Home Organizations Info የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን

የባለሥልጣኑ ተልዕኮ
‹‹ታክስና ቀረጥን በፈቃደኝነት የመክፈል ባህልን በማዳበር ህግን ሊያከብር የሚችል ሙያዊ ብቃትና ተነሳሽነት ያለው ባለሙያ በመጠቀም ዘመናዊ የታክስና ቀረጥ አስተዳደር ሥርዓት በመዘርጋት ለአገራዊ እና ለከተማ አስተዳደር ልማት የሚውል ገቢ በብቃት በመሰብሰብ የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነትን ማረጋገጥ፤››
ራዕይ
‹‹በ2017 በአፍሪካ ግንባር ቀደም የሆነ ዘመናዊና ፍትሐዊ የታክስ አስተዳደር ሥርዓት ሰፍኖ አገራዊ ወጪ በአገራዊ ገቢ ተሸፍኖ ማየት፤››
የባለሥልጣኑ ተገልጋዮች
ሀ)ግለሰብ ታክስ/ቀረጥ ከፋዮች እና ሌሎች ተገልጋዮች
ለ)በህግ ሰውነት የተሰጣቸው ድርጅቶች እና ሌሎች የንግድ ማህበራት
ሐ)መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች
መ)መንግስታዊ አካላት
ሠ)ባለድርሻ አካላት

የባለሥልጣኑ የሚሰጡ አገልግሎቶች ዓይነት እና አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች (eligibility criteria)

