Home Organizations Info የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ

/ቤታችን የሚሰጣቸው አገልግሎቶች

ሰነድ ማረጋገጥ
የሰነድ ቅጅዎችን ከዋናው ጋር አመሳክሮ ማረጋገጥ(መመዝገብ)
ባለጉዳዮች ሲጠየቁ እንደአስፈላጊነቱ የፊርማ ወይም  የማህተም ናሙና መያዝ
ለመረጋገጥ የሚቀርቡ ሰነዶችን ህጋዊነት ማረጋገጥ
ለመረጋገጥ የሚቀርቡ ሰነዶች ላይ የሚፈረሙ ወይም የፈረሙ ሰዎችን  ችሎታ ፣መብትና  ስልጣን ማረጋገጥ
በህግ ባለቤትነት ማረጋገጫ የሚሠጥባቸውን ንብረቶች ለማስተላለፍ የሚደረጉ ውሎች
Θ ንብረት አስተላላፊው ንብረቱን ለማስተላለፍያለው  ባለመብትነትና
Θ ንብረቱን በመያዣነት ያልተሰጠ ወይም በፍርድ ቤት ትእዛዝ ያልታገደ መሆኑን ማረጋገጥ
ሰነዶች አግባብ ካለው አካል መሰጠታቸውን ማረጋገጥ
ስለተረጋገጡና ስለተመዘገቡ ሰነዶች ስልጣን ባለው ወይም አግባብ ባለው አካል ሲጠየቅ ማስረጃ መስጸት
ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ማከናወን

በኤጀንሲው የሚሰጡ አገልግሎቶችና አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

የውክልና ሥልጣን መስጫ፤ መሻሪያ እና የመተው ሰነድን ማረጋገጥና መመዝገብ

የውክልና ስልጣን መስጫ ሰነድ
ጠቅላላ ውክልና (በፍ/ህግ ቁጥር 2203 መሠረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘ ጋጀ የውክልና ስልጣን መስጫ ሰነድ፣
Θ ወካዩ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የወካይ/የወካዮች/ መታወቂያ፣
Θ የንግድ ማ/ር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣መተዳደሪያ ደንብ፤ ዋና የንግድ ምዝገባ፤እንዳስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ
Θ ከንግድ ማህበራት ውጭ የሆኑ ሌሎች ማህበራት ከሆኑ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክር        ወረቀት፤መተዳደሪያ ደንብ፤ሥራ አስኪያጅነት የሚገልጽ ደብዳቤ፤
Θ በውክልና ሰነዱ ላይ የተጠቀሰ ዝርዝር የንብረት ወይም የመብት ማረጋገጫ ማስረጃ ካለ ይህንኑ  የሚያረጋግጥ ሰነድ፣
ልዩ ውክልና (በፍ/ህግ ቁጥር 2205 መሠረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውክልና ስልጣን መስጫ ሰነድ፣
Θ ወካዩ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የወካይ/የወካዮች/ መታወቂያ ፣
Θ የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ ፣መተዳደሪያ፤ደንብ ዋና የንግድ ምዝገባ፤ እንደአስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ፣
Θ ከንግድ ማህበራት ውጭ የሆኑ ሌሎች ማህበራት ከሆኑ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤መተዳደሪያ ደንብ፤ሥራ አስኪያጅነት የሚገልጽ ደብዳቤ፤
Θ በውክልና ሰነዱ ላይ የተጠቀሰ ዝርዝር የንብረት ወይም የመብት ማረጋገጫ ማስረጃ ካለ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ፣
የቤተሰብ ውክልና (በፍ/ ስ/ ስ ህግ ቁጥር 58 መሠረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውክልና ስልጣን መስጫ ሰነድ፣
Θ ወካዩ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የወካይ/የወካዮች/ መታወቂያ፣
Θ የስጋ ዝምድና መኖሩን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣
Θ የሚወካከሉት ባልና ሚስት ከሆኑ የጋብቻ ማስረጃ፣
Θ በውክልና ሰነዱ ላይ የተጠቀሰ ዝርዝር የንብረት ወይም የመብት ማረጋገጫ ማስረጃ ካለ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ፣
የጠበቃ ውክልና (በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 63 መሠረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውክልና ስልጣን መስጫ ሰነድ፣
Θ ወካዩ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የወካይ/ዮች መታወቂያ፣
Θ የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ ፣መተዳደሪያ ደንብ ዋና የንግድ ምዝገባ፤ እንደአስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ፣
Θ ከንግድ ማህበራት ውጭ የሆኑ ሌሎች ማህበራት ከሆኑ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤መተዳደሪያ ደንብ፤ሥራ አስኪያጅነት የሚገልጽ ደብዳቤ፤
Θ የጥብቅና ፈቃዱ በእዳና እገዳ የተጣራ መሆኑን ማረጋገጥ፤
የውክልና ስልጣንን መሻር እንዲሁም መተው
የውክልና ሥልጣን መሻሪያ/በፍ/ህግ ቁጥር 2226/1/ መሠረት/
Θ  በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውክልና ስልጣን መሻሪያ ሰነድ፣
Θ የውክልና ሻሪው ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ  የሻሪ/ዎች መታወቂያ፣
Θ  ቀደም ሲል የተረጋገጠና የተመዘገበ የውክልና ሥልጣን ሰነድ፣
Θ  ውክልና ለመሻር የቀረበው የንግድ ማህበር ሲሆን ፈራሚው የሚሻረውን ውክልና የሰጠው ሥራ አስኪያጅ ካልሆነ አዲሱ ሥራ አስኪያጅ የተሾመበት ቃለጉባዔ
የውክልና ሥልጣን ስለመተው (በፍ/ህግ ቁጥር 2229/1/ መሠረት)
Θ  በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውክልና ስልጣንን መተው ሰነድ፣
Θ  ውክልናውን የሚተወው ሰው ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ  ውክልናውን የሚተወው ሰው/ዎች መታወቂያ ፣
Θ  ቀደም ሲል የተረጋገጠና የተመዘገበ የውክልና ሥልጣን ሰነድ፣
ትኩረት/ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች
Θ ውክልና ሰጪዎ እኛ ባልና ሚስት ብለው በማንኛውም ሠነድ የማረጋገጥ ሥልጣን በተሰጠው አካል ውክልና ከሰጡ ተወካይ በውክልናው መሰረት አገልግሎት ፈልጐ ሲመጣ በድጋሚ የጋብቻ ማስረጃ መጠየቅ ሳያስፈልግ መስተናገድ ይቻላል፡፡
Θ በውክልና ሥልጣን ማስረጃው ላይ ባል ለሚስት ወይም ሚስት ለባሏ ለባለቤቴ ተብሎ በተሰጠ ውክልና ላይ አንዳቸው ለመገልገል ቢመጡ በድጋሚ የጋብቻ ማስረጃ እንዲያቀርቡ አይጠይቅም፣
Θ በሕግ መሰረት ሞግዚት ሆነው የተሾሙ አባት ወይም እናት ሞግዚት ለሆኑለት ልጅ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ንብረት ማስተዳደርን በተመለከተ ውክልና መስጠት ይችላሉ፡፡
Θ በፍ/ቤት የተሾመ ማንኛውም ሞግዚት ንብረት ማስተዳደርን በተመለከተ 3ኛ ወገን ለመወከል ቢፈልግ ተጨማሪ ከፍ/ቤት ስልጣን ማምጣት አለበት፣
Θ ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል የተሰጠ የውክልና ስልጣን በየትኛ በየትኛውም የውል ሰነድን የማረጋገጥና የመመዝገብ ስልጣን ባለው አካል ፊት ቀርቦ መሻር/መተው ይቻላል፡፡
Θ ብዙ ሰዎች በአንድነት ውክልና ሰጥተው እያለ አንደኛው ወካይ ብቻውን መጥቶ ተወካዩን መሻር ከፈለገ በፍ/ብ/ህ/ቁ/ 2228 /2/ መሠረት
     • የራሱን የመወከል ሥልጣን ድርሻ ለይቶ ተወካዩን መሻር ይችላል፤
     • ተወካዩን ለመሻር በቂ ምክንያት ነው ብሎ ያመነበትን በመሻሪያ ሰነዱ ውስጥ አካቶ እሱም ሆነ ሌሎች   በጋራ ለተወካዩ የሰጡትን ውክልና ሊሽር ይችላል፡፡
Θተወካይ በውክልና ሰነዱ ውስጥ 3ኛ ወገን እንዲወክል ያልተፈቀደለት ቢሆንም በፍ/ሕ/ቁጥር 2215 /3/ ላይ በተቀመጠው መሰረት
     • ድንገተኛ መሰናክል የገጠመው መሆኑን፤
     • የተባለውን ሥራ ለመሥራት የመልካም ሥራ አመራር ያስገደደው መሆኑን፤
     • ስለ ጉዳዩ ለወካዩ ለማሳወቅ ጊዜ የሚያጥረው መሆኑን ገልፆ ለአስተዳደራዊ ተግባራት ብቻ 3ኛ ወገን     ሊወክል ይችላል፡፡
Θ በፊርማ ናሙና ብቻ የሚሰጡ ውክልናዎች በመጀመሪያ በሚሰጡበት ሰዓት ወካዩች ከውል ወይም ከህግ የመነጨ ስልጣን ያላቸው ለመሆኑ እንዲሁም በውክልና ውስጥ የሚጠቀሱ ነገሮች ማስረጃ የሚፈልጉ ሆነው ሲገኙ ይኸው ማስረጃ ያላቸው መሆኑ ተጣርቶ ሊሰጥ ይገባል፡፡
Θ የአስተዳደር ተግባር በፍታብሔር ሕግ ቁጥር 2204 ላይ የተተረጎመው ሲሆን የወካይ ሀብት የማስቀመጥ፣ የመጠበቅ፣ ከ3 ዓመት ለማያልፍ ዘመን የማከራየት፣ በብድር የተሰጠውን ሀብት የመሰብሰብ፣ ከሀብቱ የሚመጣውን ገቢ ተቀብሎ የማስቀመጥና ለተከፈሉ እዳዎች ደረሰኝ የመስጠት ስራዎች ሁሉ እንደ አስተዳደር ተግባር ይቆጠራሉ፡፡
Θ በጠበቃ ውክልና ላይ የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁጥር /63ን በመጥቀስ እንዲሁም በፍ/ሕ/ቁጥር 2204 መሰረት የጉዳይ ማስፈፀም ውክልና ሊሰጥ ይችላል፣
Θ እኛ ወካዮች ብለው በአንድነት በአንድ ሰነድ ላይ ውክልና የሚሰጡ ሰዎች ውክልና መስጠት የሚችሉት የጋራ በሚያደርጓቸው ጉዳዮች ላይ ብቻ እንጂ፤ በጋራ ውክልና በሚሰጡበት ሰነድ ውስጥ የየግል ጉዳያቸውን የሚመለከት ነገር አካተው መስጠት አይችሉም፡፡ በመሆኑም ጉዳያችን አንድ አይነት ስለሆነ ተብሎ በተሰጠ የውክልና ሰነድ ላይ የወካዮችን የየግል ጉዳይ ለይቶ ለ3ኛ ወገን ውክልና ለመስጠት ወይም ለመፈጸም የሚቀርብ የሰነድ ይረጋገጥልኝ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፡፡
Θ ከአንዳንድ የውጭ ሃገር ድርጅቶች ካንትሪ ዳይሬክተር /Country Director/ በሚል በተሰጠ ሰነድ መሠረት አገልግሎት ለማግኘት በሚቀርቡበት ጊዜ ከሰነዱ በተጨማሪ እንደ አገልግሎቱ አይነት ሌሎች በዚህ ማንዋል መሠረት መቅረብ ያለባቸው ማስረጃዎች መሟላት ያለባቸው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በሰነዱ ላይ የተጠቀሰው ግለሰብ ያለውን ሥልጣን እና የድርጅቱን ጸንቶ ያለ ህጋዊ እውቅና ለማረጋገጥ አግባብነት ባለው አካል የጸደቀ የድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ሊቀርብ ይገባል፡፡
Θ የክልል ጠበቃ ፈቃድ በፍ/ቤቶች ወይም ሥልጣን ባላቸው ሌሎች አካላት የታገደ መሆኑ በኤጀንሲያችን የተመዘገበ ሊሆን ስለሚችል በእዳና እገዳ መጣራት ይኖርበታል፡፡

