት ደረሰኝ/Invoice ከነፕሪንት አውቱ ኮፒ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በእርጥብ ማህተም የተረጋገጠ ወይም የእጅ በእጅ ሽያጭ ከገቢዎች የደረሰኝ የህትመት ፈቃድ፡፡
 • ቸርቻሪዉ ለገዢዉ Invoice ከነፕሪንት አውቱ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ይቆርጣል፡፡
 • የአስመጭው እና የቸርቻሪው የታደሰ የንግድ ፈቃድ በተጨማሪ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ለኢት ሰሌዳ የተሽከርካሪ ምዝገባ
  መሰረታዊ ሰነዶች እንደተጠበቁ ሆኖ፡
 • 44 እና ከ44 መቀመጫ እንዲሁም ከ70 እና ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ክልሎች በሚያገናኝ የንግድ/የግል ንግድ/የኮንስትራክሽን እንዲሁም የመንገድ ማመላለሻ ስራ ለሚሰሩ
 • ንብረትነታቸዉ የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤት የሆኑ ተሸከርካሪዎች
 • ክልል ተሻጋሪ በሆነ በኢንቨስትመንት ስራ ላይ የተሰማሩ ለመሆኑ ከሚመለከተው አካል የኢንቨስትመንት ፈቃድ
ለአምቡላንስ እና ለቱሪስት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውሉ ተሸከርካሪዎች ምዝገባ
መሰረታዊ ሰነዶች ማሟላታቸው እንደተጠበቁ ሆኖ፡
 • ተሽከርካሪው ለአምቡላንስ አገልግሎት የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን ለማሟላቱ ከጤና ቢሮ የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሲያቀርብ እና
 • ለቱሪስት ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭነት ለሚሰማሩ ባለንብረቶች ተሽከርካሪው ለተፈለገው አገልግሎት ብቁ መሆኑን ከፈቃድ ሰጭው አካል የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሲያቀርቡ አገልግሎት ይሰጠዋል፡፡
ማሽነሪ የሚገጠምላቸዉ ተሽከርካሪዎች ምዝገባ
መሰረታዊ ሰነዶች ማሟላታቸው እንደተጠበቁ ሆኖ፡
ለአገልግሎት አሰጣጡ እንዲያመች የኮንስትራክሽን ተሽከርካሪዎች ምዝገባ በልዩ ልዩ ይስተናገዱና የመጫን አቅሙ ማሽን የተገጠመለት በሚል አግባብ አገልግሎቱ ይሰጣል
ልዩ ጎታችና ተሳቢ ተሸከርካሪ ምዝገባ
 • ተሳቢና ጎታች የተለያየ ሰሌዳ ስለሚሰጣቸው የየራሳቸውን ዲክለራሲዮን ተሰርቶላቸው ሲቀርብ ብቻ አገልግሎቱ ይሰጣቸዋል፡፡
 • ልዩ ጎታችና ተሳቢ በሚጣመሩበት ጊዜ ልዩ ጎታችና የተሳቢው የአክስል መጠን እኩል ሲሆን ወይም ልዩ ጎታቹ በአንድ ሲበልጥ ብቻ ማጣመር ይችላል
 • ልዩ ጎታች የጭነት ልክ በአክስል ብዛት እየተቀመረ የጭነት ልኩ በሊብሬዉ ላይ ይገለፃል፡፡
 • ለተሳቢ/ለተጎታች የጭነት ልክ በአክስል ብዛት እየተቀመረ የጭነት ልኩ በሊብሬዉ ላይ ይገለፃል፡፡
ሞድፊክ ስራ/Value Add/ ያሰራ ተሽከርካሪ ምዝገባ
መሰረታዊ ሰነዶች በተጨማሪ
 • ተቋሙ ሞደፊክ/Value Add ለማድረግ የተሰጠው የአካል ለዉጥ ፈቃድ
 • ሞዲፊክ የተሰራበት/Value Add/የተደረገበት የሰነድ መረጃ
 • ከአስመጭ የተገዛበት እና ለሞዲፊክ የወጣውን የዋጋ ድምር ያካተተ ደረሰኝ እና
