Home Organizations Info የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 320/1995 የተቋቋመና አእምሯዊ ንብረት በቂ የህግ ጥበቃ እንዲያገኝ፣ ሀገር በቀል የፈጠራ ስራዎች እንዲበራከቱ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፋጠን፣ ባህል እንዲዳብር እንዲሁም ፍትሃዊ የንግድ ውድድር እንዲሰፍን አእምሯዊ ንብረትን የሚገዙ ህጎችን የሚያወጣ፣ የሚያስፈፅምና ተፈፃሚነታቸውን የሚከታተል፤ ተጠሪነቱ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሆነ መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡
♥ ጽ/ቤቱ በዋናነት በፓተንት ጥበቃና ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በንግድ ምልክት፣ በቅጅና ተዛማጅ መብቶች እንዲሁም በኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ዘርፎች የሚገኙ የፈጠራ ስራዎችን የመመዝገብና የማስጠበቅ አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡
 የጽሕፈት ቤቱ ሥልጣንና ተግባራት
. የፓተንትና የንግድ ምልክት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማመልከቻዎችን በመቀበል አግባብ ባለው ሕግ መሠረት አስፈላጊውን ምርመራ በማካሄድ ወይም እንዲካሄድ በማድረግ ተገቢውን ውሳኔ መስጠት፣
፪. በሕጋዊ ሰነድ ጥበቃ የተደረገላቸውን የውጭና የአገር ውስጥ የፈጠራ ስራዎችን በጥቅም ላይ መዋላቸውን መከታተል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የግዴታ ፈቃድ መስጠት፣
፫. የፓተንት ማመልከቻ ከመቅረቡ ወይም ቴክኒካዊ ችግሮችን ለመፍታት ምርምር ከመደረጉ በፊት በመስኩ የተሰሩ ተመሳሳይ የፈጠራ ስራዎች መኖራቸውን ለማረጋገጥ የፍለጋ መጠይቆችን መቀበል፣ የፍለጋ አገልግሎት መስጠት፣
፬. የንግድ ምልክት ማመልከቻዎች ከመቅረባቸው በፊት ቀደም ሲል ተመሳሳይ ምልክቶች አለመመዝገባቸውን ለማረጋገጥ የፍለጋ መጠይቆችን መቀበል፣ የፍለጋ አገልግሎት መስጠት፣
፭. የአእምሯዊ ንብረት መብቶች ማተምና ማሰራጨት፣
፮. የአእምሯዊ ንብረት መብቶችን የሚመለከት የመረጃ ሥርዓት መፍጠርና ለተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት፣
. መንግስት የሚያወጣቸው የአእምሯዊ ንብረት አዋጆችና ደንቦች ሥራ ላይ ማዋል፣
. በቅድሚያ የትኩረት መስኮች በፓተንት ሰነዶች የታቀፉ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን መምረጥና ማሰራጨት እንዲሁም ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲውሉ ማበረታታት፣
. የፓተንትና የንግድ ምልክት ጥበቃ ጊዜ ማራዘምና የእድሳት ማመልከቻዎችን መቀበል፣ መሰብሰብና ማደራጀት፣ በሕግ መሰረት ውሳኔ መስጠት፣
. በሕዝቡ ዘንድ የአእምሯዊ ንብረት ግንዛቤ ለመፍጠርና ለማጠናከር ሰፊና የተቀናጀ የአህዝቦት ስልት መቀየስና ሥራ ላይ ማዋል፣
፲፩. በአእምሯዊ ንብረት ጉዳዮችና ጭብጦች ላይ ጥናቶች ማካሄድ፣ በብሔራዊና በዓለምአቀፍ ደረጃ በአእምሯዊ ንብረት መስክ ያሉትን እድገቶች መከታተል፤ የሕግና የፖሊሲ ሃሳቦችን አዘጋጅቶ ለመንግስት ማቅረብ፤
፲፪. የአእምሯዊ ንብረት ፖሊሲዎችንና ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸውን ዓለምአቀፍ ስምምነቶችን ስራ ላይ ማዋል እና/ወይም ሥራ ላይ መዋላቸውን መከታተል፤
፲፫. በአእምሯዊ ንብረት ጉዳዮች ላይ ለሕዝብ፣ ለመንግስት፣ ለግል ድርጅቶችና የሙያ ማህበራት እንዲሁም ለግለሰቦች የምክር አገልግሎት መስጠት፤
፲፬. የፈጠራ ሠራተኞች፣ የደራሲያን፣የሙዚቀኞችና መሰል ማህበራት እንዲቋቋሙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ ማህበራቱን መደገፍና ማጠናከር፤
፲፭. አእምሯዊ ንብረት ባለቤቶችንና የፈጠራ ሥራቸውን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚሹ ባለሃብቶችን ለማገናኘት የሚረዱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤
፲፮. ከሌሎች የውጪ ሀገር፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የአእምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤቶች ጋር ግንኙነትና ትብብር መፍጠር፤
፲፯. ለሚሰጠው አገልግሎት ዋጋ ማስከፈል፤
፲፰. የንብረት ባለቤት መሆንና ውል መዋዋል፤
፲፱. በራሱ ስም የመክሰስና መከሰስ፤
. ዓላማውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉትን ሌሎች ተግባሮች ማከናወን፡፡
በዳይሬክቶሬቶች የሚሰጡ አገልግሎቶች፣ ስታንዳርዶች፣ ቅድመ ሁኔታዎች፣ ዳፊ ማስረጃዎችእና ፈጻሚ አካላት