የኑዛዜ፤የትርጉም፤የቃለመሃላ፤የማረጋገጫ/declaration፤ የሰነድ ቅጂዎች ማመሳከሪያ ሰነዶችን ማረጋገጥ እና በሌሎች ሥልጣን ባላቸው አካላት የተረጋገጡ ሰነዶችን መመዝገብ፤

ስለ ኑዛዜ ሰነድ
በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ (በፍ/ህግ ቁጥር/ 881 መሠረት፣)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የኑዛዜ ሰነድ፤
Θ ሁለት ምስክሮች፣
Θ የተናዛዥ እና የምስክሮች መታወቂያ፣
የኑዛዜ መሻሪያ (በፍ/ብ/ህግ/ቁጥር 898 መሰረት፣)
Θ  በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የኑዛዜ መሻሪያ ሰነድ፤2
Θ ሁለት ምስክሮች፣
Θ የኑዛዜ ሻሪው እና የምስክሮች መታወቂያ ፣
Θ ቀደም ሲል ተረጋግጦ ተመዘገበው የኑዛዜ ሰነድ፣
የተተረጐሙ ሰነዶች (በአዋጅ ቁጥር 922/08 አንቀጽ 8/3/ መሠረት)
Θ የተርጓሚው በቃለ መሃላ የተደገፈ ደብዳቤ፤
Θ የተርጓሚው ፈቃድ በእዳና እገዳ የተጣራ መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ ከመተርጐሙ በፊት ያለው ዋና /ኦርጅናል/ ሰነድ፣
Θ በሚፈለገው ቋንቋ ተዘጋጅቶ የቀረበው ሰነድ ሁለት ኮፒ፣
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ በመከላከያ ሠራዊት የክፍል ሹሞች፣ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች እና በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ተረጋግጠው የቀረቡ ሰነዶችን መመዝገብ፣ (በአዋጅ ቁጥር 922/08 አንቀጽ 6 መሠረት)
Θ  ዋና ሰነድና ኮፒ መቅረቡን ማረጋገጥ፣
Θ ሰነዱ ላይ የፈረመው ባለሥልጣን/ኃላፊ
Θ ፊርማ፤
Θ ሙሉ ስምና የስራ ኃላፊነትን የሚገልጽ ቲተር፤
Θ የተቋሙ ማህተም በሰነዱ ላይ መኖሩን ማረጋገጥ፣
Θ በሰነዱ ላይ የፈረመው ባለሥልጣን/ኃላፊ ፊርማ በእዳና እገዳ የተጣራ መሆኑን ማረጋገጥ፣
የሰነድ ቅጂዎችን ከዋናው ጋር ማመሣከር (በአዋጅ ቁ/ 922/2008 አንቀጽ 12 መሠረት)
Θ የሰነድ አቅራቢው መታወቂያ፣
Θ በውክልና ከሆነ የተወካዩ የውክልና ስልጣን ማስረጃ፣
Θ ከህጋዊ ተቋም የተሰጠ ዋና ሰነድ እንዲሁም የሰነዱ ኮፒ፣
የቃለ መሃላ ሰነድ (በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 92/205/ መሠረት፣)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የቃለ መሃላ ማመልከቻ፣
Θ የቃለ መሃላ አቅራቢው መታወቂያ፣
Θ በቃለ መሀላ ሰነድ ውስጥ ማስረጃ የሚጠይቁ የተጠቀሱ ነገሮች ካሉ አግባብነት ያላቸው ማስረጃዎች፣
የፈቃደኝነት ማረጋገጫ/ ዲክለሬሽን
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የፈቃደኝነት ማረጋገጫ ሰነድ፣
Θ ማረጋገጫ ሰጪው ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የማረጋገጫ ሰጪው መታወቂያ፣
Θ በማረጋገጫ ሰነዱ ውስጥ ስለተጠቀሰው ጉዳይ ህጋዊ ማስረጃ ለምሳሌ ዋናው የልደት የምስክር ወረቀት፣ የሕክምና ማስረጃ…፣
Θ በማረጋገጫ ሰጪውና በተቀባዩ መካከል በሕግ መሰረት ዝምድና መኖሩን ማረጋገጥ፣
ልዩ ትኩረት/ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች
Θ  ከውጭ ጉዳይ ሚ/ር ተረጋግጠው ለሚቀርቡ ሰነዶች ባለጉዳዩ ሰነዱን ለማስመዝገብ ኤጀንሲው ዘንድ ይዞ ሲቀርብ የተከፈለበት ደረሰኝ እንዲያቀርብ ወይም እንዲያሳይ አይገደድም፣
Θ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ከውጭ ሀገራት የሚመጡ የውክልናና መሰል ሰነዶችን ስለትክክለኛነታቸው ማረጋገጫ ሲጠይቁ ኤጀንሲው በሰነዱ ላይ ያለውን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ሃላፊ የፊርማ ናሙና መሆኑን ከማረጋገጥና ከመመዝገብ ውጪ ሰነዱን መርምሮ ያላረጋገጠና በሰነዱ ውስጥ የተጠቀሰው ሰውም በፊቱ ቀርቦ ያልፈረመ መሆኑን ገልፆ መልስ መስጠት ይገባል፡፡
Θ ከግል ተቋማት የሚመጡ ሰነዶችን በተመለከተ ትርጉም ይሰራልኝ ወይም ኮፒ ይመሳከርልኝ ጥያቄ ሲቀርብ ሰነዱን የሰጠውን ድርጅት የመዘገበው ወይም እውቅና የሰጠው የመንግስት ተቋም በሰነዱ ጀርባ ላይ ማህተም ማድረጉን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
Θ እስቱደንት ኮፒ፣ ሊብሬ፣ የቤት ካርታ፣ የጋብቻ ወይም ያላገባ ማስረጃዎች፣ የልደት ሰርተፍኬት ኮፒ ማመሳከሪያ አይሰራላቸውም፡፡
Θ ማረጋገጫው ልጅን የሚመለከት ሲሆን ሁለቱም ወላጆች ቀርበው የፈቃደኝነት ማረጋገጫውን መስጠት አለባቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ በአካል መገኘት ባልቻለ ጊዜ ፈቃዱን በህጋዊ መንገድ ለሌላኛው ወላጅ የሰጠው መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዞ ከቀረበ ይህንኑ ማስረጃ ከሰነዱ ጋር በማያያዝ ማረጋገጫውን ብቻውን መስጠት ይችላል፡፡
Θ ልዩ ልዩ የሰውነት አካላት ስምምነቶችን ለምሳሌ የኩላሊት ልገሳን በተመለከተ በቃለ መሃላ የሚሸፈን ሆኖ ቃለመሃላውን በሚያደርጉበት ወቅት
• በሃኪሞች ቦርድ የተረጋገጠ የታማሚው ማስረጃ፣
• የለጋሽ የጤና ብቃት ማረጋገጫ፤
• የለጋሽ የጋብቻ ወይም ያላገባ ማስረጃ፣
• የሰጪና የተቀባይ የገቢ መጠን በቃለመሃላ የተረጋገጠ፣
• ማረጋገጫ የሚሰጠው ሰው ያገባ ሲሆን የትዳር አጋሩ ሙሉ ፈቃድና የጋብቻ ማስረጃ፣
• ለጋሽ ያላገባ ከሆነ የቅርብ ቤተሰብ የፈቃደኝነት ማስረጃ በማያያዝ ወደፊት የህግ ማእቀፍ እስከሚዘጋጅለት ድረስ በዚህ መስፈርት መሠረት የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
Θ በቃለ መሃላ የሚረጋገጡ ጉዳዮች በሌላ አካል በማስረጃ ሊረጋገጡ ከሚችሉ ኩነቶች ውጪ መሆን አለባቸው፡፡