         የአስመጭ የንግድ ፈቃድ ሰነዶችን አያይዞ ሲቀርቡ አገልግሎት ይሰጣል

የተሽከርካሪ የአካልና የአገልግሎት ለውጥ ምዝገባ አገልግሎት

የአካል ለውጥ ያደረገ ተሸከርካሪ አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ሰነዶች፡
 • የማመልከቻ ፎርም
 • የአካል ለውጥ የፈቃድ ደብዳቤ
 • በእርጥብ ማህተም የተረጋገጠ የባለጋራዡ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ
 • በእርጥብ ማህተም የተረጋገጠ የታደሰ የአካል ለውጥ የብቃት ማረጋገጫ ኮፒ
 • አካል ለውጡን ያሰራበት ደረሰኝ፣
 • ተሽከርካሪውን በአካል በማቅረብ የመዝጋቢ ተቋሙ ቴክኒሻኖች የተሰራውን የአካል ለውጥ ስራ በስታንዳርዱ መሰረት ለተጠየቀው አገልግሎት ብቁ መሆኑን በማረጋገጥ የአገልግሎት ክፍያ እና የአካል ለውጡን ያሰራበት ደረሰኝ 2% በማስከፈል አገልግሎቱን መስጠት፡፡
 • የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር /ሊብሬ/
 • ከቀረጥ ነፃ ለገባ ተሸከርካሪ ከፈቀደው አካል የስምምነት ደብዳቤ
 • በዕግድና በዕዳ ከተያዘ እግዱን ያወረደው አካል የስምምነትደብዳቤ
 • የአካል ለውጥ የሰራዉ ጋራዥ የሰራበት ስታንደርድና የመሸኛ ደብዳቤ
 • የጭነት ልክ ለሚያስፈልጋቸው የሚዛን ማረጋገጫ
ኮድ-03 እና ኮድ -01 ተሽከርካሪ የአገልግሎት ለውጥ ለሚያደርግ ከሆነ የግብር ክሊራንስ ማቅረብ ይጠበቅበታል

የተሽከርካሪ የባለቤትነት ሥም ዝውውር አገልግሎት

ለሃገር ውስጥ ተሸከርካሪዎች የሥም ዝውውር አገልግሎት ለመስጠት
የተሽከርካሪ መሰረታዊ ሰነዶችን ማሟላት እንደተጠበቀ ሆኖ፡
 • ማመልከቻፎርም
 • የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር /ሊብሬ/
 • በተሽከርካሪው ላይ የተላለፈ ማንኛውም ዓይነት እዳ እና እገዳ እንዲሁም ቀረጥ ያለበት ከሆነ ህጋዊ ማስነሻ ማስረጃ ወይም የስምምነት ደብዳቤ
 • ኮድ 01 ኮድ 03 እና የመንግስት ልማት ድርጅት ተሽከርካሪ ከሆነ ከገቢዎች የግብር ክሊራንስ
 • የዘመኑን ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ/ቦሎ/ ያደረገ
 • የጸደቀ የውልና ማስረጃ ሰነድና የስም ዝውውር 2% የከፈለበት ማስረጃ
 • የንግድ ተሸከርካሪ ከሆነ አንዱ የግምት ውጤት ለሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ሁለተኛውን የግምት ውጤት ሁለቱ ተዋዋዮች ውል መፈፀም የሚችሉ ለመሆኑ በሸኚ ደብዳቤ ለሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተላከበት ሰነድ
 • የቤት ተሸከርካሪ ከሆነ የግምት ውጤቱን በቀጥታ ለሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ የተላከበት ሰነድ
 • የገዥ 2 ጉርድ ፎቶግራፍ እና ባለንብረቱን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ/ ወይም የትዉልደ ኢትዮጲያዊ መታወቂያ ከፓስፖርት ጋር እንዲሁም ፓስፖርት፡
 • ተሽከርካሪው የዋጋ ግምት ከተሰራለት ከ 6 ወር በኋላ ከመጣ ተሽከርካሪውን ድጋሚ በማቅረብ ለቴክኒክ ምርመራ ይቀርባል፡፡ ከ6 ወር በፊት ከቀረበ ግን በዋጋ ግምት ላይ በተሰራለት ስፔስፊኬሽን አገልግሎት ያገኛል፡፡