የታክስ ከፋዮች ምዝገባ ና ስረዛ አገልግሎት

ሀ) በግለሰብ ለሚካሄድ የንግድ ሥራ፣ በተቀጣሪና የሙያ ሥራ ለሚሰራ ሰው
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ የታደሰ የቀበሌ/የገበሬ ማህበር መታወቂያ/የመንጃ ፈቃድ፣
Θ ለውጭ ዜጋ የሥራ ፈቃድ/ፓስፖርት/፣
Θ 2 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
Θ በሞግዚትነት/በእንደራሴነት የሚያስተዳድር ከሆነ የሞግዚትነት/ እንደራሴነት ከፍ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ፣
የይዞታ ማረጋገጫ ወይም የኪራይ ውል(የንግድ ሥራ)፣
ለ) ኩባንያዎች፣ አክስዮን ማህበራት፣ የሽርክና ማህበራት፣ የአሽሙር ማህበራት እና በንግድ ሥራ የተሰማሩ ማናቸውም ማህበራት
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ የጸደቀ የማህበር መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ፣
Θ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በግሉ ያወጣው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ሁለት ከ6 ወር ወዲህ የተነሳዉ ጉርድ ፎቶ፣
Θ በውክልና የሚቀርብ ማመልከቻ ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ተቀጣሪ ከሆነ የደመወዝ መጠን የሚገልጽ የስራ ዉል፣
Θ ከማህበረተኞቹ መካከል የውጭ ዜጋ ካለ ማንነቱን የሚገልጽ ፓስፖርት ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ከኢንቨስትመንት ጽ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ፣
Θ በጥቃቅን ከተደራጀ ከአደራጁ ጽ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ፣
ሐ) የመንግስት የልማት ድርጅቶች
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ ድርጅቱ የተቋቋመበት ደንብ፣
Θ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ የምደባ ደብዳቤ፣
Θ የሥራ አስኪያጁ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
Θ በውክልና የሚቀርብ ማመልከቻ ከሆነ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ፣
Θ መንግስት ከውÜ አካላት ጋር በስምምነት ቋቋመው ከሆነ በዉÜ ጉዳይ ሚ/ርና በሌሎች አስፈፃሚ አካላት የተረጋገጠ ሰነድ፣
መ) የመንግስት ባለባጀት መስሪያ ቤቶች
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ የማቋቋሚያ አዋጅ ወይም ደንብ፣
Θ የስራ አስኪያጅ የሹመት ደብዳቤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
) መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ ሥልጣን ከተሰጠው መንግስታዊ ተቋም የተሰጠ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
Θ የሥራ አስኪያጅነት ማረጋጫ ደብዳቤ እና የሥራ አስኪያጁ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
) የግዴታና ዘርፍ ለተ/እ/ታክስ ምዝገባ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ በማናቸውም የ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ያከናወነው ወይም የሚያከናውነው ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ግምት ከብር     500 ሺህ በላይ ከሆነ ወይም ይሆናል ተብሎ የሚገመት ከሆነ፣
Θ ለተ/እ/ታ የዘርፍ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ቋሚ የመኖሪያ፣ የማረፊያ ወይም የንግድ ቦታ፣ የባንክ ሂሣብ ያለው፣
) ተናጠል ለተ/እ/ታክስ ምዝገባ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ ቋሚ የመኖሪያ፣ የማረፊያ ወይም የንግድ ቦታ፣
Θ ለተ/እ/ታ የመመዝገብ ግዴታ ያለበት መሆኑ ማረጋገጥ፣
Θ የንግድ ስራው በድርጅት አቋም የሚያከናውን መሆን፣
Θ ራሱን የቻለ የሂሳብ አያያዝ ስርዓት መዘርጋትና ያስፈለገበት/ የተገደደበት ምክንያት ማስረዳት፣
Θ ራሱን የቻለ ንኡስ ግ/ከ/መ/ቁጥር ማሟላት፣
Θ የቅርንጫፉ/የስራ ክፍሉ የንግድ ስራ እንቅስቃሴው ዓይነትና የሚገኝበት ቦታ ተለይቶ የሚታወቅና ከ100 ኪ/ሜ በላይ መራቁን ማስረጃ ማቅረብ፣
ተ) ጊዜያዊ ተ/እ/ታክስ ስረዛ
Θ ስራውን ያቆመበትንና የሚጀምርበትን ጊዜ በማመልከቻው ገልፆ ማቅረብ፣
Θ ያለበትን ወቅታዊ ዕዳ ክፍያ አጠናቆ መክፈል፣
ቸ) ቋሚ ተ/እ/ታክስ ስረዛ
Θ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ያለው የ3 ዓመት ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ባሉት 12 ወራት ውስጥ የሚያከናውናቸው ታክስ የሚከፈልባቸው ግብይቶች ጠቅላላ ዋጋ ከብር 500 ሺ የማይበልጥ መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ ታክስ የሚከፈልበትን ግብይት ካቋረጠበት ቀን ጀምሮ በ30 ቀን ጊዜ ውስጥ ምዝገባው እንዲሰረዝ ማመልከቻ ማቅረብ፣
Θ ታክስ ከፋዩ ታክስ የሚከፈልበትን ግብይት የተቋረጠበትን ቀን እና ግብይቱን ካቋረጠበት ቀን ጀምሮ ባለው የ12 ወር ጊዜ ውስጥ ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ለማከናወን ያቀደ መሆን ወይም ያለመሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ፣
Θ የተናጠል ምዝገባ ከሆነ ከሁለት ዓመት ያላነሰ መሆኑ ማረጋገጥ፣
Θ ያለበትን የታክስ ዕዳ ክፍያ አጠናቆ መክፈል፣
Θ የተሰጠውን የምዝገባ ሰርቲፊኬት መመለስ