ግዙፍነት ያላቸውና የሌላቸውን ንብረቶች በውል የማስተላለፍ እና የማከራየት ሰነዶችን ማረጋገጥና መመዝገብ፣

የተንቀሳቃሽ ንብረት ማስተላለፍ ውል፤(በፍ/ብ/ህ/ቁ/2266 እና 2427 መሠረት፣)
ሀ/ የመኪና ሽያጭ ውል (ለኮድ 1፣ 2 እና 3)
Θ  በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የሽያጭ ውል ሰነድ/ፎርም/
Θ  እዳና እገዳ ስላለመኖሩ የተጣራ መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ  የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ፣
Θ  የሻጭና የገዥ መታወቂያ፣
Θ  ሻጭ እና ገዢ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ ፣ዋና የንግድ ምዝገባ፤ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፣
Θ  የሻጭ ያላገባ ማስረጃ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፣
Θ  ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ የመኪና ዋጋ ግምት፣
Θ  ለኮድ 1 እና 3 ከትራንስፖርት ባለስልጣን እና ከገቢዎች የሚሰጥ ክሊራንስ፤
Θ  ለኮድ 1 እና 3 1ዐ ዓመት ቢሞላውም ከቀረጥ ነፃ ከሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክ ከቀረጥ ነፃ መብት ማስተላለፍ ባለሥልጣን የተፃፈ ደብዳቤ፣
ለ/ የመኪና ሽያጭ ውል (ለኮድ 511፣ ፣35 እና ለመሳሰሉት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የሽያጭ ውል ሰነድ/ፎርም/፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ የተጣራ መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ፣
Θ የሻጭና የገዥ መታወቂያ፣
Θ ሻጭ እና ገዢ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የማህበሩ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤መተዳደሪያ ደንብ፤ሥራ አስኪያጅነት የሚገልጽ ደብዳቤ፤
Θ ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ የመኪና ዋጋ ግምት፣
Θ ከሃይማኖት ተቋማት በስተቀር ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም የተሰጠ የማስተላለፍ የእውቅና/የድጋፍ ደብዳቤ፤
ሐ/ የመኪና ስጦታ ውል፤(የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 2427 መሠረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የስጦታ ውል ሰነድ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ፣
Θ የስጦታ አድራጊውና የስጦታ ተቀባይ መታወቂያ፣
Θ ስጦታ አድራጊው እና ስጦታ ተቀባይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ ፣ዋና የንግድ ምዝገባ፤ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፣
Θ የስጦታ አድራጊው ያላገባ ወይምያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳ አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
Θ ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ የዋጋ ግምት፤
Θ ለኮድ 1 እና 3 ከገቢዎች ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ ክሊራንስ፤
መ/ የመኪና ድርሻ ስጦታ ወይም ሽያጭ ውል፤ (የፍ/ብ/ህ/ቁ/1260-1262)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የሽያጭ ወይም የስጦታ ውል ሰነድ፤
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ የተጣራ መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ ንብረቱ የጋራ መሆኑን የሚገልጽ የባለቤትነት ማስረጃ ሊብሬ፣
Θ የድርሻ ሻጭ/ሰጪ እና ገዢ/ተቀባይ መታወቂያ፣
Θ ድርሻ ሻጭ/ሰጪ እና ድርሻ ገዢ/ተቀባይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የድርሻ ሻጭ/ሰጪ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋሩ የፈቃድ ስምምነት፣
Θ ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ዋና ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፤
Θ ከትራንስፖርት ባለስልጣን የሚሰጥ የመኪና ዋጋ ግምት፣
Θ ለኮድ 1 እና 3 ከትራንስፖርት ባለስልጣን እና ከገቢዎች የሚሰጥ ክሊራንስ፤
Θ መኪናው 1ዐ ዓመት ቢሞላውም ከቀረጥ ነፃ ከሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክ ከቀረጥ ነፃ መብት ማስተላለፍ ባለሥልጣን የተፃፈ ደብዳቤ፣
ሠ/ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ሽያጭ ወይም ስጦታ ውል
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ የሻጭ/ የስጦታ አድራጊ እና የገዢ/የስጦታ ተቀባይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ ከሚመለከተው የመንግስት ተቋም የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ፣ ግምት እና ክሊራንስ፣
Θ ከገቢዎች ክሊራንስ፣
Θ ከቀረጥ ነፃ የገባ ከሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክ ከቀረጥ ነፃ መብት ላላቸው የማስተላላፍ መብት ደብዳቤ፣
Θ የሻጭና የገዥ መታወቂያ፣
Θ ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ዋና ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፤
Θ የሻጭ/ የሰጪ የጋብቻ ወይም ያላገባ ማስረጃ እና የፈቃድ ስምምነት፣
ረ/ የተሽከርካሪ ሞተር ሽያጭ ወይም ስጦታ ውል
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ ከትራንስፖርት ባለሥልጣን የዋጋ የተሰጠ ግምት፣
Θ የሻጭ/ስጦታ አድራጊ እና የገዢ/ስጦታ ተቀባይ መታወቂያ፣
Θ ከቀረጥ ነፃ የገባ ከሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክ የቀረጥ ነፃ መብት ክሊራንስ፣
Θ የሻጭ/ የስጦታ አድራጊ እና የገዢ/የስጦታ ተቀባይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የሻጭ/ የስጦታ አድራጊ እና የገዢ/የስጦታ ተቀባይ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋሩ የፈቃድ ስምምነት ፣
Θ ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ዋና ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፤
Θ የሻጭ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ/ደብዳቤ፡፡
ሰ/ ተለያዩ ተንቀሳቃሽ ማሽነሪዎች ሽያጭ ወይም ስጦታ ውል
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ በተቋሙ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ የተዋዋዩች መታወቂያ፣
Θ የሻጭ/ የስጦታ አድራጊ እና የገዢ/የስጦታ ተቀባይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የሻጭ/ የስጦታ አድራጊ እና የገዢ/የስጦታ ተቀባይ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋሩ የፈቃድ ስምምነት፤
Θ የባለቤትነት ማስረጃ /ማሽነሪው የገባበት ዲክላራሲዩን ወይም በአገር ውስጥ ግዥ የተገኘ ከሆነ የተገዛበት ደረሰኝ፣/
Θ ንግድ ስራ ፈቃድ እና ዋና ምዝገባ ይህ ከሌለ አለመኖሩን የሚገልጽ የንግድ ሚ/ር ደብዳቤ፣
Θ ከቀረጥ ነፃ የገባ ከሆነ ከገቢዎችና ጉምሩክ የቀረጥ ነፃ መብት ዝውውር ደብዳቤ፣
Θ የገቢዎች ክሊራንስ፣
Θ ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ዋና ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፤
ሸ/ የንግድ መደብር/መድብል ሽያጭ ወይም ስጦታ ውል
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ ዋና የንግድ ምዝገባ እና የንግድ ፈቃድ፤
Θ የገቢዎች ክሊራንስ፣
Θ ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ ፣ዋና የንግድ ምዝገባ እና ቃለ-ጉባኤ እንዳስፈላጊነቱ፣
Θ የሻጭ/ስጦታ አድራጊ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፣
Θ የሻጭ/የስጦታ አድራጊው እና የገዢ/የስጦታ ተቀባይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የተዋዋዬች መታወቂያ፡፡
የተንቀሳቃሽ ንብረት ኪራይ ውል
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ የአከራይ እና የተከራይ፣ መታወቂያ፣
Θ የሚከራየው ንብረት የባለቤትነት ማስረጃ፣
Θ የአከራይ ወይም የተከራይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የአከራይ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋሩ የፈቃድ ስምምነት፣
Θ ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ ፣የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ እንደአስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባኤ፣ ዋና የንግድ ምዝገባ፤የንግድ ሥራ ፈቃድ፤
ልዩ ትኩረት/ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች
Θ የመጫን አቅማቸው ከ45 ሰው በላይ የሆኑ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፤ ሃይገር ሚዲ ባስ እና ከ100 ኩንታል በላይ የመጫን አቅም ያላቸው የጭነት ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነፃ የገቡ ቢሆኑም ካለ ቀረጥ ነጻ መብት ፈቃድ ሰጪ ባለሥልጣን እውቅና ሳያስፈለግ በሽያጭ ሊተላለፋ ይችላሉ፡፡ ከዚህ ውጭ የሆኑ ተሸከርካሪዎች ግን ተሽከርካሪዎቹ አገር ውስጥ ከገቡ 1ዐ ዓመት የሞላቸው ቢሆንም ከሚመለከተው አካል ከቀረጥ ነፃ መብት ማስተላለፍን በተመለከተ ደብዳቤ ካላመጡ በስተቀር በሽያጭ ሊተላለፋ አይችሉም፡፡
Θ ከቀረጥ ነፃ የገቡ ተሽከርካሪዎች ከገቢዎች እና ጉምሩክ ባለሥልጣን ፈቃድ ውጭ በሽያጭም ሆነ በስጦታ መተላለፍ አይችሉም፡፡ ውክልናም አይሰጥባቸውም፡፡
Θ በመሠረቱ በሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ሽያጭ ወቅት የሚሰደው የዋጋ ግምት መንገድ ትራንስፖርት ወይም ኮንስትራክሽን ሚ/ር በሚሰጠው ማስረጃ ላይ በመመስረት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ሆኖም ሻጭና ገዥ በሰነድ ተገልጾ ከቀረበው ግምት በላይ ተስማምተው በውላቸው ከገለጹ ያቀረቡት ግምት ዝቅተኛ እስካልሆነ ድረስ በሚመለከታቸው አካላት በተሰጠው ግምት ሳይገደዱ እነሱ ባቀረቡት ከፍተኛ ግምት ሊስተናገዱ ይችላሉ፡፡
Θ የውጭ ሃገር ዜጎች የጋብቻ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታን በሚመለከት ባላቸው ልዩ የዜግነት እና የአኗኗር ሁኔታ ማስረጃውን ማቅረብ የማችሉ ከሆነ፣
• አመልካች የጋብቻ ማስረጃ ማቅረብ የማይችልና ማንኛውንም ሃላፊነት የሚወስድ መሆኑን የሚገልጽ ማመልከቻ፣
• በማመልከቻው መሠረት ተሞልቶ በኤጀንሲው የተረጋገጠ ቃለመሃላ፤
• የተደራጀው ኮሚቴ የአመልካችን ማመልከቻ እና ቃለመሃላ በመመርመር የሰጠው የውሳኔ ቃለጉባዔ፣
• ቃለ-መሀላው የአመልካችን ዝርዝር ማንነት፣ ጋብቻ ካለ የተጋቢ ሙሉ ስም፣ ዜግነት፣የመኖሪያ አድራሻ፣ የተሸከርካሪውን ዝርዝር መረጃ የያዘ መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ ከውጭ ሃገር የሚመጡ ያላገባ ማስረጃዎች ከተሰጡበት ጊዜ ጀምሮ ስድስት ወር ያላለፈባቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ቀኑ መቆጠር ያለበት ሰነዱን መጀመሪያ የሰጠው አካል ከፃፈበት ቀን ጀምሮ መሆን አለበት፡፡ ነገር ግን ሰነዱ ላይ የአገልግሎት ጊዜው የሚያበቃበት ቀን ካለው እስከ ቀነ ገደቡ ድረስ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