 • ማሰልጠኛ ተሽከርካሪዎች ስም ዝውውር ለማድረግ ሲፈልጉ ተቋሙ የማሰልጠን ፈቃዱን ከሰጠው አካል ፈቃድ ወይም የተፈቀደለትን ካታጎሪ መቀየሩን መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
 • ተወካይ ከሆነ ለግል ባለጉዳይ የዉክልና ደብዳቤ ከዉልና ማስረጃ ከታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ጋር ባለ 5 ብር ቴምብር መቅረብ አለበት
 • የተሸከርካሪ ሽያጭ የመንደር ውል ወይም በውልና ማስረጃ የጸደቀ፤በስጦታ ከሆነ በውልና ማስረጃ የጸደቀ የስጦታ ውል ሰነድ፤ በፍ/ቤት ትዕዛዝ ከሆነ የፍ/ቤት ውሳኔ፣ በባንክ፤ በኢንሹራንስ፤ በጉምሩክ …ወዘተ በጨረታ የተሸጠ ከሆነ በጨረታ የሽያጭ ህግናስርዓትመሰረት የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ
 • ግለሰቦች ተሸከርካሪ ገዝተው በማህበር አባልነት ለማስመዝገብ ሲፈልጉ የማህበሩ የመተዳደሪያ ደንብ እና የማህበሩ አባላት ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
 • 3ኛ ወገን ኢንሹራንስ
 • የመንገድ ፈንድ የክፍያ ደረሰኝ
 • መሰረታዊ ፋይል ለሌላቸዉ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በተላለፈዉ ሰርኩላር መሰረትይፈጸማል፡፡
 • የስም ዝውውር የአገልግሎት ክፍያ
ለዓለምአቀፍድርጅቶችእናለኮርዲፕሎማቲክተሸከርካሪዎችየሥም ዝውውር አገልግሎት ለመስጠት
 • ማናቸውም ዕዳ ዕገዳ ካለበት የተነሣበትወይም የተሰረዘበት ማስረጃ
 • የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ/
 • በግንባር የቀረበው ገዥው ከሆነ 2 ፎቶግራፍ እና ባለ ብር ቴምብር
 • ባለንብረቱን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ/መንጃ ፈቃድ/ ወይም የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ከፓስፖርት ጋር እንዲሁም ፓስፖርት፡
 • ድርጅቱ ለውጭጉዳይ ሚ/ር የፃፈው ደብዳቤ
 • የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የስም ማዛወሪያ ደብደቤ /ሴልስ አግሪመንት
 • ሞተርና ሻንሲው በቴክኒክ የታየበት ማስረጃ
በጨረታ የሚሸጡ ተሸከርካሪ ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ ሰነዶች
በጨረታ ተሸከርካሪ ለመሸጥ ህጋዊ መብት ያላቸው ተቋማት የተሸጡ የስም ዝውውር አገልግሎቱን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ሰነዶች፡-
 • ተሸከርካሪው ቀረጥ ያለበትና ዲክለራሲዮን የሌለው ከሆነ አዲስ በገዥው ስም የተሰራ ዲክላራሲዮን
 • በተጠቃለለው የጨረታ አዋርድ ደብዳቤ (ጨረታ የወጣበትን ቀንና ቁጥር፣የጋዜጣ ስም፣የአሽናፊውን ስም፣የተሸከርካሪውን የሻንሲና የሞተር ቁጥር ጨረታውን ያሽነፈበትን ዋጋ መያዝ አለበት) ከክፍያ ደረሰኝ ጋር ማቅረብ
 • ከመንግስት ተቋማትና ባንኮች በሚካሄድ የጨረታ የተሽከርካሪ ሽያጭ በሚከናወንበት ጊዜ የተሽከርካሪ ስም ዝውውር 2% ክፍያ የጨረታ ዋጋውን በመውሰድ በአገልግሎት መስጫ ተቋሙ የሚከፈል ይሆናል፡፡