የትምህርትና ድጋፍ አገልግሎት

ሀ) ለሚዲያ መረጃ መስጠት
Θ ማንነት የሚገልፅ መታወቂያ መያዝና ማሳየት፣
Θ የሚፈለገውን መረጃ በፅሑፍ ወይም በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ከሳምንት በፊት ማቅረብ፣
Θ መረጃ ሚስጥራዊ ያለመሆኑን /በህግ መረጃው እንዳይሰጥ ያልተከለከለ መሆኑን እርግጠኛ መሆን፣
Θ የመረጃ ፍላጎቱ የመ/ቤቱን ኃላፊዎች ለቃለ-መጠይቅ የሚጠይቅ ከሆነ ቀድሞ ቀጠሮ ማስያዝ፣
Θ ቅድመ ዝግጅት እንዲረዳ የመረጃ ፍላጎቱ በምን ዙሪያ የሚያጠነጥኑ መሆኑን ቀድሞ መረጃ መስጠት፣
ለ) ለትምህርትና የጥናት ተቋማት ከቤተ መፀሐፍ መረጃ መስጠት
Θ የትብብር ደብዳቤ ማቅረብ፣
Θ ማንነት የሚገልፅ መታወቂያ መያዝና ማሳየት፣
ሐ) ከመረጃ ነፃነት አዋጅ ጋር የተያያዙ የመረጃ ጥያቄዎች
Θ ጥያቄ በፁሑፍ ማቅረብ፣
Θ አስቸኳይ የመረጃ ጥያቄ ሲቀርብ መረጃው ካልተሰጠ በሰው ህይወትና አካላዊ ደህንነት ላይ የቅርብ ጊዜ አደጋ ሊያስከትል የሚችል መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ፣

የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ አጠቃቀምና ድጋፍ አገልግሎት

ሀ) የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ አቅራቢነት እውቅና ለማግኘት
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ የንግደ ምዝገባና ፍቃድ፣
Θ የተ/እ/ታ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣
Θ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
Θ የሰለጠነ የሰው ሃይል አደረጃጀት(ስራ አስኪያጅ፣ የጥገና ኃላፊ፣ ቴክኒሽያን፣ የሽያጭ ሠራተኛ፣ የመሳሪያ ተቀባይ፣ መሳሪያ አስረካቢ፣ ስልጠና ሰጪ፣ ኦኘሬተር)፣
Θ የቢሮ፤ ለስልጠና እና ለጥገና የሚሆን የተደራጀ ቦታ፣
Θ የ 1 ሚሊዮን ብር ዋስትና፣
ለ) የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ እውቅና ለማግኘት
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ የመሳሪያው ናሙና እና ሌሎች ዶክሜንቶች አደራጅቶ ማቅረብ፣
Θ ከአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ ምህንድስና አካል ውል መዋዋል፣
Θ የማስፈተሻ አገልግሎት ክፍያ መፈፀም፣
Θ ስለመሳሪያው በድንብ ቁጥር 139/1999 አንቀጽ 9፤ 10 እና 11 መሰረት ዕውቅና የሚጠየቅበትን መሳሪያ ባህሪያት የሚያሳዩ ደጋፊ መረጃዎች ማቅረብ፣
ሐ) የሽያጭ ነቁጣ ሶፍትዌር አምራችና አከፋፋይ እውቅና ለማግኘት
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ፣
Θ የተ/እ/ታ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣
Θ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
Θ የሰለጠነ የሰው ሃይል አደረጃጀት (ስራ አስኪያጅ፣ ሶፍትዌር ዴቨሎኘር፣ ስልጠና ሰጪ፣ ኦኘሬተር) የማሟላት፣
Θ ለስልጠና እና ለጥገና የሚሆን የተደራጀ ቢሮና ቦታ፣
Θ የ 1 ሚሊዮን ብር ዋስትና ሰርተፍኬት፣
መ) ለሽያጭ ነቁጣ ሶፍትዌር እውቅና ለማግኘት
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ የሶፍትዌሩ ሶፍትኮፒ እና ሌሎች ዶክሜንቶች አደራጅቶ ማቅረብ፣
Θ ከፈታሽ አካል ውል መዋዋል፣
Θ ማስፈተሻ አገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣
ሠ) የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ እና ሶፍትዌር አቅራቢነት እውቅና ስረዛ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 139/1999 አንቀጽ 15 መሰረት የተዘረዘረ መረጃ ማቅረብ፣

የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ እና ሌሎች አገልግሎቶች

)አዲስ የሽ//መሳሪያ ለስራ ለማዘጋጀት
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ ንግድ ፈቃድ፣ ዋና ምዝገባ፣
Θ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
Θ የተ/እ/ታ ሰርተፍኬት፣
)ዓመታዊ ዕድሳት ለማግኘት
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ
Θ ለግብር ማዕከሉ እና ለአገልግሎት ማዕከል ማሳወቅ፣
Θ ማሽኑን ወደ አገልግሎት ማዕከል ማስገባት፣
ሐ) የማሽን ጥገና
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ ለግብር ማዕከሉና ለአቅራቢው ማሳወቅ፣
Θ ማሽኑ ወደ አቅራቢ እንዲገባ ማድረግ፣
Θ የገባበትን ቀንና ሰዓት መመዝገብ፣
መ)የማሽን አድራሻ ለውጥ ለማድረግ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ የአዲሱ አድራሻ ንግድ ፈቃድ፣ ዋና ምዝገባ፣
Θ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
Θ ደብዳቤ ለአቅራቢው ይዘጋጃል፣
ሠ)የማሽን የባለቤትነት የስም እና የንግድ ስያሜ ለውጥ ለማግኘት
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሁለቱም ሞልተዉ ማቅረብ፣
Θ የባለቤት ለውጡን የሚወስደው ንግድ ፈቃድ፣ዋና ምዝገባ
Θ የተ/እ/ታ ሰርተፍኬት፣
ረ)የሽ//መሳሪያ ተመላሽ ለማድረግ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ የንግድ ፈቃድ፣ ምዝገባው የተቋረጠበት ደብዳቤ፣
ሰ)ተንቀሳቃሽ የሽ/መ/መሳሪያ ለማድረግ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ
Θ ተንቀሳቃሽ ከተፈቀደላቸው የንግድ ዘርፎች ውስጥ መሆኑ፣
ሸ) በአደራ ለማስቀመጥ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ የኪራይ ውል የተቋረጠበት፣
Θ በልማት ምክንያት የፈረሰ ከሆነ የተጻፈ ደብዳቤ፣
Θ በኦዲት/በአወሳሰን/ ጊዜ ላይ መሆናቸው፣ በፍርድ ቤት ጉዳይ፣ በቅሬታ በይግባኝ ወዘተ ሥራ ላይ አለመሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ፣
ቀ)ሰሲስተም ውስጥ ያለው የግብር ከፋይ መረጃ ተሳስቶ ማስተካከያ ሲጠየቅ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ
Θ ማሽኑ ሲገዛ የነበረ መረጃ፣
Θ ሰርቪስ ቡክ፣
Θ ከማሽን የሚወጣው ዜድ ሪፖርት፣
Θ ዋና ምዝገባ፣
Θ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
በ)ኤግዚቢሽን ላይ ለመሳተፍ ተንቀሳቃሽ ማሸን ለመጠቀም
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ
Θ ከአዘጋጁ ባዛሩ ላይ እንደሚሳተፉ የሚገልጽ ደብዳቤ ፣
Θ ማመልከቻ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
Θ ዋና ምዝገባ፣ ንግድ ፈቃድ፣
Θ የተ.እ.ታክስ ሰርተፍኬት (ተንቀሳቃሽ ከተፈቀደላቸው )