Θ በትውልድ ኢትዮጵያውን የሆኑ የውጭ ሃገር ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰጠ ያላገባ ማስረጃም ሆነ የቀበሌ መታወቂያ በማቅረብ አገልግሎት ቢጠይቁ መስተናገድ የለባቸውም፡፡
የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የማስተላለፍ ውል(በፍ///ቁጥር 1723 እና 2875 መሠረት)
ሀ/ የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ወይም ስጦታ ውል
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ የተዋዋዬችና የምስክሮች መታወቂያ፣
Θ ሻጭ/የስጦታ ሰጪ እና ገዢ/ስጦታ ተቀባይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የሻጭ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፣
Θ የሻጭ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ፣
Θ ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ዋና ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፤
Θ በኤጀንሲው የተዘጋጀና በሻጭ የሚሞላ ቅጽ፣
ለ/ የንግድ ድርጅት ቤት ሽያጭ ወይም ስጦታ ውል
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ የዋና ንግድ ምዝገባ እና የንግድ ፈቃድ፤
Θ የሻጭ/የስጦታ አድራጊው ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምነት፣
Θ የገቢዎች ክሊራንስ፣
Θ ሻጭ/ስጦታ አድራጊው እና ገዢ/ስጦታ ተቀባይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የንብረት የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ፣
Θ ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ዋና ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፤
Θ የሻጭ/የስጦታ/ አድራጊው፣ የገዥ/የስጦታ ተቀባዩ እና የሁለት ምስክሮች መታወቂያ፣
ሐ/ የኮንዶሚኒየም ቤት ሽያጭ ወይም ስጦታ ውል፤
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ የባለቤትነት ካርታ ጀርባው ስለትክክለኛነቱ የተረጋገጠ ማህተም፣
Θ የኮንዶሚኒየሙ ባለቤት ቤቱን ከተረከበው አምስት አመት ስለመሙላቱ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማረጋገጫ ደብዳቤ፣
Θ የተዋዋዬችና የሁለት ምስክሮች መታወቂያ፣
Θ ሻጭ/የስጦታ አድራጊው እና ገዢ/የስጦታ ተቀባይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ዋና ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፤
Θ የሻጭ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፣
መ/ በማህበር የተሰራ ቤት ሽያጭ ወይም ስጦታ ውል
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ የባለቤትነት ካርታ ጀርባው ስለትክክለኛነቱ በማህተም የተረጋገጠ፣
Θ ከክፍለ ከተማ ማህበራት ማደራጃ ዕዳ ዕገዳ እንደሌለበት የማረጋገጫ ደብዳቤ፣
Θ የሻጭ/የስጦታ አድራጊ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
Θ የተዋዋዬችና የሁለት ምስክሮች መታወቂያ፣
Θ ሻጭ/የስጦታ አድራጊው እና ገዢ/የስጦታ ተቀባይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ በግብር ደረሰኝ ኮፒ ላይ የክፍለ ከተማ ማህተም፣
ሠ/ የማይንቀሳቀስ ንብረት የድርሻ ስጦታ ወይም ሽያጭ ውል፤ (በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1260 አና 1261 መሠረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፤
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ የተጣራ መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ ንብረቱ የጋራ መሆኑን የሚገልጽ የባለቤትነት ማስረጃ፣
Θ የድርሻ ሻጭ/ሰጪ እና ገዢ/ተቀባይ እና የምስክሮች መታወቂያ፣
Θ የድርሻ ሻጭ/ሰጪ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የድርሻ ሻጭ/ሰጪ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፣
Θ ንብረቱ የንግድ ማህበር ከሆነ የማህበሩ መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፣ዋና ምዝገባ፣ እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ እና የገቢዎች ክሊራንስ፤
ረ/ የሊዝ መብት ሽያጭ ወይም ስጦታ ውል
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የሊዝ ውል፣
Θ የሻጭ/የሰጪ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፣
Θ የተዋዋይ ወገኖች እና የምስክሮች መታወቂያ፣
Θ ሻጭ/የሰጪ እና ገዢ/የተቀባይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የሚተላለፈው የሊዝ መብት የንግድ ድርጅት ከሆነ ከገቢዎች ክሊራንስ፤
Θ የንግድ ማህበር ከሆነ መመስረቻ ጽሑፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ እና የንግድ ዋና ምዝገባ እና እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፤
ልዩ ትኩረት/ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች
Θ ባል ለሚስት፣ሚስት ለባል ወይም ወራሽ የሆኑ ልጆች በህይወት ላሉ ወላጆች ድርሻ መልቀቅ አይችሉም፡፡ ነገር ግን ባል ወይም ሚስት አንዱ ሌላውን በኑዛዜ ወራሽ በሚሆንበት ጊዜ ወራሽ ሆነው ስለሚቆጠሩ በውርስ ያገኙትን ንብረት በተመለከተ ከሌሎች ወራሾች ጋር የድርሻ መልቀቅ ውል ሊዋዋሉ ይችላሉ፡፡
Θ የውርሱ ሀብት የአክሲዩን መብት ከሆነ በወራሾች መካከል ብቻ በስጦታ ወይም በሽያጭ ውል ማስተላለፍ የሚቻል ሲሆን ክሊራንስ አይጠየቁም፡፡
Θ በስጦታ፣ በውርስ፣ በሽያጭ ወይም በሌላ መንገድ ተገልጋዮች ንብረት ለማስተላለፍ ሲመጡ ካርታው ከጀርባው ከተረጋገጠና የወራሾች ዝርዝር ከጀርባው ከተፃፈ ወደ ኋላ ሄዶ ሌሎችን የወራሽነት ማስረጃዎች ማየት ሳያስፈልግ መስተናገድ ይችላሉ፡፡
Θ በውርስ ወይም በስጦታ የተገኘ ንብረትን ለማስተላለፍ ወይም ለማከራየት የጋብቻ ማስረጃ አይጠየቅም፡፡
Θ በውሉ ውስጥ ቅድሚያ ክፍያን በተመለከተ የተገለጸ ነገር ካለ ይህንኑ የሚገልጽ የቅድሚያ ክፍያ ደረሰኞች መቅረብ አለባቸው፡፡
Θ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ውጭ የሚገኙ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን የማስተላለፍ ወይም የማከራየት አገልግሎት ማግኘት የሚቻለው ንብረቶቹ በሚገኙበት ክልል/ከተማ አስተዳደር ሲሆን፤ በመሆኑም በአዲስ አበባ በሚገኙ የኤጀንሲው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ሊስተናገዱ አይችሉም፡፡
Θ ከጋብቻ በፊት በኤጀንሲው ቀርበው የንብረት ማግለል ውል ያደረጉ ወይም በፍ/ቤት ያጸደቁ ተጋቢዎች ንብረታቸውን ለማስተላለፍ ወይም ለማከራየት ሲመጡ የትዳር አጋራቸው ስምምነት አያስፈልግም፡፡ ሆኖም የንብረት ማግለሉ ስምምነት አሁን ካለው የትዳር አጋር ጋር የተደረገ ሊሆን ይገባል፡፡
Θ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን በተመለከተ ንብረት ለመግዛትና ለመሸጥ ሁለቱም ወለጆች ሊገኙ ይገባል ወይም አንዱ ለሌላው የውክልና ሥልጣን የሰጠ ከሆነ መስተናገድ ይቻላል፡፡ ሆኖም በልጁ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ ሞግዚቱ ማንም ቢሆን በፍ/ቤት የተሰጠ ተጨማሪ ስልጣን ሊያቀርብ ይገባል፡፡
Θ ከመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ የተሰጣቸው ካርታ ማህተም ሳያስፈልግ አገልግሎት ይሰጣቸዋል፡፡
Θ ነባሩ ካርታ እና ከይዞታ አስተዳደር የሽግግር ጊዜ ጊዜያዊ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የጀርባ ማህተም መደረግ አለበት፡፡
የማይንቀሳቀስ ንብረት የኪራይ ውሎች፣ (በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 2896 መሠረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ፣
Θ ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣፣
Θ የአከራይ ያላገባ ወይም ያገባ ማስረጃ እና የፍቃድ ስምምነት፣
Θ የሕንጻ መጠቀሚያ ፈቃድ የምስክር ወረቀት እንደአስፈላጊነቱ፣
Θ አከራይ ወይም ተከራይ የንግድ ማሕበር ከሆነ የመመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ፣
የንግድ ዋና ምዝገባ እና ንግድ ፈቃድ እንዲሁም ቃለጉባኤ እንደአስፈላጊነቱ፣
Θ አከራይ ለትርፍ ያልተቋቋመ ማህበር ከሆነ ከሚመለከተው አካል የማከራየት የፈቃድ መተደዳሪያ ደንብ፤ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤
Θ የተዋዋዮች መታወቂያ፤
ልዩ ትኩረት/ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች
Θ ካርታው በባንክ ወይም በሌሎች የፋይናንስ ተቋማት የተያዘ ከሆነ ባንኩ ወይም የፋይናንስ ተቋሙ በአድራሻ ለኤጀንሲው በመሸኛ የሚልከው ደብዳቤና የካርታ ኮፒ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ለውስጥ አገልገሎት ያገለግላል፣
Θ የንብረት ማስረጃዎቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከመሸኛ ደብዳቤ ጋር የሚያመጡ ተገልጋዮች ከባንኮች በተጨማሪ ከሌሎች የፋይናንስ ተቋማት መሰል ማስረጃ ሲያመጡ ተቋማቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ህጋዊ እውቅና ያላቸው ስለመሆኑ መረጋገጥ አለበት ፡፡
Θ የተመሳከረው የባንክ ወይም የፋይንናንስ ተቋም ደብዳቤ የሚያገለግለው ባንኩ ወይም ተቋሙ ደብዳቤውን ከጻፉበት ቀን ጀምሮ ለ6 ወር ጊዜ ብቻ ይሆናል፤
Θ ሰነድ አልባ ይዞታዎች፤ በፍርድ አፈጻጸም የተሸጠ፤ በኤጀንሲው ተረጋግጦና ተመዝግቦ የተሸጠ የማይንቀሳቀስ ንብረት ስም ለማዞር በሂደት ላይ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ከሚመለከተው አካል ሲያቀርቡ ለአንድ ዓመት ብቻ ኪራይ ለማከራየት መስተናገድ ይችላሉ፣
Θ ባለ አንድ ፎቅ (G+1) ከዚያ በላይ ለሆኑት የሕዝብ መገልገያ ወይም ከመኖሪያ ውጭ ያሉ ሕንጻዎች ለኪራይ ውል ሲቀርቡ የህንጻም መጠቀሚያ ፈቃድ የምስክር ወረቀት ማቅረባቸውን ማረጋገጥ አለበት፣
Θ የኮንዶሚኒየም ንግድ ቤት ሽያጭን በተመለከተ ልክ እንደሌላው የንግድ ድርጅት ቤት ሽያጭ የሚስተናገድ ይሆናል፣
Θ ሚቀርበው ውል ላይ የንግድ ድርጅቱ በንግድ ሥራ ላይ ያልተሰማራ መሆኑን ኤጀንሲው ባዘጋጀው ቅጽ ላይ ካረጋገጠ ክሊራንስ እንዲያቀርብ አይገደደም፣
/ ንብረቱ በውርስ የተገኘ እና ካርታው ወደ ወራሾች ያልዞረ ሲሆን፣
Θ ከወራሽነት ማስረጃ ጋር በፍ/ቤት የተረጋገጠ የውርስ አጣሪ ሪፖርት፣
Θ ከሚመለከተው አካል ስም ለማዞር በሂደት ላይ መሆኑንና የሚገልጽ ደብዳቤ ሲያቀርቡ
Θ ኪራዩ የሚጸድቀው ከግማሽ በላይ ወራሾች ወይም ከሀብቱ አጋማሽ የበለጠ ቁጥር ድርሻ ያላቸው የቀረቡ ሲሆን፣/የፍ/ብ/ህ/ቁ/1265/2/
/ ከግማሽ በላይ የሆኑ የንብረት ተጋሪዎች በሚቀርቡበት ጊዜ የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 1265 መሠረት ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው በጋራ ስማቸው የተመዘገበ የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ሊቀርብ ይገባል፡፡