 • ከተለያዩ የግል ድርጅቶች በጨረታና በቀጥታ ሽያጭ በሚከናወንበት ጊዜ በውልና ማስረጃ በጸደቀ ሰነድ ብቻ አገልግሎት የሚሰጣቸው ሆኖ የስም ዝውውር 2% ክፍያ በአዋዋዩ ተቋሙ የሚከናወን ሆኖ የከፈለበትን ደረሰኝ በመቀበል ይስተናገዳል፡፡
 • በጨረታ ተሸጦ ለምዝገባ የመጣ ተሸከርካሪ የዓመታዊ ቴክኒክ ምርመራ በማድረግ ሰርትፍኬት ማምጣት
በጨረታ የተሸጠ የሰነድ ጉድለት ያለበት የመንግስት ተሽከርካሪ ምዝገባ
 • የጠፋው ሊብሬ ከሆነ ስለጠፋው ሊብሬ የማረጋጫ ደብዳቤ ከጨረታ አውጭ መስሪያ ቤቱ ማቅረብ
 • ጨረታ አውጭ መስሪያ ቤት ስለ ተሽከርካሪው የመረጃ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ ማቅረብ
 • በሻንሲና በሞተር ቁጥር ዲክላራሲዮን ማሰራት
 • ተሽከርካሪው በአካል እንዲቀርብ ማድረግ ስፔስፊኬሽን መስራት
 • በተጠቃለለው የጨረታ አዋርድ ደብዳቤ (ጨረታ የወጣበትን ቀንና ቁጥር፣የጋዜጣ ስም፣የአሽናፊውን ስም፣የተሸከርካሪውን የሻንሲና የሞተር ቁጥር ጨረታውን ያሽነፈበትን ዋጋ መያዝ አለበት)ከክፍያ ደረሰኝ ጋር ማቅረብ
 • ከተሽከርካሪው ጨረታ አውጭው መ/ቤቱ ወይም ድርጅት በይዞታው ስር በነበረ ጊዜ በተሽከርካሪው ላይ የሚፈለግ ማንኛውም ጉዳይ ኃላፊነቱን ይወስዳል
አደጋ የደረሰበት የኢንሹራንስ ተሽከርካሪ ስም ዝውውር ምዝገባ
 • ኢንሹራንስ በሻንሲው ላይ ሙሉ ጉዳት ደርሶበት የተረከቡትን ተሸከርካሪ በሚወገዱበት አግባብ ከማስወገድ ውጭ አስጠግኖ ለሽያጭም ሆነ ለማስመዝገብ ማቅረብ አይችሉም ይሁን እንጅ በአካል ለውጥና ጥገና መመሪያ መሰረት ፈቃድ ወስዶ አስጠግኖ ከቀረበ የሚስተናገድ ይሆናል፡፡
 • ከላይ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የተሽከርካሪው ባለቤት ለኢንሹራንሱ በውልና ማስረጃ የጸደቀ የውክልና ማስረጃ ሲቀርብ
 • ቻንሲ ቁጥር የሚመታ እና ቻንሲና ሞተር የሚቀየር እንዲሁም የአካል ለውጥ የሚደረግ ከሆነ ድርጅቱ በጥገና ጊዜ የቻንሲና ሞተር ቁጥር የማስመቻ ፈቃድ፣ የሻንሲና የሞተር ለውጥ ፈቃድ እና የአካል ለውጥ ፈቃድ ባለስልጣኑ መ/ቤት ባወጣው ስታንዳርድ እና አሰራር መሰረት ተረጋግጦ ፋይሉ ካለበት ከክልል/ከተማ አስተዳደር የትራንሰፖርት ቢሮ ያስፈቀደበት ደብዳቤ ሲቀርብ
 • ከላይ በተፈቀደለት መሰረት ተሸከርካሪው የቻሲና የሞተር ቁጥር መመታት እና መለወጥ እንዲሁም የአካል ለውጥ ካደረገ የአካል ለውጥ፣ የቻሲና የሞተር ቁጥር መመታት እና መለወጥ ያደረገበት ማስረጃ እንዲሁም ህጋዊ ፈቃድ ካለው ጋረዥ የጥገና ሰነድ ጋር ሲቀርብ
 • የጥገና እና የአካል ለውጥ ካደረገ በኋላ ለአገልግሎቱ ብቁ መሆኑን የቴክኒክ ብቃቱ በባለሙያዎች ተፈትሾና ተረጋግጦ ሲቀርብ እና
 • በጨረታ ሲሸጥ ኢንሹራንሱ የሸጠበት የጨረታ ዋጋ ለቴምብር ቀረጥ የማስከፈያ የዋጋ ግምት በመጠቀም አገልግሎት ይሰጣል
 • ድርጅቱ ለራሱ ለመጠቀምም ሆነ ለመሸጥ የህግ አግባብ ማቅረብ ካልቻለ ተሸከርካሪን የሚወርሰውም ሆነ የሚሸጠው የተሸከርካሪ መመሪያ በሚያዘው መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡
የሰነድ ጉድለት ያለበት የመንግስት ተሽከርካሪ በጨረታ ተሽጦ ለምዝገባ ሲቀርብ
 • የጠፋው ሊብሬ ከሆነ ስለጠፋው ሊብሬ የማረጋጫ ደብዳቤ ከጨረታ አውጭ መስሪያ ቤቱ ማቅረብ