ቨ) Z-report በየቀኑ ላለማውጣት የሚቀርብ ጥያቄ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ ከተፈቀደላቸው የስራ ዘርፎች ውጭ መሆን፣
ተ) የሽ//መሳሪያ FD ስህተት የአድራሻ ለውጥና ማስተካከያ ለማድረግ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ የንግድ ፈቃድ ኮፒ፣
Θ የግ/ከ/መ/ቁጥር፣
Θ ሰርቪስ ቡክ፣
Θ ዜድ ሪፖርት፣
ቸ)የንግድ ፈቃድ ለመዝጋት መረጃ ይጣራልኝ ጥያቄ
Θ የመረጃ አጣርቶ በማደራጀት የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ኮፒ፣
Θ ለከብት ዕርድ አገልግሎት መረጃ ፈላጊዎች የዕርድ መስመርና የመስመር ቁጥር፣
Θ ለግሮሰሪ ለሆቴል ለባርና ሬስቶራንት የቢራ፣ የድራፍት፣ የለስላሳ እና አልኮል መጠጥ ወኪል አከፋፋይ ካርድ ፎቶ ኮፒ፣
ኀ. መረጃ ይጣራልኝ የአገልግሎት ጥያቄ
Θ ከቅ/ጽ/ቤት እና ወረዳው የተጻፈ ደብዳቤ፣
Θ ንግድ ፈቃድ ኮፒ፣
Θ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ኮፒ፣
ነ. ከአምራችና አከፋፋይ ድርጅቶች የሚሰበሰብ የሽያጭ መረጃ በማጠናቀር እና በመተንተን ለክልሎች ማሰራጨት
Θ ክልሎች የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ
ኘ.ከክልሎች የሚቀርብ የመረጃ አገልግሎት ጥያቄ
Θ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
Θ መረጃው የሚፈለግበት ዘመን፣
Θ ንግድ ፈቃድ ኮፒ፣
አ)የታክስ ምጣኔ ለውጥ አገልግሎት ጥያቄ
Θ ማመልከቻ
Θ የተ.እ.ታ ተመዝግቢ ከሆኑ ሰርተፍኬት
Θ የንግድ ፈቃዱ
ከ)መብራት መጥፋት ፣ የማሽን ብልሽት ማስታወቅ
Θ ችግርን ማሳወቅ/ በስልክም ሆነ በአካል ፣
Θ የድርጅት/የግለሰቡ ስም መግለፅ ፣
Θ የግ/አ/ቢ/ቁጥር ማስመዝገብ ፣
Θ የማሽን ቁጥር (MRC No) ፣
Θ ብልሽቱ ወይም ችግር የንግድ አድራሻ እና ልዩ ቦታ ፣ ቀንና ሰዓት ማስመዝገብ ፣
Θ የእጅ በእጅ ደረሰኝ የጀመረበት መነሻ ቁጥር ማስመዝገብ ፣
ወ) ለኦዲትር /ለአወሳሰን የእጀ በእጅ መጠቀም ወይም Z-reoprt ያልወጣበት ምክንያት ለማስታወቅ
Θ አገልግሎት ጥያቄ ማቅረብ ፣
Θ በወቅቱ ትግሩን ያስመዘገበ መሆኑ ፣
Θ ችግሩን ሲፈታ ያስታወቀበት
ዐ)መብራት መጥፋት ወይም ብልሽት በወቅቱ ሳያዝመዘግበ ልስተናገድ የአገልግሎት ጥያቄ
Θ ማመልከቻ ያቀርባል ፣
Θ እድሳት እና ብልሽት ከሆነ በሰርቪስ ቡክ የተመዘገበበትን ማቅረብ ፣
Θ መብራት መጥፋት ከሆነ ቃለ መሃላ መግባት ፣
ዘ)መረጃ ተቀበሉኝ የአገልግሎት ጥያቄ
Θ የግዥና ሽያጭ ቅፆች ምልቶ ማቅረብ
Θ በTIN እና ያለ TIN የተፈፀመ ግዥዎችን ለይቶ ማቅረብ
ዠ) ለጥገና ወይም ዓመታዊ ማሽን የገባ መመለሱን ማሳወቅ
Θ የምርመራ መዝገብ ማቅረብ፣
Θ ማሽኑ ወደ አገልግሎት ማዕከል ሲገባ ያስመዘገቡበትን የመዝገብ ቁጥር ማቅረብ
የ) የተሰረቁ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ ማሳወቅ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ቅጽ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ ማሽኑ መጥፋቱን ከፖሊስ ጣቢያ ማስረጃ ማቅረብ፣
Θ ማሽኑ ከመጥፋቱ በፊት የነበረ የመጨረሻ ቀን ዜድ ሪፖርት ማቅረብ