የፓተንት ጥበቃና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬ

ፓተንት ምንድን ነው?
♥ ፓተንት ምንድን ነው?
• ፓተንት ማለት አዲስ የፈጠራ ስራን ለማስጠበቅ የሚሰጥ መብት ሲሆን በቴክኖሎጂ መስክ ለአንድ የተወሰነ ችግር ተግባራዊ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችልና ፈጠራዉ ከምርት ወይም ከምርት ሂደት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል፡፡
♥ ግልጋሎት ሞዴል ምንድን ነው?
• ይህ የፈጠራ ባለመብትነት የጥበቃ ዓይነት የሚሰጠው ለተግባራዊ አገልግሎት ጥበቃ ላላቸው ለአነስተኛ ፈጠራዎች ሲሆን ይህም በሀገር ውስጥ የፈጠራ ባህልን ለማሳደግና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማበረታታት ነው፡፡
♥ አስገቢ ፓተንት ምንድን ነው?
• በአገራችን ያልተመዘገቡ፣ በውጭ ሀገር ፓተንት የተሰጣቸውና የጥበቃ ጊዜያቸው ያላለፈ የፈጠራ ሥራዎች በአገራችን ለማስጠበቅ የሚሰጥ የጥበቃ ዓይነት ነው፡፡
♥ ፓተንት የሚሰጣቸው የፈጠራ ስራዎች
• አንድ የፈጠራ ስራ አዲስነት፣ፈጠራዊ ብቃትና ኢንዱስትሪያዊ ተግባራዊነት ካለው ፓተንት ሊሰጠው ይችላል፡፡
 የፓተንት መብት ለማን ይሰጣል?
• የፓተንት መብት የሚሰጠው ለፈጠራ ሠራተኛው ነው፤ ወይም ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች በጋራ አንድ የፈጠራ ስራ ካከናወኑ የጋራ የፓተንት መብት ይኖራቸዋል፤
• ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር በአገልግሎት ወይም በቅጥር ውል አማካኝነት እንዲከናወንለት ላደረገው ሰው ወይም ለቀጣሪው ይሆናል፤
• ከቅጥር ወይም ከአገልግሎት ውል ጋር ግንኙነት በሌለው መንገድ የቀጣሪውን ወይም የአሰሪውን ሀብት፤ መረጃ ማምረቻ ወይም አገልግሎት መስጫ ማቴሪያል ወይም መሳሪያ ሳይጠቀም ለሚያከናውነው የፈጠራ ስራ ባለቤት ተቀጣሪው ወይም በውሉ መሰረት ሥራውን የሠራው ሰው ይሆናል፤
• የፈጠራ ሠራተኛውን የግል አስተዋጾኦ የቀጣሪውን ሀብት፣መረጃ፣ የማምረቻ ወይም አገልግሎት መስጫ ማቴሪያል ወይም መሳሪያ በማስተባበር ወይም በውሉ መሰረት ሥራውን በሚሰራው ሰው የተከወኑ በዚህ አንቀጽ 3 ስር ሊካተቱ የማይችሉ የፈጠራ ስራዎች ተቃራኒ ስምምነት ከሌለ በቀር እኩል ድርሻን መሰረት በማድረግ የሁለቱም የጋራ ንብረቶች ይሆናሉ፡፡
 የፓተንት መብት ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ
• በአጠቃላይ የፓተንት መብት ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጥበቃ ለማግኘት የቀረበው ማመልከቻ ከተመዘገበበት ቀን አንስቶ ለ20 ዓመት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ፓተንት ህግ መሰረት ግን የፓተንት መብት ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጥበቃ ለማግኘት የቀረበው ማመልከቻ ከተመዘገበበት ቀን አንስቶ ለ15 ዓመታት ይሆናል ፡፡
• ሆኖም ፈጠራው በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገባ ስራ ላይ እየዋለ መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ ሲቀርብ የፓተንቱ መብት ለተጨማሪ አምስት አመታት ሊራዘም ይችላል፡፡
በፈጠራ ስራ ላይ የሚኖሩ ህጋዊ መብቶች እና ግዴታዎች
.በፈጠራ ስራ ላይ የሚኖሩ ህጋዊ መብቶች እና ግዴታዎች
• ባለ ፓተንቱ ፓተንት የተሰጠውን ፈጠራ በብቸኝነት የመፈብረክ፣ የማከራየት፤ የመሸጥ፤ በውርስ የማስተላለፍ፣ በፈጠራ ስራው የመገልገል ወይም በሌላ ማናቸውም መንገድ የመጠቀም መብት ይኖረዋል፤
• መብቱ ሲጣስ በህግ የመጠየቅ መብት ይኖረዋል፤
• ሶስተኛ ወገኖች ከባለፓተንቱ ፈቃድ ካላገኙ በቀር ፓተንት የተሰጠበትን ፈጠራ ለመጠቀም አይችሉም፤
• ባለ ፓተንቱ በኢትዮጵያ ፓተንት የተሰጠውን ፈጠራ ውጤት ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባት የሞኖፖሊ መብት አይኖረውም፤
• በእንካ ለእንካ ወይም እንደ አግባቡ ኢትዮጵያ በምትገባው ማናቸውም ስምምነት ላይ በመመስረት የውጪ ሀገር ባለመብቶች ኢትዮጵያውያን ያሏቸው መብቶችና ግዴታዎች ይኖራቸዋል፡፡
 የፖተንት ጥበቃ የማይደረግባቸው የፈጠራ ስራዎች