ልዩ ልዩ ውሎች

የአእምሮአዊ ንብረት ሽያጭ፤ ስጦታ ወይም የኪራ ውል
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ የፈጠራ ባለቤቱ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ እንደ ፈጠራው ዓይነት ከአእምሮዊ ንብረት ጽ/ቤት ወይም ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚ/ር የተሰጠ የፈጠራ ባለቤትነት ማስረጃ ፣
Θ የፈጠራ ባለቤቱ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፣
Θ አግባብነት ያለው የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
Θ የተዋዋዮች መታወቂያ፣
የብድር ውል ስምምነት (በፍ/ብ/ህ/ቁ/ 2471 መሠረት ፣)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የተዋዋዮች መታወቂያ፣
Θ የተዋዋዮች ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፣
Θ ተበዳሪው የንግድ ማህበር ከሆነ መመስረቻ ጽሑፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ እና የንግድ ዋና ምዝገባ እና እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፤
ከጋብቻ በፊት የሚደረግ የግል ንብረትን ማስመዝገብ ውል፤ (የተሻሻለ የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 42 እና 44 መሠረት፣)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ የተዋዋዮች እና የአራት ምስክሮች መታወቂያ፣
Θ የተዋዋዮች ያላገባ ማስረጃ፣
Θ የንብረት ባለቤትነት ማስረጃ፤
የቅጥር ውል፤ (በዓዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 4 መሠረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የተዋዋዮች መታወቂያ፣
Θ የተቀጣሪው የሙያ ፈቃድ እንደአስፈላጊነቱ፣
Θ የንግድ ማህበር ከሆነ መመስረቻ ጽሑፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ እና የንግድ ዋና ምዝገባ እና እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፤
Θ በግል የተመዘገበ የንግድ ድርጅት ከሆነ የቀጣሪው ሕጋዊ የንግድ ምዝገባ እና ንግድ ፈቃድ፣
የእንደራሴነት ውል፤ (በንግድ ህግ ቁ.328/2/ እና 398 መሰረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የተዋዋዮች መታወቂያ፣
Θ ወራሾች ከሆኑ በፍ/ቤት የተረጋገጠ የወራሽነት ማስረጃና የውርስ ሪፖርት ፣
Θ የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ፣ እንዲሁም የንግድ ዋና ምዝገባ፣
የመያዣውል፤ (በፍ/ብ/ህ/ቁ 2825 እና 3041 መሠረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የመያዣ ውል ሰነድ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ የተዋዋዮች መታወቂያ፣
Θ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሆነ ሁለት የሰው ምስክሮች፣
Θ ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የተዋዋዮች ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፣
Θ በመያዣነት የቀረበው ንብረት የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ፣
Θ የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፤ መተዳደሪያ ደንብ እና ቃለጉባኤ እንደአስፈላጊነቱ ዋና የንግድ ምዝገባ፣
ዳረጐት ውል፤ (በፍ/ብ/ህ/ቁ1962 መሠረት፣)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የዳረጎት የውል ሰነድ፣
Θ የዳረጎት ሰጪው ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፣
Θ የክፍያው ጊዜ የደረሰ ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል የተረጋገጠ የገንዘብ መብት ያለው የውል ሰነድ፣
Θ የተዋዋይ ወገኖች መታወቂያ፣
Θ ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
Θ በውሉ ላይ የተገለጸ ንብረት ካለ የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስረጃ፣
Θ የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፤ ዋና የንግድ ምዝገባ እና እንደአስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፤
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ ባንኮች ባለገንዘብ ሲሆኑ እዳው ከባለእዳው ወደ ተደራጊው እንዲተላለፍ መፍቀዱን በኤጀንሲው አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ፡፡
የአላባ ጥቅም ውል፤ (በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1309 መሠረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የአላባ ውል ሰነድ ፣
Θ ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
Θ የባለቤትነት ማረጋገጫ ማስራጃ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ የአላባ ሰጪና የአላባ ተቀባይ መታወቂያ፣
Θ የአላባ ውሉ የሚደረገው በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ ከሆነ ሁለት ምስክሮች፤
Θ የአላባ ሰጭው ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
Θ የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፤ ዋና የንግድ ምዝገባ እና እንደአስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፤
በጋራ አብሮ የመሥራት ውል/ joint veneture agreement/
Θ በህግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ የተዋዋይ ወገኖች የተናጠል/ የየግላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤
Θ አባል የሚሆነው ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፤ የመተዳደሪያ ደንብ፣ ዋና ምዝገባ እና እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፤
Θ በውል ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር የተገለጸና ማስረጃ የሚያስፈልገው የለቤትነት ወይም የመብት ማጣቀሻ ካለ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ፤
Θ የተዋዋይ ወገኖች መታወቂያ፣
ውል ስለማሻሻል
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የማሻሻያ ውል ሰነድ፣
Θ ቀደም ሲል የተመዘገበው ወይም የሚሻሻለው የውል ሰነድ፣
Θ ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
Θ የተዋዋይ ወገኖች መታወቂያ፤
Θ ውሉ የሚሻሻለው የማይንቀሳቀስ ንብረት ማስተላለፍ ውልን በሚመለከት ሲሆን ሁለት ምስክሮች፤
Θ የተዋዋዮች ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
Θ የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ፤ ዋና የንግድ ምዝገባ እና እንደአስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፤
ውልን ቀሪ ስለማድረግ፤ (በፍ/ብ/ህ/ቁ 1819 መሠረት፣)
Θ ውሉ ቀሪ የሚሆንበት በህግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ ስመ ንብረቱ ያልዞረ መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ ቀደም ሲል የተመዘገበው የውል ሰነድ፤
Θ የቤት ኪራይ ውል ከሆነ የውሉ ዘመን ያለመጠናቀቁን ማረጋገጥ፤
Θ ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
Θ የተዋዋይ ወገኖች መታወቂያ፣
Θ ቀሪ የሚሆነው ውል የማይንቀሳቀስ ንብረት ማስተላለፍን የሚመለከት ሲሆን ሁለት ምስክሮች፤
Θ የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ጽሁፍ፣መተዳደሪያ ደንብ፤ዋና የንግድ ምዝገባ እንደአስፈላጊነቱ ቃለ ጉባዔ፤
ንግድ ፈቃድ በአንድ ሰው ስም የሚወጣበት ውል(በዓዋጅ ቁጥር 980/08 አንቀጽ 5/8 መሠረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ የተዋዋይ ወገኖች መታወቂያ፣
Θ ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
Θ ንብረቱ በውርስ የተገኘ ከሆነ በፍርድ ቤት የጸደቀ የውርስ ንብረት ማጣሪያ ሪፖርት፤
Θ በጋራ የተመዘገበ ንብረት ሲሆን የባለቤትነት ማስረጃ፣
Θ ንብረቱ በጋራ ስም የተመዘገበ ሲሆን የባለንብረቶቹ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
የውርስ መብት ድርሻ መልቀቅ ውል፤ (በፍ/ብ/ህ/ቁጥር 983 መሰረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ የድርሻ ለቃቂው፤ የድርሻ ተቀባይ እና የምስክሮች መታወቂያ፣
Θ ድርሻ ለቃቂ ወይም ተቀባይ ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ ከፍርድ ቤት የተሰጠ የወራሽነት ማስረጃ፣
ልዩ ትኩረት/ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች
Θ ወደፊት ለሚቋቋም የንግድ ማህበር የመመስረቻ ጽሁፍና የመተዳደሪያ ደንብ አያስፈልግም፡፡
Θ የዳረጎት ውል ስምምነት የሚፈጸመው በባለ ገንዘቡ እና በተዳራጊው ወይም በባለዕዳው ወይም በሶስትዮች ሊሆን ይችላል፡፡
Θ ውሉ ቀሪ የሚደረገው በውክልና ከሆነ የውክልናው ሰነድ ተወካዩ ውሉን እንዲያፈርስ በግልጽ ማመልከት አለበት፡፡
Θ በቅጥር ውል ወቅት ተቀጣሪው የሚያቀርበው የትምህርት ወይም የሞያ ብቃት ማስረጃ የተሰጠው ከግል ወይም ከውጭ ሀገር ተቋማት ከሆነ ማስረጃው በሃገር ውስጥ በሚመለከተው አካል የተረጋገጠ መሆን አለበት፡፡
Θ የውርስ መብት ድርሻ መልቀቅ ጥያቄበየሚስተናገደው የውርስ ሃብቱ በወራሾች ስም ከመመዝገቡ በፊት መሆን አለበት፡፡