 • ጨረታ አውጭ መስሪያ ቤት ስለ ተሽከርካሪው የመረጃ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ ማቅረብ
 • በሻንሲና በሞተር ቁጥር ዲክላራሲዮን ማሰራት
 • ተሽከርካሪው በአካል እንዲቀርብ ማድረግ ስፔስፊኬሽን መስራት
 • በተጠቃለለው የጨረታ አዋርድ ደብዳቤ (ጨረታ የወጣበትን ቀንና ቁጥር፣የጋዜጣ ስም፣የአሽናፊውን ስም፣የተሸከርካሪውን የሻንሲና የሞተር ቁጥር ጨረታውን ያሽነፈበትን ዋጋ መያዝ አለበት)ከክፍያ ደረሰኝ ጋር ማቅረብ
 • ከተሽከርካሪው ጨረታ አውጭው መ/ቤቱ ወይም ድርጅት በይዞታው ስር በነበረ ጊዜ በተሽከርካሪው ላይ የሚፈለግ ማንኛውም ጉዳይ ኃላፊነቱን ይወስዳል
የሰነድ ጉድለት ያለበት እና የጠፋ ፋይል ያለው የተሽከርካሪ ስም ዝውውር ምዝገባ
 • ቀደም ሲል በሊብሬው አገልግሎት እንዳገኙ/እንዳደሱ ማረጋገጥ
 • አገልግሎቱን የሚያገኝ ተሽከርካሪ የሊብሬ፣ የቦሎ፣ እና የክፍያ ደረሰኝ   የአገልግሎት ክፍያ ማስረጃዎችን ማረጋገጥ
 • በሁሉም የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እና ወደ ሲስተም ያልገባ ፋይል መረጃቸው በሲስተም እና በሃርድ ኮፒ ተፈልጎ የሌሉ መሆኑን በደብዳቤ ማረጋገጥ
 • በሻንሲና በሞተር ቁጥር ዲክላራሲዮን ማሰራት
 • ለንግድ/ለግል ንግድ የንግድ ፈቃድ ወይም የግብር ክሊራንስ
 • ተሽከርካሪው በአካል እንዲቀርብ በማድረግ ስፔስፊኬሽን መስራት
 • ተሽከርካሪው የመ/ቤቱ ወይም የድርጅቱ ከሆነ በንብረትነት ይዞ በነበረ ጊዜ በተሽከርካሪው ላይ የሚፈለግ እዳና እግድ በማንኛውም ጉዳይ  ተጠያቂ ለመሆን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ከተቋሙ ማምጣት
 • የግለሰብ ተሽከርካሪ ከሆነ ባለንብረቱ በተሽከርካሪው ላይ የሚፈለግ እዳና እግድ ቢኖር ለመተካት ወይም ተጠያቂ ለመሆን የሚያስችል የውል ግዴታ በህግ አገልግሎት ክፍል በተዘጋጀ ፎርማት መፈረም ፎርሙ በአባሪነት ይያያዛል ውዝፍ ክፍያ ካለ በማስከፈል አገልግሎቱን መስጠት

በዓመታዊ የተሽከርካሪ ብቃት ምርመራ/ቦሎ/ አገልግሎት

 • የማመልከ ቻፎርም
 • የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ/
 • የምርመራ ሰርተፊኬት የቆይታ ጊዜ ተሸከርካሪው ከተመረመረበት ቀን ጀምሮ ቦሎ ለመውሰድ ለኢ.ት ሰሌዳ 30 ቀን ለሌሎች ክልል ወይም ከተማ መስተዳድሮች 20 ቀን ያላለፈዉ
 • የመርማሪ ቴክኒሻኖች ስም፤ የፊርማ ናሙና እና የትምህርት መረጃ ሲስተም ዉስጥ የተመዘገበ መሆኑ
 • አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ በሚካሄድበት ወቅት የምርመራ ተቋሙ ሁለት ቴክኒሽያኖችን እና የተቋም ኃላፊ መፈረማቸው
 • ተሽከርካሪው ወደ ምርመራ ቦታ መጥቶ የተመረመረ ስለመሆኑ የሚያረጋግ የተሸከርካሪዉን ሰሌዳ በግልጽ የሚያሳይ ምስል ፕሪንት አውት ላይ ፎቶግራፍ ከሚነበብ ሰሌዳ ጋር መኖሩ
 • ለግል ንግድ በንግድ ፈቃዱ ስም፤ ለንግድ በተሽከርካሪው ሰሌዳ፣ የሻንሲና የሞተር ቁጥር የተገለጸ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ወይም የግብር ክሊራንስ መኖር
 • የ3ኛ ወገን ኢንሹራንስ የገባበት ዉል መኖሩን
 • የመንገድ ፈንድ ክፍያ የከፈለበት ደረሰኝ ኮፒ መኖሩን እና