የሚከተሉት ስራዎች የፖተንት ጥበቃ አይደረግላቸውም፡፡

• የህዝብ ሰላም ወይም ስነ-ምግባር የሚፃረሩ ፈጠራዎች፤
• የእፅዋት ወይም የእንስሳት አይነቶች ወይም የእፅዋት ወይም የእንስሳት ውጤቶችን ማስገኘት በስነህይወት ዘርፍ የሚከናወኑ ስራዎች፤
• ጨዋታዎችን ለማካሄድ ወይም የንግድና የኢንዱስትሪ ስራዎችን ለማከናወን የተዘጋጁ ስልቶች፣ ደንቦች፣ ዘዴዎች እንዲሁም የኮምፒዩተር ኘሮግራሞች፣
• ግኝቶች፣ ሳይንሳዊ ቲዎሪዎችና የቅመራ ዘዴዎች
• ሰውን ወይም እንስሳትን በቀዶ ጥገና ወይም በቴራፒ ህክምና ዘዴዎች ለማከም እንዲሁም የሰዎችን ወይም እንስሳትን በሽታ ለመመርመር የሚረዱ ዘዴዎች፡፡
የፓተንት መብት ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
♥ አዲስነት (NOVELTY)
አንድ የፈጠራ ስራ አዲስ ነው የሚባለው በቀደምት ጥበብ ያልተሸፈነ ሲሆን ነው፡፡ ቀደምት ጥበብ ማለት የፈጠራ ስራውን በተመለከተ ማመልከቻ ከገባበት ወይም እንደአግባቡ ከቀዳሚ ቀን በፊት በየትኛውም የአለም ክፍል በተጨባጭ በሚታይ ህትመት ወይም በቃል ወይም ጥቅም ላይ በመዋል ወይም በሌላ ማናቸውም መንገድ የተገለፀ ነገርን ያጠቃልላል፡፡
♥ ፈጠራዊ ብቃት (INVENTIVE STEP)
አንድ የፈጠራ ስራ ፈጠራዊ ብቃት አለው የሚባለው ከማመልከቻው ጋር አግባብነት ካለው ቀደምት ጥበብ አንፃር ሲታይ በመስኩ ተራ እውቀት ላለው ሰው ግልፅ ያልሆነ እንደሆነ ነው፤፤
♥ ኢንዱስትሪያዊ ተግባራዊነት (INDUSTRIAL APPLI CABILTY)
አንድ የፈጠራ ስራ ኢንዱስትሪያዊ ተግባራዊነት አለው የሚባለው በዕደጥበብ፣ በግብርና፣ በማህበራዊ አገልግሎቶችና ሌላ ማናቸውም መስክ ሊሰራ ወይም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ሲሆን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በውጭ ሀገር ጥበቃ ያገኙና የጥበቃ ጊዜያቸው ያላለፈ የፈጠራ ስራዎች በአስገቢ ፓተንት ጥበቃ የሚደረግላቸው ሲሆን ለፓተንት የተገለፁት መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የግልጋሎት ሞዴል ሰርተፊኬት ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
የአዲስነትና የኢንዲስትሪያዊ ተግባራዊነትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አነስተኛ ፈጠራዎች በግልጋሎት ሞዴል ሰርቲፊኬት ጥበቃ ይደረግላቸዋል፤
♥ አዲስነት
አንድ አነስተኛ ፈጠራ ስራ አዲስ ነው የሚባለው ማመልከቻው በተመዘገበበት ቀን በኢትዮጵያ ውስጥ በታተሙ ፅሁፎች ላይ ቀደም ሲል ያልተገለፀ ወይም ለህዝብ ያልቀረብ በይፋ ጥቅም ላይ ያልዋለ ከሆነ ነው፡፡
♥ ኢንዱስትሪያዊ ተግባራዊነት
አንድ የፈጠራ ስራ ኢንዱስትሪያዊ ተግባራዊነት አለው የሚባለው በዕደጥበብ፣ በግብርና፣ በማህበራዊ አገልግሎቶችና ሌላ ማናቸውም መስክ ሊሰራ ወይም ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ሲሆን ነው፡፡ ከፓተንት ጋር ሲነፃፀር የግልጋሎት ሞዴል ቀላል፣ ውድ ያልሆነና ፈጣን የፈጠራ ስራ ማስጠበቂያ መንገድ ነው፡፡
የማመልከቻ አቀራረብ ይዘት
ማመልከቻዎች በተገቢው የማመልከቻ ቅፅ በአማርኛ ወይም በእንግሊዘኛ ቋንቋ ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ ቅፆቹን በነፃ ከጽሕፈት ቤቱ ማግኘት የሚቻል ሲሆን የፓተንትና ግልጋሎት ሞዴል ማመልከቻዎች መግለጫ፣ የመብትወሰን፣ አብስትራክት እና እንደ አስፈላጊነቱ ስእሎችን ያካተተ ይዘት ይኖራቸዋል፡፡
ኢንዱስትሪያል ዲዛይን /ንድፍ
ኢንዱስትሪያል ንድፍ ምንድን ነው?
በፈጠራ፣አነስተኛ ፈጠራና ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ አዋጅ ቁጥር 123/1987 መሰረት ኢንዱስትሪያል ንድፍ ማለት በምርቶች ሰንሰለት ላይ መሰረት አድርጎ ቅርጽን፣ መስመሮችን ፣የቀለሞች ቅንጅት እንዲሁም ከመስመሮች እና ከቀለሞች ጋር የተያያዘ ወይም ያልተያያዘ ቅርጽ በመጠቀም ሊዘጋጅ ይችላል፡፡ ቅንጅቱ ወይም ቅርፁ ለኢንዱስትሪ ወይም ለዕደጥበብ ልዩ መልክ የሚሰጥና በኢንዱስትሪ ወይም በዕደጥበብ ለሚመረት ምርት እንደ ንድፍ የሚያገለግል መሆን አለበት፡፡
♥ ለኢንዱስትሪያል ንድፍ ጥበቃ ማድረግ ለምን ይጠቅማል?
ብራንድን/ምልክትን ተጨማሪ ውበት የሚሰጥ በመሆኑ ምርቱን /አገልግሎቱን ለማስተዋወቅ፤፤
◊ አዳዲስ የገበያ ዕድል ለማግኘትና የምርቶቹን ወይም የአገልግሎቶቹን ዋጋ ለመጨመር ፤፤
◊ የውጪ ንግድን ለማሳደግ እና ትርፍ ለማግኘት፤
◊ ፈጠራን እና የንግድ ውድድርን ለማበረታታት፤
♥ በምዝገባው ምን ዓይነት መብት ይገኛል
የንድፍ ባለመብት በንድፍ የመስራት፣ የመገልገል ወይም በሌላ በማናቸውም መልኩ የመጠቀም መብት ይኖረዋል፡፡
♥ የኢንዱስትሪያዊ ንድፍ መብት ለምን ያህል ጊዜ ይቆያል
የኢንዱስትሪያዊ ንድፍ መብት ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከማመልከቻ ቀን አንስቶ ለአምስት ዓመት ሲሆን ስራ ላይ መዋሉ ከተረጋገጠና ዓመታዊ ክፍያ ከተከፈለ ለተጨማሪ ሁለት አምስት ዓመታት ሊራዘም ይችላል ፡፡
በፓተንት ጥበቃና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የሚሰጡ አገልግሎቶች
[