የንግድ ማህበራት መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ቃለጉባኤ ማረጋገጥና መመዝገብ፤

የንግድ ማህበራትን መመስረቻና መተዳደሪያ ደንብ ማረጋገጥና መመዝገብ፤ (በንግድ ህግ ቁ.284፣ 298፣ 313 እና 517 መሠረት፣)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የመመስረቻ ጽሁፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ ከ4 ኮፒ ያላነሰ፣
Θ የማህበሩን ስያሜ የሚገልጽ ከንግድ ሚ/ር/ ቢሮ የተሰጠ ደብዳቤ፣
Θ የንግድ ማህበሩ የአባላት መታወቂያ፣
Θ በንግድ ማህበሩ ውስጥ በአይነት የሚገባ መዋጮ ካለ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ፣ እንዲሁም የባለንብረቱ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
Θ በአይነት የሚገባ ንብረት ሲኖር እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ ፈራሚዎች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
Θ በማህበሩ ውስጥ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ሰው በአባልነት ተመዝግቦ የሚገኝ ከሆነ የልደት ሰርተፍኬት ወይም በፍርድ ቤት የተሰጠ የሞግዚትነት ማስረጃ፤
Θ የወላጆች የጋራ ፈቃድ ወይም አንዱ ሌላውን የወከለበት የውክልና ስልጣን ማስረጃ፣
የንግድ ማህበራት ቃለ ጉባኤ ማረጋገጥና መመዝገብ፤
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ ቃለ ጉባኤ ከ3 ኮፒ ያላነሰ፣
Θ የስም ስያሜ ለውጥ ሲኖር የስም ስያሜውን የሚያሳይ ደብዳቤ ከንግድ ሚ/ር/ ቢሮ እንዲሁም የገቢዎች ክሊራንስ፣
Θ ፈራሚዎች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
Θ የንግድ ማህበሩ መመስረቻ ፅሁፍ፤ መተዳደሪያ ደንብ፤ዋና የንግድ ምዝገባ እንደአስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፤
Θ በስብሰባው ላይ የተገኙ የአባላት መታወቂያ፣
የውጭ አገር ዜጐች በነባር የንግድ ማህበር ሲገቡ ቃለ ጉባኤውን ማረጋገጥና መመዝገብ፣
Θ በህግ አግባብ የተዘጋጀ የቃለ ጉባኤ፤
Θ የንግድ ማህበሩ መመስረቻ ፅሁፍ፤ መተዳደሪያ ደንብ፤ዋና የንግድ ምዝገባ እንደአስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፤
Θ ፈራሚዎች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
Θ ከንግድ ሚ/ር የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ፣
Θ ከንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን የድጋፍ ደብዳቤ፣
Θ በኢንቨስትመንት አዋጁ መሰረት ሊከፈል የሚገባውን መዋጮ መከፈሉን ማረጋገጥ፣
Θ የገቢዎች ክሊራንስ፤
Θ አዲስ የሚገባው የንግድ ማህበር ከሆነ የመመስረቻ ፅሁፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ እንደአስፈላጊነቱ ቃለ-ጉባኤ፤ ዋና ምዝገባ ወይም የድጋፍ ደብዳቤ፣
የንግድ ማህበራት ውህደት
ሀ/ በንግድ ህግ ቁጥር 549 እና በንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀጽ 9/3/ መሰረት
Θ በሕግ አግባብ የጸደቀ የተናጠል ቃለ ጉባኤ ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መረጋገጡን ማጣራት፣
Θ የውህደት ፈፃሚ ማህበራት የጋራ ቃለ ጉባኤ ከ3 ኮፒ ያላነሰ፣
Θ የማህበሩ ጠቅላላ ካፒታል ከሰላሳ ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን ከንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ኤጀንሲ ውህደቱን የሚፈቅድ ደብዳቤ፣
Θ የሚዋሀዱት የንግድ ማህበራት ለእያንዳንዳቸው የገቢዎች ክሊራንስ፤
Θ የሚዋሃዱት የንግድ ማህበራት የየራሳቸውን ነባር መተዳዳሪያ ደንብና መመስረቻ ጽሁፍ፤ዋና የንግድ ምዝገባ እና እንዳስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፣
Θ በስብሰባው ላይ የተገኙ የማህበሩ አባላት መታወቂያ፣
Θ ፈራሚዎች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
ለ/ የተዋሀዱ የንግድ ማህበራትን መመስረቻ ፅሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ስለማፅደቅ
Θ ውህደት የተደረገበት የጸደቀ ቃለጉባዔ፤
Θ የስም ለውጥ ካለ ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠ ደብዳቤ፤
Θ በህግ አግባብ የተዘጋጀ አዲስ የመመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ፤
Θ የፈራሚዎች መታወቂያ፤
Θ ፈራሚዎች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
የንግድ ማህበራት ከአንድ አይነት ወደ ሌላ አይነት አቋም ለውጥ፤ (በንግድ ህግ ቁጥር 545 እና 547 መሰረት)
Θ ወደ ሌላ አይነት የንግድ ማህበር እንዲለውጥ የተስማሙበት የጸደቀ የቃለጉባኤ፣
Θ የተሻሻለ መተዳዳሪያና መመስረቻ ጽሁፍ፣
Θ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ የስያሜ ለውጥ ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠ ደብዳቤ፤
Θ የገቢዎች ክሊራንስ፣
Θ ነባሩ መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብዋና የንግድ ምዝገባ፤ እንደአስፈላጊነቱ ቃለጉባኤ፤
Θ በስብሰባው ላይ የተገኙ የአባላት መታወቂያ፣
Θ ፈራሚዎች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
ተቋቁሞ የነበረን የንግድ ማህበር ስለማፍረስ፤ (በንግድ ህግ ቁጥር 217፣ 495 እና 542 መሰረት)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ ቃለ ጉባኤ ከ3 ኮፒ ያላነሰ፣
Θ የንግድ ማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብቃለ ጉባኤ እንደአስፈላጊነቱ
Θ በተቋሙ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ መጣራቱን ማረጋገጥ፣
Θ ዋና የንግድ ምዝገባ፤ ካላወጡ ከንግድ ሚር ደብዳቤ፣
Θ የፈራሚዎች የታደሰ መታወቂያዎች፣
Θ ፈራሚዎች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
ልዩ ትኩረት/ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች
Θ የንግድ ማህበር ስራ አስኪያጅ የሚንቀሳቀስ /የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመግዛት/ ለመሸጥ ወይም ለመከራየት ሲመጣ መመስረቻ ጽሁፍ ላይ የስራ አስኪያጁን ስልጣን በተመለከተ በንግድ ህጉና በዚህ መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ የሚሸፈን ይሆናል በሚል የተመለከተ ከሆነ የስራ አስኪያጁ ስልጣን ከንግድ ህጉና ከማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ አንፃር መታየት አለበት፡፡ ነገር ግን የመመስረቻ ጽሁፋና መተዳደሪያ ደንብ ላይ የመሸጥና የማከራየት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል በሚል በግልጽ ከተመለከተ በዚሁ ማስተናገድ ይቻላል፡፡
የስራ አስኪያጁ ተግባራት በንግድ ህጉ ወይም በመመስረቻ ጽሁፍ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን መያዣ ማድረግ ወይም መሸጥ፣ መለወጥ ወይም ማከራየት ስልጣን እንዳለው በግልጽ ካልተመለከተ ሊስተናገድ አይችልም፡፡
Θ ከሃምሳ በላይ አባላት ያላቸው የአክስዩን ማህበሮች ድንገተኛ እና መደበኛ የባለ አክሲዮኖችን ጉባኤ የሚያስተላልፏቸው ውሳኔዎች በተመለከተ፣ (የንግድ ህግ ቁጥር 422 እና 417)
Θ ስብሰባው በህግ አግባብ መጠራቱን የሚገልጽ ማስረጃ ከአጀንዳዎቹ ጋር መያያዙ፣
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የቃለ ጉባኤ ፤
Θ ቃለጉባኤው ሊይዛቸው የሚገቡ የማህበሩ ሙሉ ስም፤ስብሰባው የተደረገበት ቦታ፤ስብሰባው የተደረገበት ቀን፤ በስባሰባው ላይ የተገኙ አባላት ዝርዝር፤ በስብሰባው ላይ ያልተገኙ አባላት ዝርዝር፤ የሁሉም አባላት የአክስዮን ድርሻ መጠን፤ የስብሰባው አጀንዳዎች፤ የውሳኔው ይዘት መግለጽ ይኖርበታል፡፡
Θ በድንገተኛም ሆነ በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተገኙ አባላትን የሚገልጽ የአቴንዳስ ሽት ከቃለ ጉባኤው ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
Θ የድንገተኛም ሆነ የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ቃለጉባኤዎች በተለያዩ ሰነዶች ተዘጋጅተው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
Θ ማንኛውም የባንክ፤የኢንሹራንስና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የመመስረቻ ጽሁፍ፤ መተዳደሪያና ቃለጉባኤዎች የብሄራዊ ባንክ በሰነዶቹ ላይ ማህተም በማድረግ በሸኝ ደብዳቤ ለኤጀንሲው መላክ አለባቸው፡፡
Θ በአይነት የሚደረግ መዋጮ ካለ የተደረገው መዋጮ ለኢንቨስትመንት የተሰጠ የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሆነ ንብረቱ ከሚገኝበት ክልል ከኢንቨስትመንት ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ፤ መዋጮው የሚንቀሳቀስ ንብረት ሲሆንና ከቀረጥ ነፃ የገባ ከሆነ ከሚመለከተው አካል የድጋፍ ደብዳቤ፤
Θ ንብረቱ የሚገኘው ከአዲስ አበባ ውጭ የሚገኝ ከሆነና ከዚህ ቀደም እዳና እገዳ የሌለበትና ህጋዊ ይዞታ ስለ መሆኑ የሚገልጽ በኤጀንሲው አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ፣
Θ በቃለ ጉባኤው ውስጥ አክሲዮኑን በሽያጭ ወይም በስጦታ የማስተላለፍ አጀንዳ ካለበት ከገቢዎች ክሊራንስ መቅረቡን ማረጋገጥ፣
Θ ለአክስዮን ሽያጭና የስም ለውጥ በሚደረግበት ጊዜ እዳና እገዳ ስላለመኖሩ በተቋሙ መረጋገጡን ማጣራት፣
Θ ካፒታሉ ከ30 ሚሊዮን ብር ከሆነ አክሲዩን በሽያጭና በስጦታ ሲተላለፍ ከንግድ ሚ/ር እና ከንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ኤጀንሲ የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ክሊራንስ መቅረብ አለበት፡፡
Θ በንግድ ማህበሩ ስም የተመዘገበ ንብረት ለአባላት የካፒታል ማሳደጊያ ሊውል አይችልም፡፡የንግድ ማህበራት የሚፈርሱት በንግድ ህጉና በመተዳደሪያ ደንባቸው መሠረት ይሆናል፡፡