የደረሰኝ ህትመት ፈቃድ እና አወጋገድ አገልግሎት

ሀ.የሽያጭ ደረሰኝ ለማሳተም
Θ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣
Θ የተ/እ/ታ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ለተመዘገበ)
Θ በንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ፣
Θ የንግድ ስም በሚታተመው ደረሰኝ ላይ እንዲጠቀስ የሚፈልጉ የንግድ ስም ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
Θ ማሳተም የሚፈለገዉ የደረሰኝ ዓይነት ናሙና
Θ ማሳተም የሚፈለገዉ የደረሰኝ ዓይነትና ብዛት በደረሰኞች ሕትመት፣መጠየቂያና መፍቀጃ ቅጽ መሠረት ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ በባለስልጣኑ የተዘጋጀውን የቃል ኪዳን ውል (commitment form) መፈረም፣
ለ. ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ለተቀነሰ ግብር የሚሰጥ ደረሰኝ ለማሳተም
Θ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣
Θ በንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ፣
Θ የንግድ ስም በሚታተመው ደረሰኝ ላይ እንዲጠቀስ የሚፈልጉ የንግድ ስም ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
Θ በንግድ ስራ ላይ ያልተሰማሩ መሆናቸው የሚያረጋግጥ ከሚመለከታቸው አካላት የተሠጠ ማስረጃ፣
Θ ማሳተም የሚፈለገዉ የደረሰኝ ዓይነት ናሙና
Θ ማሳተም የሚፈለገዉ የደረሰኝ ዓይነትና ብዛት በደረሰኞች ሕትመት፣መጠየቂያና መፍቀጃ ቅጽ መሠረት ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ በባለስልጣኑ የተዘጋጀውን የቃል ኪዳን ውል (commitment form) መፈረም፣
ሐ. የተ/እ/ታ ቀንሰው ገቢ የማድረግ ሃላፊነት የተጣለባቸው ወኪሎች ደረሰኝ ለማሳተም
Θ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
Θ የሚታተመው ደረሰኝ ላይ ምልክት (logo) እንዲካተትላቸው ጥያቄ ከቀረበ ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ምልክቱ የተመዘገበበት ማስረጃ፣
Θ ማሳተም የሚፈለገዉ የደረሰኝ ዓይነት ናሙና ፣
Θ ማሳተም የሚፈለገዉ የደረሰኝ ዓይነትና ብዛት በደረሰኞች ሕትመት፣መጠየቂያና መፍቀጃ ቅጽ መሠረት ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ በባለስልጣኑ የተዘጋጀውን የቃል ኪዳን ውል (commitment form) መፈረም፣
መ.በኮምፒውተር የተዘጋጀ ደረሰኝ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ በሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያ መጠቀም የማይችሉበትን አሳማኝ ምክንያት፣
Θ የኮምፒዩተር ሥርዓቱ ስለሚሰራበት ፕሮግራም የፃፈው ሰው ወይም ድርጅት ዝርዝር መረጃ መግለፅ፣
Θ ጥቅም ላይ የዋለውን/ የሚውለውን ከ-እስከ ማስመዝገብ፣
ሠ.ደረሰኝ መጥፋት ማስታወቅ
Θ ከግብር ከፋዩ ቁጥጥር ውጭ ከአቅም በላይ በሆኑ አደጋዎች /የእሳት ቃጠሎ፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ በሌባ / መሰረቅ
Θ ማስረጃ ከፖሊስ፣ ማህበራዊ ፍ/ቤት ወይም ከእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ኤጀንሲ
Θ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ በማናቸውም ጋዜጣ ወይም በመንግስት የቴሌቪዥን እና /ወይም ሬድዮ ፕሮግራም ለሁለት ጊዜ ማስታወቂያ ማስነገር
ረ.ደረሰኝ መመለስ እና አወጋገድ
Θ የንግድ ሥራ ሲቋረጥ ወይም የዘርፍ፣ የአድራሻ እና የስም ለውጥ የአገልግሎት መጠየቂያ ማቅረብ
Θ ጥቅም ላይ የዋሉ እና ያልዋሉ ደረሰኞች በግንባር በመቅረብ እንዲሰረዝ (Void) ማስደረግ፣
Θ የተሰረዘው ደረሰኝ ጥራዝ ሙሉ በሙሉ ያልተሰራበት ከሆነ ማስረከብ፣