የፓተንት መረጃ አገልግሎት መስጠት
የፓተንት፤ የአስገቢ ፓተንት፣ የግልግሎት ሞዴልና ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ማመልከቻ አቀራረብ ጋር በተያያዘ የምክር አገልግሎት መስጠት፤
በፓተንት ሰነዶች የታቀፉ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን በሲዲ በርን በማድረግ ለዩኒቨርስቲዎች፤ ለምርምር ተቋማት እና ለመሳሰሉት መስጠት
የሴቶችን ጫና የሚቀንሱና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በመምረጥ ማሰራጨት
የፓተንትና የግልጋሎት ሞዴል ሙሉ መረጃ ኮፒ አድርጎ መስጠት (የሰነድ ቅጅ)
በአጠቃላይ በፓተንት ዙርያ ትምህርታዊ ስልጠና መስጠት
የፓተንትና የግልግሎት ሞዴል የፍለጋ አገልግሎት መስጠት
የፓተንት፤ የአስገቢ ፓተንትና የግልግሎት ሞዴል ማመልከቻዎችን በመቀበል የፎርማሊቲና ስረ-ነገር ምርመራ በማድረግ የባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠት
የኢትዱስትሪያዊ ንድፍ ማመልከቻዎችን በመቀበል የፎርማሊቲና ሰረ-ነገር ምርመራ በማድረግ የባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠት
የኢትዱስትሪያል ንድፍ ፈቃድ ውል መብት ማስተላለፍ
የፓተንትና የግልግሎት ሞዴል የድህረ ምዝገባ አገልግሎት መስጠት
ከፍትህ አካላት ለሚጠየቁ መረጃዎችና ሙያዊ አስተያየቶች ተገቢውን ምላሽ መስጠት
ለፈጠራ ሰራተኞ በዶክመንት አዘገጃጀት ላይ የምክርና የድጋፍ አገልግሎት መስጠት
በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ የምክርና የድጋፍ አገልግሎት መስጠት
♥ በፅ/ቤቱ ጥበቃ ያገኙ የፈጠራ ባለቤቶችን በተለያዩ ሚዲያዎች እንዲተዋወቁ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
የፈጠራ ባለመብቶች የፈጠራ ስራዎቻቸው ወደ ጥቅም እንዲቀየሩ የድጋፍ ደብዳቤዎችን መፃፍና ኢግዚቢሽን ማዘጋጀት
የቲስክ/TISC/ ማዕከላትን በተለያዩ ተቋማት ማቋቋም
ለሶሰተና ወገን የተቃውሞ ጥሪ ፈጠራቸውን በጽ/ቤቱ መጽሄት ይፋ ማድረግ
በፓተንት ጥበቃና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የሚሰጡ አገልግሎቶች
1. የፈጠራ ስራ ማመልከቻ ለማስገባት
ሀ. የውጭ ሀገር ፓተንትን በሀገር ውስጥ በፓተንት ለማስመዝገብ
በአግባቡ የተሞላ የጥያቄ ማቅረቢያ ቅጽ (በ3 ኮፒ)
በውጭ ሀገር ከተመዘገበ አንድ አመት ያልሞላውን የፓተንት ማመልከቻ ሰነድ/ቅጂውን (በ 3 ኮፒ)
የተፃፈበትን ቋንቋ ከአማርኛና ከእንግሊዘኛ ውጭ ከሆነ ከእንግሊዘኛው ወይም ከአማርኛው የትርጉም ሰነድ ጋር (በ3 ኮፒ)
የፈጠራው ሰራተኛ (ኞች) እና የፈጠራው ባለቤቶች የውል ስምምነት ሰነድ (Deed of assignment) (በ3 ኮፒ)
የውክልና ማስረጃ (በ3 ኮፒ) እስከ አንድ ወር ጊዜ ሊቀርብ ይችላል
ለ. ለሀገር ውስጥ የፓተንትና ግልጋሎት ሞዴል ማመልከቻ
አብስትራክት፣መግለጫ፣የመብት ወሰን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ስዕሎችን ያካተተ የፈጠራ ስራ ማመልከቻ ሰነድ (በ3 ኮፒ)
ወኪል ካለ የውክልና ማስረጃ (በ 3 ኮፒ)
ሐ. ለአስገቢ ፓተንት ማመልከቻ
በውጭ ሀገር የጥበቃ ጊዜው ያላለፈበትንና በሀገር ውስጥ ፓተንት ያልተሰጠው የፈጠራ ስራ ማመልከቻ ሰነድ/ቅጂ (በ 3 ኮፒ)
መ. ለኢትዱስትሪያዊ ንድፍ ማመልከቻ
♥ ማመልከቻ ፎርም በ2 ኮፒ መሙላትና ማቅረብ
የንድፉን የፎቶግራፍ ወይም ስዕላዊ መግለጫ 1010 መጠን ማቅረብ
የውጭ ሃገር አመልካች ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ በመወከል የምዝገባ ማመልከቻ ማቅረብ
በውጭ ሀገር ንድፍ የተመዘገበበትን ማስረጃ / Home certificate/ ማቅረብ
♥ ለኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ማመልከቻ ከሁለት ኮፒ ጋር ማቅረብ
ለድርጅት 25 ዶላር ወይም ለግለሰብ 6.25 ዶላር /በወቅቱ የምንዛሪ መሸጫ ዋጋ መሠረት/ ክፍያ መፈጸም
2. ለፈጠራ ስራ ክፍያ ማመልከቻዎች
የፈጠራ ስራውን ክፍያ ማመልከቻ ሰነድ ማቅረብ (በ3 ኮፒ)
3. ለፈጠራ ስራ ማመልከቻ ማሻሻያ
የተሻሻለውን የፈጠራ ስራ ጽሁፍ ሰነድ ማቅረብ (በ3 ኮፒ)
4. ለሠርተፍኬት እድሳት
የፈጠራ ስራው በሀገር ውስጥ በስራ ላይ እየዋለ ስለመሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ የጥበቃ ጊዜው ከማለቁ 3 ወር በፊት ማቅረብ (በ 3 ኮፒ)
5. ለግዴታ ፈቃድ ማመልከቻ
ፈጠራው በሌላ ፓተንት በተሰጠው ስራ ላይ ጥገኛ መሆኑና ይህን ፓተንት የተሰጠውን ፈጠራ ካልተጠቀመ በስተቀር የራሱን ፈጠራ ለመጠቀም የሚቸገር ሲሆን
ባለፓተንቱ ከግዴታ ፈቃድ ጠያቄው የፈቃድ ውል ጥያቄ የደረሰው መሆኑና የግዴታ ፈቃድ ጠያቄው ፍቃዱን በተገቢው ሁኔታና ጊዜ ውስጥ ለማግኘት ያልቻለ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ሲያቀርብ
የግዴታ ፍቃድ ጠያቂው ፓተንት የተሰጠውን ፈጠራ በስራ ላይ ለማዋል የቀየሰውን የስራ እቅድ ፈጠራውን በኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ ለማዋል ብቃት ያለው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ሲያቀርብ
6. ለድጋፍ ደብዳቤ ጥያቄ
የድጋፍ ደብዳቤ ጥያቄ ማመልከቻ ማቅረብ
7. ለፓተንትና ግልጋሎት ሞዴል ሰነድ ቅጂ
♥ የፓተንቱን ወይም የግልጋሎት ሞዴሉን ሰነድ ቁጥር
8. ለፈጠራ ስራ ሰርተፍኬት ባለቤትነት ለውጥ ጥያቄ
በተዋዋይ ወገኖች የተፈረመውን ህጋዊ የለውጥ ስምምነት ሰነድ (በ3 ኮፒ)
ማስታወሻ፡- ስለማንኛውም አይነት አገልግሎት የምክር አገልግሎት መጠየቅና ማግኘት መብት ነው፡፡
የአገልግሎት ክፍያዎች
የአገልግሎት አይነት  