ለትርፍ ያልተቋቋሙ ማህበራት መተዳደሪያ ደንብ እና ቃለጉባኤ ማረጋገጥና መመዝገብ

ለትርፍ ያልተቋቋሙ ማህበራት መተዳደሪያ ደንብ ማረጋገጥና መመዝገብ፣
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የመተዳደሪያ ደንብ ከ4 ኮፒ ያላነሰ፣
Θ የስም ስያሜውን የሚገልጽ ማስረጃ አግባብነት ካለው የሚመለከተው አካል፣
Θ የፈራሚዎች መታወቂያ፣
Θ የዓይነት መዋጮ ካለ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ፤
Θ የባለንብረቱ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፣
Θ ፈራሚዎች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
ለትርፍ ያልተቋቋሙ ማህበራት ቃለ ጉበኤ ማፅደቅ፣(በዓዋጅ ቁጥር 621/2001 አንቀጽ 73 መሰረት፣)
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የቃለ ጉባኤ ሰነድ ከ4 ኮፒ ያላነሰ
Θ የማህበሩ ጊዜ ያላለፈበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤
Θ በመተዳደሪያ ደንባቸው ላይ የቦርድ አባላት ስም ዝርዝር ከሌለ የቦርድ አባላትን ስም እና ኃላፊነታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከሚመለከተው አካል፤
Θ የፈራሚዎች መታወቂያ፤
Θ የአይነት መዋጮ ካለ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ፤
Θ የንብረት ባለቤቱ ያላገባ ወይም ያገባ ከሆነ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት፤
Θ በንብረቱ ላይ እዳና እገዳ የሌለበት መሆኑን መጣራቱን ማረጋግጥ፤
Θ ፈራሚዎች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት፣ የህብረት ስራ ማህበራት፣ እና እድሮች ሽያጭ ወይም ኪራይ እና ግዥ ውል፣
Θ በሕግ አግባብ የተዘጋጀ የውል ሰነድ፣
Θ ጊዜ ያላለፈበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
Θ አግባብ ባለው አካል የተረጋገጠ መተዳደሪያ ደንብ፣
Θ የማህበሩ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ፤
Θ እዳና እገዳ መጣራቱን ማረጋገጥ፤
Θ ማህበራቱ ከተቋቋሙበት ዓላማ አንጻር ንብረት ለመሸጥ፤ ለማከራየት፤ለመስጠት ወይም ለመግዛት የተፈቀደላቸው መሆኑን ከሚመለከተው አካል ደብዳቤ፣
Θ ተዋዋዮች ከህግ ወይም ከውል የመነጨ ስልጣን ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤፣
Θ የተዋዋይ ወገኖች እና እንደአስፈላጊነቱ የምስክሮች መታወቂያ፡፡