 • የቴክኒክ ምርመራ ባለፈው ዓመት ምርመራ ካላደረገ የቅጣት ጨምሮ የዘመኑ ቦሎ ክፍያ ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎችን መክፈሉ ተረጋግጦ ቦሎ ይሰጣል
 • ማንኛውም ግለሰብ ከላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች እና ማንነቱን የሚገልጽ የመታወቂያ ኮፒ ሲያቀርብ ይሰተናገዳል፡፡

የተሽከርካሪ የዕዳና ዕገዳ ምዝገባ አገልግሎት

አንድ ተሽከርካሪ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ በማናቸውም መንገድ ሰነዱ ወደ ሌላ ሰውእንዳይዞር የእገዳ ትእዛዝ የሚቀርበው ከባንክ፣ ከፍርድ ቤት፣ከኢንቨስትመንት ቢሮ፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ የብድርና ቁጠባ ተቋማት እንዲሁም ሌሎች ህግ የሚፈቅድላቸውናቸው፡፡
 • ማመልከቻ ፎርም
 • የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ/ ማቅረብ
 • እግድ የቀረበበት ተሽከርካሪ ፋይል ስለመኖሩ በኮምፒውተር እና በደረቅ ፋይል ውስጥ ስለመኖሩ ማረጋገጥ ፣
 • የእግድ ትእዛዝ ሲመጣ ወደ መ/ቤታችን ገቢ በሆነበት እለት ወዲያው ተሽከርካሪው መታገድ አለበት፡፡መታገዱንም እንዲታገድለት ለጠየቀው አካል ማስታወቅ ፡፡
 • እንዲታገድ የታዘዘውን ተሸከርካሪ በጥያቄው መሠረት የእግድ ደብዳቤና የተሽከርካሪው ፋይል እንዲሁም የኮምፒውተር መረጃዎቹ መጣጣማቸውን ማረጋገጥ፣
 • እግድ በኮምፒውተርና በተሸከርካሪው ፋይል ላይ በትክክል ተመዝግቦ በሠራተኛው ፊርማና ቲተር ማረጋገጥ እና
 • የባንክ እግድ ጥያቄ በባንኩ ወኪል ሲቀርብ አቅራቢው ህጋዊነት እንደአስፈላጊነቱ በማረጋገጥ የገንዘቡን መጠን በሊብሬው ላይ በማስፈር፤ በኮምፒውተር ሲስተም ፋይል እና በሊብሬ ላይ አግዶ ሊብሬውን ለባንኩ ተወካይ ማስረከብ
 • የአገልግሎት ክፍያ በታሪፉ መሠረት ማስከፈል፣
 • ሌሎች ተቋማት በውልና ማስረጃ የፀደቀ የስምምነት ሰነድ ካቀረቡ ተሽከርካሪው ሊታገድላቸው ይችላል፡
   የፍርድ ቤት ዕግድ
 • የተሽከርካሪው ሰሌዳ ሳይጠቀስ የባለንብረቱ ስም ብቻ ተጠቀሶ እንዲታገድ ሲመጣ በርካታ ተመሳሳይ ስም ሊኖር ስለሚችል ለጊዜው ፋይሉን በጥንቃቄ በማገድ አስፈላጊ ሲሆን ተጨማሪ ማብራሪያ እግዱን ከሰጠው አካል መጠየቅ እና
 • ፍ/ቤቶች ሰሌዳውን ብቻ በመጥቀስ የባለቤቱን ስም አጣርታችሁ ሳይል እንዲታገድ ብቻ ትእዛዝ ከሰጡ ትእዛዙ መፈፀም አለበት፡፡
  ባንኮችና የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት/ድርጅቶች፦
 • ባንኮችና የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት /ድርጅቶች በዋስትና የያዙትን ተሽከርካሪ እንዲታገድላቸው በሚጽፉት ደብዳቤ ጊዜ እግዱ በፋይል፣ በኮምፒውተር፣ በባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ/ ላይ መመዝገብ አለበት
 • ባንኮችና የአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት/ ድርጅቶች ተሽከርካሪ እንዲታገድላቸው በሚያቀርቡት ደብዳቤ ላይ ሌላ እዳና እግዳ፣ ቀረጥ ነጻ እንደሌለበት አጣርታችሁ፤ በአንደኛ ደረጃ እግዱን መዝግቡልን የሚል አገልግሎት አይሰጥም፡፡