ለግለሰብ

 

ለድርጅት

1 ፓተንት ማመልከቻ 17.5 USD 70 USD
2 ለእያንዳዱ የፓተንት ክፋይ ማመልከቻ 17.5 USD 70 USD
3 ግልጋሎት ሞዴል ማመልከቻ 8.75 USD 35 USD
4 የግልጋሎት ሞዴል ክፋይ ማመልከቻ 17.5 USD 70 USD
5 የማመልከቻ ማስተካከያ 2.5 USD 10 USD
6 የፍለጋና ምርመራ ክፍያ 50 USD 200 USD
7 የፓተንትና ግልጋሎት ሞዴል ህትመት ክፍያ 56.25 USD 225 USD
8 ለፓተንት እድሳት

ከ1ኛ – 11ኛ አመት

18.75 USD 75 USD
9 ለፓተንት እድሳት

ከ12ኛ – 15ኛ አመት

43.75 USD 175 USD
10 ለፓተንት እድሳት 16ኛ አመትና ከዛ በላይ 50 USD 200 USD
11 ለግልጋሎት ሞዴል እድሳት እስከ 5ኛአመት 7.5 USD 30 USD
12 ግልጋሎት ሞዴል እድሳት 6ኛ አመትና ከዛ በላይ 12.5 USD 50 USD
13 ለዘገየ ፓተንትና ግልጋሎት ሞዴል እድሳት ክፍያ ቅጣት 10% 10%
14 የፓተንት መብትን ለተጨማሪ 5 አመት ለማራዘም 50 USD 200 USD
15 የግልጋሎት ሞዴል መብትን ለማራዘም 12.5 USD 50 USD
16 የግዴታ ፈቃድ ለመጠየቅ ማመልከቻ 18.75 USD 75 USD
17 ለአስገቢ ፓተንት ማመልከቻ 18.75 USD 75 USD
18 ለአስገቢ ፓተንት እድሳት 12.5 USD 50 USD
19 የፓተንት ማመልከቻ ጥያቄን ወደ ግልጋሎት ሞዴል ወይም በግልባጩ ለመቀየር  

8.75 USD

 

35 USD

20 የኢትዱስትሪያዊ ንድፍ ማመልከቻ 6.25 USD 25 USD

የንግድ ምልክት ጥበቃና ልማት ዳይሬክቶሬት

ንግድ ምልክት ምን ማለት ነው?
የንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አስፈላጊነት በንግድ ምልክት ምዝገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 ዓ.ም የህግ ማዕቀፍ ውስጥ የተደነገገ ሲሆን ይህ ለደንበኞች የሚያገለግል ማብራሪያ በዋነኛነት ይህንን አዋጅ መሠረት በማድረግ ደንበኞች የንግድ ምልክት ምዝገባ ለማመልከትም ሆነ በጽ/ቤቱ አገልግሎት አሰጣጥና አሰራር ላይ ጠቅለል ያለ ግንዛቤ እንዲያገኙ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
♥ ንግድ ምልክት ምን ማለት ነው?
ንግድ ምልክት ማለት የአንድን ሰው/ድርጅት ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ከሌሎች ሰዎች/ድርጅቶች ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ለመለየት የሚያስችል የሚታይ ምስል ነው፡፡ ምልክቱም ቃላቶችን፣ ንድፎችን፣ ፊደሎችን፣ ቁጥሮችን፣ ቀለሞችን፣ የእቃዎችን ወይም የመያዣዎቻቸውን ቅርጽ ወይም የእነዚሁኑ ቅንጅት ሊይዝ ይችላል፡፡
ንግድ ምልክት ጥበቃ ማድረግ ለምን ያስፈልጋል?
ንግድ ምልክት ጥበቃ ማድረግ የሚያስፈልገው፡-
· እቃ በማምረት እና በማከፋፈል ወይም አገልግሎት በመስጠት የንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መልካም ስምና ዝና ለመጠበቅ፤
· በተመሳሳይ እቃዎችና አገልግሎቶች መካከል መሳከርን በማስወገድ ሸማቾች የሚፈልጉትን ምርት ወይም አገልግሎት በግልጽ ለመለየት እንዲሁም
· በብሔራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ ምቹ የንግድ ውድድር በመፍጠር የንግዱን ማህበረሰብ መልካም ስምና ዝና በመጠበቅ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማስቻል የሀገራችንን ፈጣንና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡
 ለምዝገባ ብቁ ስለሆኑ የንግድ ምልክቶች
ማንኛውም የንግድ ምልክት የአንድን ሰው/ድርጅት ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ከሌሎች ሰዎች/ድርጅቶች ወይም አገልግሎቶች በግልጽ ለመለየት የሚያስችል ከሆነ ሊመዘገብ ይችላል ፡፡ ሆኖም፡-አንድ ሊመዘገብ የሚችል የንግድ ምልክት የምልክቱን ልዩ ባህሪይ የሚቀንስ ወይም የሌላ ሰውን መብት የሚጥስ እስካልሆነ ድረስ ጥበቃ ሊደረግላቸው የማይችሉ ክፍሎችን ሊይዝ ይችላል፡፡
ምሳሌ፡- “North Pole Ice cream” የሚል አንድ ንግድ ምልክት ለ “Ice cream” ምርት ሊመዘገብ ይችላል፡፡ ነገር ግን “Ice cream” የሚለው መጠሪያ አይስክሬም አምራቾች በሙሉ የሚጠቀሙበት ቃል ስለሆነ አመልካቹ ብቸኛ መብት የሌለው መሆኑን በጽሁፍ ማረጋገጥ አለበት፡፡ንግድ ምልክት በጥቁርና ነጭ ወይም በሌላ ቀለም ሊመዘገብ ይችላል፤ በጥቁርና ነጭ ቀለም የተመዘገበ ንግድ ምልክት በማናቸውም የቀለም ቅንጅት ጥበቃ የሚደረግለት ሲሆን የንግድ ምልክቱ የተመዘገበው ከሁለቱ ቀለሞች ውጪ ከሆነ ጥበቃ የሚደረግለት በተመዘገበው የቀለም ቅንጅት ብቻ ይሆናል፡፡
ለምዝገባ ብቁ ስለማይሆኑ የንግድ ምልክቶች
 የእቃዎችን ወይም የአገልግሎቶችን ዓይነት፣ ጥራት፣ ብዛት፣ ጠቀሜታ፣ ዋጋ፣ እቃዎቹ ወይም አገልግሎቶቹ የመነጩበትን ቦታ፤ የተመረቱበትን ወይም የሚቀርቡበትን ጊዜ ወዘተ የያዘ የንግድ ምልክት፣የእቃዎቹን ወይም አገልግሎቶች የመነጩበትን ቦታ ወይም የእቃውን አይነትና ባህሪይ በተመለከተ ሕዝቡን ወይም የንግዱን ማህበረሰብ ሊያሳስት የሚችል ንግድ ምልክት፣ (ሆኖም ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ክልከላዎች ቢኖሩም ንግድ ምልክቱ ጥቅም ላይ በመዋሉ ምክንያት በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገባ የሚታወቅ መሆኑ ከተረጋገጠ ሊመዘገብ ይችላል፡፡)
· በንግድ እንቅስቃሴ ወይም በማህበረሰቡ ውስጥ የተለመዱና በጋራ መግባቢያነት የሚያገለግሉ ቃላቶች/ምልክቶች፤
· ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ሳይገኝ ወታደራዊ አርማ፣ የክብር አርማ፣ ሰንደቅ አላማ ወይም በአህጽሮት ቃል     የተፃፈ የታዋቂ ድርጅቶች ስም ወይም ሌላ ተመሳሳይ መለያዎች፤
· የህዝብን ሰላም ወይም ስነ-ምግባር የሚፃረር የንግድ ምልክት፤
· ድምጽ ወይም ሽታን የያዘ የንግድ ምልክት እንዲሁም
· ያለ ግለሰቡ ፍቃድ የአንድን በህይወት ያለ ግለሰብ ሙሉ ስም በንግድ ምልክትነት ማስመዝገብ አይቻልም፡፡
♥ የንግድ ምልክት ጥበቃ ጊዜ
አንድ የተመዘገበ የንግድ ምልክት በየሰባት አመቱ እድሳት የሚደረግለት ሲሆን በታደሰ ቁጥር የጥበቃ ጊዜውም እየተራዘመ ይሄዳል፡፡
የንግድ ምልክት የሚታደስባቸው ሁኔታዎች፡-
· የቆይታ ጊዜው ካለቀ ጀምሮ ባሉት ሶስት ወራት ያለቅጣት፤
· የሶስት ወራት ጊዜ ካለፈ በደንቡ የተወሰነውን ክፍያ በመክፈል በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ በቅጣት፤
· በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ ያልታደሰ ንግድ ምልከት እንደተተወ ተቆጥሮ መብቱ ይሰረዛል፡፡
የንግድ ምልክት ምዝገባ የሚያስገኘው መብት