የግብር ማስታወቅ ክፍያ መቀበልና ደረሰኝ መስጠት

ሀ.የንግድ ትርፍ እና የኪራይ ገቢ ግብር
Θ በትክክል የተሞላ አመታዊ የግብር ማስታወቂያ ቅፅ
Θ የትርፍና ኪሳራ መግለጫና የሂሳብ ሪፖርቶች
Θ የደረጃ ሀ”ግብር ከፋይ ከሆነ የሃብትና ዕዳ መግለጫ
Θ የእርጅና ቅናሽ ስሌትና የዘመኑ የሂሳብ ሰነዶች
Θ ዊዝሆልዲንግ ዝርዝር መረጃ፣
Θ ኤፍ ኤም/ማጠቃለያ ሪፖርት፣
Θ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ከ1000 ብር በታች ከሆነ ጥሬ ገንዘብ
ለ.የተጨማሪ እሴት ታክስ
Θ በትክክል የተሞላ ወርሀዊ የታክስ ማስታወቂያ ቅፅ
Θ ወርሀዊ የግብአት ግዢ የተሞላበት ማሳወቅያ ቅፅ
Θ የወሩ የግብአት ግዢ የሂሳብ ሰነዶች
Θ ኤፍ ኤም/ማጠቃለያ ሪፖርት
Θ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ከ1000 ብር በታች ከሆነ ጥሬ ገንዘብ
ሐ.የተርን ኦቨር ታክስ
Θ በታክስ ጊዜው በትክክል የተሞላ የታክስ ማስታወቂያ ቅፅ
Θ የታክስ ጊዜው የግብአት ግዢ ማሳወቅያ ቅፅ የሂሳብ ሰነዶች
Θ ኤፍ ኤም/ማጠቃለያ ሪፖርት
Θ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ከ1000 ብር በታች ከሆነ ጥሬ ገንዘብ
መ.የኤክሳይዝ ታክስ
Θ በትክክል የተሞላ ወርሀዊ የታክስ ማስታወቂያ ቅፅ
Θ ኤፍ ኤም/ማጠቃለያ ሪፖርት
Θ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ከ1000 ብር በታች ከሆነ ጥሬ ገንዘብ
ሠ.የስራ ግብር፣ የጡረታ መዋጮና የወጪ መጋራት
Θ በትክክል የተሞላ ወርሀዊ የታክስ ማስታወቂያ ቅፅ፣
Θ ፔይሮል
Θ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ከ1000 ብር በታች ከሆነ ጥሬ ገንዘብ
ረ. የቅድመ ግብርና ተ/እ/ታ with holding
Θ በታክስ ጊዜው በትክክል የተሞላ የታክስ ማስታወቂያ ቅፅ
Θ የታክስ ጊዜው ደጋፊ የሂሳብ ሰነዶች
Θ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ከ1000 ብር በታች ከሆነ ጥሬ ገንዘብ
ሰ. የሠንጠረዥግብሮች (የፈጠራ መብት በማከራየት፣ ከቴክኒክ አገልግሎት፣ ከዕድል ሙከራ፣ ከአክስዮን ትርፍ ድርሻ ከንብረት ኪራይ፣ ከጠቀማጭ ገንዘብ ወለድ እና ከካፒታል ጌይን)
Θ በየታክስ ዓይነቱ የታክስ ጊዜ በትክክል የተሞላ የታክስ ማስታወቂያ ቅፅ
Θ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ያገኙትን ግብር ከፋዮች ዝርዝር የሚያሳይ መረጃ አያይዞ ማቅረብ፣
ሸ. የማዘጋጃ ቤታዊ ክፍያዎች (የቦታ ኪራይና ቤት ግብር፣ ንግድ ቤት ኪራይ፣የውጭ ማስተዋወቅ )
Θ ለውጭ ማስተዋወቅ የልኬት መረጃ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ፣
Θ ለከተማ አስተዳደር ንግድ ቤት ኪራይ የታደሰ ውል፣
Θ ለመዝናኛ ግብር አገልግሎት ላይ የሚውል ትኬት 10% ክፍያ
ቀ.በውሳኔ ማስታወቂያ፣ በጊዜ ስምምነትና ሌሎች ክፍያዎች
በውሳኔ ማስታወቂያ ለአንድ የሂሳብ ጊዜ
Θ የግብር/ታክስ የውሳኔ ማስታወቂያ
Θ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ከ1000 ብር በታች ከሆነ ጥሬ ገንዘብ
በጊዜ ስምምነት ለአንድ የሂሳብ ጊዜ
Θ ክፍያ የጊዜ ስምምነት ውል
Θ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ከ1000 ብር በታች ከሆነ ጥሬ ገንዘብ
በ.ሌሎች ክፍያዎች
Θ የክፍያ አገልግሎት መጠየቂያ ቅፅ መሙላት፣
Θ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ከ1000 ብር በታች ከሆነ ጥሬ ገንዘብ
ተ)በግምት (በቀን ገቢ ግምት/ በቁርጥ ግብር ስርዓት ወይም በመረጃ)ግብር አወሳሰን ስርዓት የሚስተናገድ
Θ በአገልግሎት መጠየቂያ ቅፅ ማመልከቻውን ማቅረብ፣
Θ የቀን ገቢ ግምት ካልተገመተ ማስገመት፣
Θ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች ከሚመለከታቸው አካላት (ግምትና ወይም ውል) እንዲያቀርብ ሲጠየቅ ማቅረብ፣