 • የፋይናንስ ተቋማት የዕግድ ጥያቄ ሲያቀርቡ ከዚህ በፊት የተላለፈ እግድ አለመኖሩን ማረጋገጥ፣ቀደም ሲል የተመዘገበ እግድ ካለ ይህንኑ በዝርዝር በመግለፅ እንዲታገድለት ለጠየቀው አካል በጽሁፍ ማሳወቅ አለበት
 • አነስተኛ ብድር አቅራቢ ድርጅቱ ከተሽከርካሪ ባለመብት ግለሰብ ጋር ያደረገውን የብድር ውል ስምምነቱን እና የእግድ ደብዳቤ ሲቀርብ የዕግድ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
   የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዕግድ፦
 • በግለሰቡ ስም ወይም በድርጅቱ ስም፣ ወይም በተሸከርካሪው ላይ የሚፈለግበት ዕዳእንዳለበት በመጥቀሰ እንዲታገድለት ጥያቄ ሲቀርብ አገልግሎት ይሰጠዋል፡፡

የተሽከርካሪ የዕዳና ዕገዳ ስረዛ/ ማንሳት አገልግሎት

 • ማመልከቻ ፎርም
 • የባለጉዳዩን ማንነትና ህጋዊነት ማረጋገጥ፣
 • የታገደው እግድ እንዲነሳ የጠየቀው አካል በትክክል የእርሱ ሰነድ መሆኑን ማለትም የታገደበት ቀንና ቁጥር፣ የታገደበት ጉዳይ፣ ያገደው አካል ማረጋገጥና የተሸከርካሪ ታሪክ ከደረቅ ፋይልና ከኮምፒውተር ተመሳሳይ መሆኑን ማጣራት
 • ከዕግድ የተነሳ መሆኑ እዳ እገዳ የተመዘገበውን እግድ ከኮምፒውተርና ከፋይል በመሰረዝ ማረጋገጫ መስጠት፣
 • ለተሰጠው አገልግሎት በታሪፉ መሠረት የአገልግሎት ክፍያ ማስከፈል፣
 • እግዱ የሚነሳው በባክንኮችና በአነስተኛ የብድር ተቋማት የታገዱ ከሆነ ከላይ የተዘረዘሩት ነጥቦች እንደተጠበቁ ሆነው የብሩ መጠን መገለጽ አለበት
 • በአንድ ተሸከርካሪ ላይ በተለያዩ ባለመብቶች ጠያቂነት በፌደራልና በክልል ፍ/ቤቶች የተሰጡ የተለያዩ እግዶች በተመሳሳይ ጊዜ ከተነሱ ቀድሞ የአፈፃፀም ፋይል ከፍቶ ተሸከርካሪውን ለመረከብ የመጣው የፍርድ ባለመብት በፍርድ ባለ እዳው ይግባኝ ተጠይቆ አፈፃፀሙ እንዳልታገድ ተጣርቶ ተገቢውን አገልግሎት ይሰጠዋል፡፡
 • በአንድ ተሸከርካሪ ላይ በተለያዩ ባለመብቶች ጠያቂነት የተለያዩ የፌደራልና በክልል ፍ/ቤቶች እግድ ቢሰጡና ከፍርድ ቤቶቹ መካከል አንዱ ከባለመብቶቹ ላንዱ እግዱን አንስቶ ፍርድ ቢሰጥና የፍርድ ባለመብቱም የአፈፃፀም ፋይል ከፍቶ አገልግሎት ለማግኘት ሲያቀርብ የሌሎች ፍርድ ቤቶች እግድ ቢኖርም በፍርድ ባለ እዳም ሆነ በሌሎች ባለመብቶች ይግባኝ ተጠይቆ አፈፃፀሙ እንዳልታገደ ተጣርቶ አገልግሎት ይሰጠዋል፡፡
 • የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር /ሊብሬ/ ማቅረብ የእግድ ማንሳት ውሣኔውን መረጃ መያዝና ፋይሉን ኮምፒዮተር ሲስተሙ ላይ መመዝገብ

በቃሊቲ አዲስ አሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫና ፈቃድ ጽ/ቤት የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች፤ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች

የቅድመ ፈተና ምዝገባና የፈተና ቀጠሮ መስጠት
 • የጤንነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት
 • የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የልደት ሰርተፍኬት ወረቀት