የንግድ ምልክት ምዝገባ የሚያስገኘው መብት

አንድን ንግድ ምልክት ሳያስመዘግቡ ለረዥም ጊዜ መጠቀም የንግድ ምልክት ባለቤትነት መብት የሚያስገኝ ቢሆንም በምልክቱ ላይ በሚኖሩ የይገባኛል ክርክሮች ላይ በቀላሉ ውሳኔ ለመስጠት ከማስቸገሩ ባለይ መብትን ለማስከበር ሰፊ ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ ይጠይቃል፡፡ የተመዘገበ ንግድ ምልክት ከሆነ ግን ለባለ መብቱ፡-
የምዝገባ ሰርተፍኬቱ ለሚነሱ ክርክሮች በቂ ማስረጃ ሆኖ ያገለግላል፤
ምልክቱ ከተመዘገበበት እቃዎች ወይም አግልግሎቶች ጋር አያይዞ የመጠቀም፣ ሌላ ሰው እንዲጠቀምበት የመፍቀድ፣ የማከራየትና መብትን ለማስተላለፍ፤
ሌሎች ሰዎች በንግድ ምልክቱ እንዳይጠቀሙ የመከልከል፣ በተለይም በተመሳሳይ ምልክቶች ተመሳሳይ እቃዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ በጉምሩክ በኩል እገዳ እንዲደረግ ለመጠየቅ እንዲሁም
ምልክቱ በሌሎች ሀገሮች በቀላሉ ለማስመዝገብ ያስችለዋል፡፡
የንግድ ምልክት መብት ተፈፃሚነት
የንግድ ምልክት መብት ገሰሳን ለመከላከል ባለመብቱ በማስረጃ የተደገፈ ክስ ሲያቀርብ ስልጣን የተሰጠው ፍ/ቤት፡-
♥ ፈጣንና ጊዜያዊ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል፣
በፍትሀብሔርና ወንጀል ስነ-ስርዓት ህጎች መሠረት ፍተሻ ማካሄድና እቃዎችን መያዝ ይችላል፣
ተከሳሹ የመብት መጣሱን ድርጊት እንዲያቆም የማዘዝና በባለመብቱ ላይ ለደረሰው ጉዳት ካሳ መወሰን ይችላል፡፡
የወንጀል ቅጣትን በተመለከተ፡-
የወንጀል ሕግ የበለጠ ቅጣት የሚያስቀጣ ካልሆነ በቀር በዚህ አዋጅ ጥበቃ ያገኘ መብትን ሆነ ብሎ የጣሰ ማንኛውም ሰው ከ 5 ዓመት በማያንስ እና ከ10 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡
የወንጀል ሕግ የበለጠ ቅጣት የሚያስቀጣ ካልሆነ በቀር በዚህ አዋጅ ጥበቃ ያገኘ መብትን በጎላ ቸልተኝነት የጣሰ ማንኛውም ሰው ከ1 ዓመት በማያንስ እና ከ5 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡
የንግድ ስምና የንግድ ምልክት ልዩነት
♥ የንግድ ስም የአንድ ድርጅት የህጋዊ ሰውነት መለያ ሲሆን ንግድ ምልክት ግን  የአንድን ሰው/ድርጅት እቃዎች ወይም አገልግሎቶች ከሌሎች ሰዎች/ ድርጅቶች እቃዎች ወይም አገልግሎቶች ለመለየት የሚያስችል የሚታይ ምስል ነው፡፡
ንግድ ምልክት ጥበቃና ልማት ዳይሬክቶሬ የሚሰጡ አገልግሎቶች
♥  በንግድ ምልክት ማመልከቻ አቀራረብ ላይ የምክር አገልግሎት መስጠት፤
የንግድ ምልክት ማመልከቻዎችን በመቀበል የፎርማሊቲና ሰረ-ነገር ምርመራ በማድረግ የባለቤትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠት
የንግድ ምልክት ማመልከቻዎች አቀራረብ መስፈርት፣
• ማመልከቻ ፎርም በ2 ኮፒ መሙላትና ማቅረብ
• የምልክቱን ናሙና 33 ሴ.ሜ ስፋት ያለውና ብዛቱ 8 የሆነ በአንድ A4 መጠን ባለው ወረቀት ማቅረብ
• አንድ A4 መጠን ባለው ወረቀት ላይ የምልክቱን አንድ ናሙና በትልቁ ማቅረብ
• ለሀገር ውስጥ ምዝገባ አመልካቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ
• የውጭ ሃገር አመልካች ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ በመወከል የምዝገባ ማመልከቻ ማቅረብ
• የውጭ ሃገር አመልካች ንግድ ምልክቱ በውጭ ሀገር የተመዘገበበትን ማስረጃ /Home certificate/ ማቅረብ
ተቀባይነት ባገኙ የንግድ ምልክት ማመልከቻዎች ላይ የተቃውሞ ጥሪ ማስታወቂያ አዘጋጅቶ መስጠት፤
በተቃውሞ ጥሪ መሰረት ተቃዋሚ ካልቀረበ የምዝገባ የምስክር ወረቀት መስጠት፣
የንግድ ምልክት ፈቃድ ውል መብት ለማስተላለፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት፣
• ፈቃድ የተሰጠበትን ወይም መብት የተላለፈበትን የስምምነት ሰነድ በሰነዶች ማረጋገጫ ወይም አቻ ተቋም የፀደቀበትን ዋናውን ከማመልከቻ ጋር ማቅረብ፣
• የማመልከቻ ቅጽ መሙላት፣
• ጉዳዩን ሰፊ ሀገራዊ ሽፋን ባለው በጋዜጣ ላይ ማውጣት፣