ስለማንነት ማረጋገጫዎችና አጠቃላይ ማሳሰቢያዎች

በኤጀንሲው ተቀባይነት ያላቸውን የማንነት ማረጋገጫዎች
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የማንነት ማረጋገጫዎች ሲቀርቡ
Θ ለዘመኑ የታደሱ፣
Θ ፎቶ ግራፍ የተለጠፈባቸው፣
Θ ማህተሙ በአግባቡ ያረፈባቸው፣
Θ ስርዝ ድልዝ የሌለባቸው፣
Θ መታወቂያውን የሰጠው ኃላፊ ፊርማ፣ ስምና ኃላፊነት በቲተር ወይም በእጅ ጽሁፍ በትክክል ያረፈባቸው መሆን አለባቸው፡፡
ተቀባይነት ያላቸው የማንነት ማረጋገጫዎች አይነቶች፤
Θ የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ፣
Θ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ፤
Θ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሠራተኛነት መታወቂያ፣
Θ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ሠራተኛነት መታወቂያ፣
Θ መንጃ ፈቃድ፣ (አለም አቀፍን ጨምሮ)
Θ ፓስፖርት፣
Θ ከደህንነት፤የኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለስልጣን የሚሰጥ ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ፤
Θ በኢትዮጵያ የኤንባሲዎች መታወቂያ፤
Θ የAU/UN መታወቂያ፤
Θ የጠበቃ ፈቃድ፣
Θ ከውጭ ጉዳይ ሚ/ር ለዲፕሎማቶች የሚሰጥ መታወቂያ፤
Θ የመንግስት ሠራተኞች ጡረታ መታወቂያ፣
Θ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የቀን ተማሪ መታወቂያ፣
Θ የሙያ ሥራ ፈቃድ መታወቂያ፤
Θ የማሪታይም መታወቂያ ናቸው፡፡
አጠቃላይ ማሳሰቢያዎች
Θ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ያሉ ሰዎች አገልግሎት ፈልገው ሲመጡ ከጣቢያ የአጃቢውን ፖሊስና የግለሰቡን ስም የሚገልፅ ደብዳቤ ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
Θ ለሚመለከተው ተብሎ ወይም በተገልጋዩ ስም ተጽፎ የሚመጣን ክሊራንስ ከዋናው ጋር በማመሰክርና የተመሳከረውን ኮፒ በማያያዝ አገልግሎት መስጠት ይቻላል፡፡
Θ መስማት የተሳናቸውና በምልክት ቋንቋ የሚግባቡ ሰዎች ተገልጋይ ሆነው ሲቀርቡ መስማት ከተሳናቸው ማህበር አስተርጓሚ ሰው በደብዳቤ የተመደበላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፡፡
Θ ስጦታው የሚደረገው በውክልና ከሆነ የውክልናው ይዘት የሚተላለፈውን የንብረት ዓይነትና ንብረቱ ለማን እንደሚሰጥ መግለጽ አለበት፡፡ በተመሳሳይ የንግድ ማህበርም ሆኑ ሌሎች ማህበራት ስጦታ ሲያደርጉ የሚተላለፈውን የንብረት ዓይነትና ንብረቱ ለማን እንደሚሰጥ የሚገልጽ ቃለ ጉባኤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
Θ የአስተርጓሚነት ደብዳቤ ይዘው የሚመጡ የውጭ አገር ዜጐች ከኤንባሲዎቻቸው የተሰጠና በውጭ ጉዳይ ሚ/ር በኩል አልፎ የተረጋገጠ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
Θ ማናቸውም ሰነዶች ለአገልግሎት ሲቀርቡ በዕለቱ መቅረብ አለባቸው፡፡
Θ ሰነዶች በተገልጋዮች ከተፈረሙ በኋላ ከኃላፊ እውቅና ውጭ በባለሞያ እጅ ማደር የለባቸውም፡፡ ኃላፊው በቂ ነው በሚለው ተገቢ ምክንያት ሰነዱ እንዲያድር ከፈቀደ አረጋጋጩ ሰነዱ በምን ምክንያት እንዳደረ ማስታወሻ ጽፎ ከሰነዱ ጋር አያይዞ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
Θ ከማህበራዊ ፍ/ቤት የሚሰጡ ያላገባ ማስረጀዎች ተቀባይነት የሚኖራቸው ማዘጋጃ ቤት የሌላቸው የቀበሌ አስተዳደሮች ሲሆኑ፤
Θ የማስረጃው መሸኛ በማህበራዊ ፍ/ቤቱ ወይም በቀበሌው አስተዳደር ጽ/ቤት የተጻፈ ሊሆን ይችላል፡፡
Θ በህግ ወይም ላያቸው ላይ ባለው ማሳሰቢያ/ መግለጫ እድሳት የሚያስፈልጋቸው ሰነዶች ከሚረጋገጠው ሰነድ ጋር የግድ መያያዝ ካለባቸው የአገልግሎት ጊዜያቸው ያላለፈባቸው መሆን አለባቸው፡፡
Θ ያላገባ ማስረጃ መግለጫ ላይ ከዚህን ቀን ጀምሮ ያላገባ በሚል የተገለጸ ነገር ሲኖር ተገልጋዩ ንብረት ለማከራየትና ለ3ኛ ወገን ለማስተላለፍ ሲመጣ መግለጫው ላይ ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የተፈራ ከሆነ የግሉ ስለመሆኑ ተጨማሪ ማስረጃ አይጠየቅም፡፡ ነገር ግን መግለጫው ላይ ከተጠቀሰው ቀን በፊት የተፈራ ከሆነ ንብረቱ የግሉ ብቻ ስለመሆኑ ተጨማሪ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
Θ ለአገልግሎት የሚቀርቡ ማናቸውም ሰነዶች ከመረጋገጣቸው፤ከመመዝገባቸውም ሆነ ዋናው ሰነድ ከኮፒዎች ጋር ከመመሳከሩ በፊት ይዘታቸው ከሃገሪቱ ህጎችና ከማህበረሰባችን የሞራል እሴት ጋር የማይቃረኑ መሆናቸው በኦፊሰሩ ከተመረመሩ በኋላ፡-
Θ የሚመለከታቸው አገልግሎት ጠያቂዎች እና እንደአስፈላጊነቱ ምስክሮቻቸው በቀረበው ሰነድ ላይ በአረጋጋጩ ፊት እንዲፈርሙ ይደረጋል፤
Θ በመቀጠል ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ እንዲከፍሉ ይደረጋል፤
Θ ከዚያም ኦፊሰሩ ሰነዱ ላይ ፈርሞ ቲተሩን ያደርጋል፤
Θ በመጨረሻም በማህተም አዳይ ሠራተኛ አማካይነት የተረጋገጡት ሰነዶች ላይ የኤጀንሲውን ክብ ማህተም አድርጎ የተገልጋዩን ድርሻ ሰነድ ለሚመለከተው ተገልጋይ ይሰጣል፡፡
Θ ማንኛውም ሰነድ እንዲረጋገጥለት ወይም እንዲመዘገብለት የሚጠይቅ ተገልጋይ ከላይ በዝርዝር በተመለከተው ሂደት መሠረት ሰነዱ የተረጋገጠለት ወይም የተመዘገበለት መሆኑን እርግጠኛ መሆን አለበት፡፡ ነገርግን ከሂደቶቹ አንዱን ሳያሟላና ማህተም ሳያስደርግ በሂደት ላይ ያለውን ሰነድ ይዞ ቢሄድ ለሚፈጠረው ችግር ኤጀንሲው ተጠያቂ አይሆንም፡፡
Θ ከሰነድ ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ ማናቸውም ከሌሎች መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የተሰጡና በተገልጋይ በማስረጃነት የሚቀርቡ ህጋዊ ሰነዶች ይዘታቸው የሚነበብና የማያጠራጥር፤ ተገቢው ህጋዊ ማህተም የተደረገበት፤ በሰነዱ ላይ የሚፈርመው ባለሥልጣን ፊርማ፤ ስምና የሥራ ኃላፊነትን የሚገልጽ ቲተር ወይም የእጅ ጽሁፍ ያለበት ሊሆን ይገባል፡፡
Θ ኤጀንሲው ለሰጣቸው ሰነድ የማረጋገጥ፤ የመመዝገብ፤ ኮፒ የማመሳከርና መሰል አገልግሎቶች በሚኒስትሮች ምክር ቤት በጸደቀው ደንብ መሠረት ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል፡፡
Θ በኤጀንሲው የተረጋገጡና የተመዘገቡ ማናቸውም ውሎችና የኑዛዜ ሰነዶችን ቀሪ ለማድረግ የሚመጡ ተገልጋዮች በየትኛውም የኤጀንሲው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች መገልገል ይችላሉ፡፡

ቢሮ አደራሻ

የዋናዉ ቢሮ አደራሻ
ከሜክሲኮ አደባባይ ወረድ ብሎ ከፊሊፕስ ህንፃ ፊትለፊት ጨለለቅ አልሳም ታወር (ከ2ኛ ፎቅ- 4ኛ ፎቅ) ልደታ ክፍለ ከተማ
    • ቴሌ፡ +251-11-553-4788,+251-11-553-7133,+251-11-553-7133
    • ፋክስ +251-11-515-6390
    • ፖ.ሳ.ቁ 22935
    • ኢ-ሜል፡ mj_daro@ethionet.et
ቅርንጫፍ 1-ላንቻ
የቅርነጫፍ አንድ ጽ/ቤት አደራሻ ደብረ ዘይት መንገድ አጎና ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ 1ኛ ፎቅ
ቴሌ፡ +251-11-466-3263
ቅርንጫፍ 2-መሳለሚያ
የጽ/ቤት አደራሻ መሳለሚያ እህል በረንዳ እራብ የገበያ ማዕከል
ቴሌ፡ +251 112 732 359
ቴሌ: +251 112 735 767
ቅርንጫፍ 3-መገናኛ
የጽ/ቤት አደራሻ መገናኛ ድራርቱ ቱ ሉ ህንጻ
ቴሌ፡ +251-11-6551967
ቅርንጫፍ 4-6 ኪሎ
ቅርንጫፍ አራት ስድስት ኪሎ ወደ ገብጽ ኤንባሲ በሚወስደው መንገድ ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢኒስቲትዩት ሕንፃ 2ኛ ፎቅ
ቴሌ፡ +251-11-1-24-02-70
ቅርንጫፍ 5-ጉለሌ
ከኢዜአ ወረድ ብሎ በመሚገኘው ዳርሌ ህንጻ
ቴሌ፡ +251-11-1-55-12-41
ቴሌ:+251-11-1-55-12-43
ቅርንጫፍ 6-አየር ጤና
አየር ጤና አደባባይ አጠገብ ዘውዲቱ ህንጻ
ቴሌ፡ +251-11-438-91-33

ቅርንጫፍ 7-ቃሊቲ
ቃሊቲ ማረምያ ፊት ለፊት ሸገር ህንፃ 2ኛ
ቴሌ፡ 011-439-06-07

ቅርንጫፍ 8-ካሳንቺስ
ካዛንች ዮርዳኖስ ሆቴል ፊት ለፊት እናት ህንፃ 3ኛ ፎቅ
ቴሌ፡+251 115 518 531
ቴሌ: +251 115 152 633