 • ለምድቡ የተቀመጠው አግባብነትያለው የትምህርት እና የእድሜ ማስረጃዎች
 • ለምድቡ የተቀመጠውን የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና የጨረሰበት ማስረጃ
የንድፈ ሃሳብ ፈተና መስጠት
 • ቀጠሮ ወረቀት
 • የትምህርት ቤት መታወቂያ(ባጅ)
 • የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
የተግባር ፈተና መስጠት
 • ቀጠሮ ወረቀት
 • የትምህርት ቤት መታወቂያ(ባጅ)
 • የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ
የአዲስ አሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ መስጠት
 • የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ/ፓስፖርት በአካል ይዞ መቅረብ
 • የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ
 • የቀጠሮ ወረቀት
 • የትምህርት ቤት መታወቂያ(ባጅ)
 • የአገልግሎት ክፍያ ብር 150
የውጭ ሀገር የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለውጥ ማድረግ
 • የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ
 • ከኢትዮጱያ ጋር የመንጃ ፈቃድ ለውጥ ለማድረግ የጋራ ስምምነት ያላቸው ሀገሮች ዝርዝር ውስጥ መኖር
 • የዕድሳት ጊዜው ያላለፈበት የውጭ መንጃ ፈቃድና የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ስለመንጃ ፈቃዱ ትክክለኛነት ማረጋገጫ ደብዳቤ
 • የውጭ ጉዳይ የክፍያ ደረሰኝ
 • ከመጡበት ሀገር የትራንስፖርት መ/ቤት ስለ መ/ፈቃዱ የሚገልጽ ደብዳቤ
 • ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝግባ አጂንሲ ያረጋገጠበት ማህተም
 • ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
 • አንድ ጉርድ ፎቶ ግራፍ
 • ባለጉዳይ በአካል መቅረብ  ወይም ለዲፕሎማት ህጋዊ ውክልና ያለው ሰው፤
 • የአገልግሎት ክፍያ 100 ብር
የመከላከያ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ለውጥ ማድረግ
 • የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ/ፎርም
 • አገልግሎት ጠያቂው በአካል መቅረብ
 • ጊዜው ያላለፈበት የመከላከያ መንጃ ፈቃድ
 • ከመከላከያ ስለ መንጃ ፈቃዱ ትክክለኛነቱ የተሰጠ ደብዳቤ
 • የጤና ምርመራ ውጤት(ከሚመለከተው አካል ብቻ)
 • የአገልግሎት ክፍያ 150 ብር
የዕድሳት(የመገበሪያ ጊዜ) ላለፈባቸው አሽከርካሪዎች የተግባር ፈተና መስጠት
 • ለምድቡ ተመጣጣኝ የሆነ ተሽከርካሪ ማቅረብ፤
 • በመ/ቤት ከሆነ ከሚሰራበት መ/ቤት በተሽከርካሪው እንዲፈተን የተፈቀደበት ደብዳቤ
 • የግል ከሆነ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ኮፒ ፤
 • የጤና ምርመራ ወረቀት
 • የመንጃ ፈቃድ ኮፒ
 • ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የኮቴ የተከፈለበት ደረሰኝ
 • ማህደሩ ካለበት ክፍለ ከተማ እንዲፈተን የሚገልጽ ደብዳቤ
 • የአገልግሎት ክፍያ 100 ብር