የንግድ ምልክት ዕድሳት ለማድረግ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት፣
• የማመልከቻ ፎርም መሙላትና ማቅረብ፣
• በደንቡ መሠረት ተገቢውን የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣
 የሰነድ ቅጅ ለማግኘት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት
• ማመልከቻ ቅጽ ሞልቶ ማቅረብ
• ለንግድ ምልክት 10 ብር ክፍያ መፈጸም
• ለኢንዱስትሪያዊ ንድፍ ለእያንዳንዱ ቅጂ 0.50 ዶላር /በወቅቱ የምንዛሪ ወሸጫ ዋጋ መሠረት/ ክፍያ መፈጸም
♥  የንግድ ምልክት ፍለጋ አገልግሎት ለማግኘት፣
• የማመልከቻ ቅጽ መሙላት፣
• ፍለጋ የሚካሄድበትን ምልክት ናሙና ማቅረብ፣
• ምልክቱ የሚሸፍነውን ምርት መግለጽ፣
• ለንግድ ምልክት የማጣሪያ ፍለጋ 450 ብር ክፍያ መፈጸም፣
 ለፖሊስ፣ ለፍርድ ቤት፣ ለጉምሩክ እና መሰል የፍትህ ተቋማት መረጃ መስጠት፣
በንግድ ምልክት ምዝገባ ላይ የሚቀርቡ ተቃውሞዎችን መርምሮ ውሳኔ መስጠት፣
በንግድ ምልክት እና ኢንዱስትሪያዊ ንድፍ አሰራር ዙሪያ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠር
Requirements for Application of Trademark (Foreigner applicants)

1. Renewed Home Certificate/trade mark registration certificate)

2. Authenticated Power of Attorney

3. Sample of Trade Mark

• On (1) big size in A-4 paper
• Eight (8) pieces in A-4 paper

4. Completing application form in two (2) copies

5. Application fee 1750 birr for one class, if the trademark subject to a service covers more than one class of goods or services the fee shall include additional payment of 50 % of 1750 birr.

6. After substantive examination, certificate (registration) fee is 3000 birr for one class. If the trademark subject to a service covers more than one class of goods or services the fee shall include additional payment of 50% of 3000 birr.

Requirements for Application of TRADEMARK (DOMESTIC Applicant) (ለሀገር ውስጥ ንግድ ምልክት አመልካቾች)
1. Renewed business license (የታደሰ የንግድ ፍቃድ)
2. When the application of the registration of a trademark is filed through the agent, it shall be an accompanied Authenticated Power of Attorney (ማመልከቻው በወኪል የሚሞላ ከሆነ የውክልና ማረጋገጫ ደብዳቤ)
3. A sample of a trademark(የንግድ ምልክት ናሙና)

• One (1) big size in A-4 paper አንድ በትልቁ በA-4 ወረቀት
• Eight (8) pieces in A-4 paper (8 ትንንሽ በአንድ A-4 ወረቀት

4. Completing application form in two (2) copies (በሁለት ኮፒ የተሞላ የንግድ ምልክት ማመልከቻ)
5. Application fee 1750 birr for one class, if the trademark subject to a service covers more than one class of goods or services the fee shall include an additional payment of 50% of 1750 birr (የማመልከቻ ክፍያ ለአንድ አለም አቀፍ ምድብ ብር 1750 ሆኖም አለም አቀፍ ምድብ በጨመረ ቁጥር ከመጀመሪያው ክፍያ ላይ ተጨማሪ ሀምሳ ፐርሰንት (50)

የኮፒራይትና ማህበረሰቦች እውቀት ጥበቃና ልማት ዳይሬክቶሬት

የቅጅ መብት ምን ማለት ነው?
የስነጽሁፍ፣ የኪነጥበብ፣ የስነጥበብ እና የኮምፒውተር ፕሮግራም የመሳሰሉት የፈጠራ ስራዎች የሚያስገኙት መብት በቅጀና ተዛማጅ መብት አዋጅ ይጠበቃል፡፡ በሃገራችን የቅጂና ተዛማጅ መብትን ጥበቃ ለማድረግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 410/1996 አንድ የፈጠራ ስራ አዲስ እና ግዝፈት ካገኘ (ሊነበብ ወይም ሊደመጥ ወይም ሊታይ በሚችል መልኩ ተዘጋጅቶ ስራው ከተጠናቀቀ) ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የቅጂ መብት እንደሚያገኝና ጥበቃ እንደሚያደርግለት ይደነግጋል፡፡ የቅጂ መብትን መሰረት አድርገው የሚመነጩ ተዛማጅ መብቶችም ጥበቃ ይደረግላቸዋል፡፡
የቅጅ መብት ምን ማለት ነው?
የቅጅ መብት ከአንድ የአዕምሯዊ ውጤት ከሆነ የኪነ ጥበብ ፣የስነፅሁፍ ፣የስነ ጥበብ ወይም የሳይንሳዊ መስኮች ውጤት ከሆነ ስራ የሚመነጭ መብት ነው፡፡
 የቅጅ መብት የሚያስገኙ የፈጠራ ስራዎች የትኞቹ ናቸው?
የቅጅ መብት የሚያስገኙ ሥራዎች የሚከተሉት ናቸው
• መፃህፍት፣ቡክሌት፣መፅሄት ወይም በጋዜጣ ላይ የሚገኝ መጣጥፍ፣
• የኮምፒውተር ፕሮግራም፣
• ንግግር፣ሌክቸር ፣ለአንድ ለተወሰነ ክፍል የሚደረግ መልዕክት አዘል ንግግር፣የሀይማኖት ስብከት እና ሌላ በቃል የቀረበ ሥራ ፣
• ድራማ፣ድራማዊ የሙዚቃ ሥራ በእንቅስቀሴ ብቻ የሚቀርብ ድራማ (ፖንቶማይምስ) የመድረክ ውዝዋዜና ሌላ ለመድረክ ተብሎ የሚሰራ ስራ ፣
• የሙዚቃ፣የኦዲዮቪዥዋል፣የኪነ ህንፃ ስራ፣
• የስዕል ፣የቅብ ፣ የሀውልት፣ የቅርፃርቅርፅ፣ የህትመት የፊደል ቅርፅ ጥልፍ እና ሌላ የስነ ጥበብ ስራ፣
• የፎቶግራፍ ስራ፣
• ስዕላዊ መግለጫ፣ካርታ፣ፕላን፣ንድፍ እና ባለሶስት ገፅታ ከጄኦግራፊ ፣ቶፖግራፊ ኪነ ህንፃ ወይም ከሳይንስ ጋር የተያያዘ ስራ፣
የቅጅ መብት ጥበቃ ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መመዘኛዎች ምን ምን ናቸው ?
በአዋጅ ቁጥር 410/96 አንቀፅ 6/1/ መሠረት ማንኛውም የፈጠራ ባለቤት ያመነጨው የፈጠራ ስራ አላማና የጥራት ደረጃ ግምት ውስጥ ሳይገባ ሁለት መመዘኛዎችን ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡
እነዚህም ፡-
• የሥራው ወጥነት (ከሌላ ያልተኮረጀ)
• ግዙፍነት ማግኘት /ሊታይ ፣ሊሰማ፣ሊባዛ ፣ወይም ሊሠራጭ በሚችል መልኩ መቀረፅ ናቸው
ጥበቃ የማይደረግላቸው ስራዎች ምን ምን ናቸው?
ማንኛውም ሀሳብ፣ የአሠራር ሂደት፣ ሲስተም የአሠራር ዘዴ፣ፅንሰ ሀሳብ፣ ቀመር ፣ለአጠቃላይ ስራ የሚያገለግል የቁጥር ሰንጠረዥ ቅፅ፣ መርህ፣በአንድ ስራ ውስጥ የተብራራ፣ የተገለፀ፣የተተነተነ ወይም የተነገረ ሆነም አልሆነ ግኝት ወይም ዳታ እና የህግ ባህሪ ያላቸው ማናቸውም ይፋ የሆነ የህግ እና የአስተዳደር ሰነዶችና ይፋ የሆነ ትርጓሜያቸው ጥበቃ አይደረግላቸውም፡፡
ተዛማጅ መብት ምን ማለት ነው?
♥ ተዛማጅ መብት ምን ማለት ነው?
ተዛማጅ መብት ማለት ከዋኝ፣የድምፅ ሪከርዲንግ ፕሮዲውሰር፣የብሮድካስቲንግ ድርጅት በስራው ላይ ያለው መብት ነው፡፡
የቅጅ መብት ባለመብት ምን መብቶች አሉት?
የቅጅ መብት ባለመብት ሁለት አይነት መብቶች አሉት፡፡ እነርሱም ፡- የኢኮኖሚ መብትና የሞራል መብት ናቸው፡፡
ኢኮኖሚያዊ መብቶች
የአንድ ሥራ ባለቤት የሚከተሉትን ኢኮኖሚያዊ መብቶች ለመፈፀም ወይም ሌላ ሰው እንዲፈፅማቸው ለመፍቀድ ብቸኛ መብት ይኖረዋል፡፡
ሀ. ሥራን የማባዛት፣
ለ. ሥራን የመተርጐም ፣
ሐ. ሥራን የማመሳሰል፣የማቀናበር ወይም ወደ ሌላ አይነት የመቀየር ፣
መ. በሽያጭ ወይም በኪራይ ኦርጅናል ስራን ወይም ቅጂውን የማከፋፈል
ሠ. ኦርጅናል ስራን ወይም ቅጂውን ከውጭ ሀገር የማስገባት፣
ረ. ኦርጅናል ስራን ወይም ቅጂውን ለህዝብ የማሳየት፣
ሰ. ስራን በይፋ የመከወን፣
ሸ. ስራን ብሮድካስት የማድረግ ፣
ቀ. ስራን በሌላ መንገድ የማሰራጨት፣
የሞራል መብት
የስራ አመንጪው የኢኮኖሚ መብት ባለቤት ቢሆንም ባይሆንም የሚከተሉት የሞራል መብቶች አሉት፡፡
ሀ. ወቅታዊ ሁኔታን በብሮድካስት አማካኝነት ለመዘገብ ባጋጣሚ ወይም በድንገት ከተካተተ ስራ ውጪ የስራ አመንጪነቱ እንዲታወቅ የመጠየቅ፣
ለ. ሳይታወቅ የመቆየት ወይም የብዕር ስም የመጠቀም፣
ሐ. ክብሩንና መልካም ስሙን የሚያጐድፍ የስራ መዛባት ፣መቆራረጥ ወይም በሌላ መልክ መቀየርን የመቃወም እና
መ. ሥራን የማሳተም፣