የክፍያ ጊዜ ስምምነት/ ክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ ስምምነት አገልግሎት

ሀ.የክፍያ ጊዜ ስምምነት
Θ የክፍያ ጊዜ ስምምነት ማመልከቻ፣
Θ የግብር/ታክስ የውሳኔ ማስታወቂያ
Θ ክርክር ላይ የነበረ ከሆነ ክርክሩን እያየው ከነበረ አካል በራስ ፈቃድ ክርክሩን ስለማቋረጣቸው ማስረጃ፣
Θ እንደ ግብር ከፋዩ ደረጃ ግብሩ/ታክሱ በመ/ቁ/55/2003 ከተቀመጠው አነስተኛ የገንዘብ መጠን በላይ መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ የዕዳውን 25% ቅድሚያ ክፍያ የተፈፀመበት ደረሰኝ፣
Θ ሃብት/ንብረት ከተያዘ በኋላ ከሆነ የዕዳውን 50% ቅድሚያ ክፍያ የተፈፀመበት ደረሰኝ፣
Θ በፍርድ አፈፃፀም ላይ የሚገኝ ከሆነ ለአፈፃፀም ባለሥልጠኑ ያወጣቸውን ወጪዎችና አግባብነት ያለውን ቅድመ-ክፍያ የተፈፀመበት ደረሰኝ
ለ.የክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ ስምምነት
Θ የክፍያ ጊዜ ተሰጥቶት ግዴታውን ከአቅም በላይ መወጣት ያልቻለበትን ማስረጃ

የታክስ ኦዲት አገልግሎት

ሀ) የሂሳብ መዝገብ ለሚይዙ ግብር ከፋዮች
Θ ኦዲት እንደሚደረግ ደብዳቤ እንደደረሰ የሂሳብ ሠነዶችን፣ መዘግቦችንና ማስረጃዎችን በሙሉ ማቅረብ፣
Θ በኦዲት ሂደት የተጓደሉ ማስረጃዎችን ማሟላት፣
Θ የኦዲት ሥራው ሲጠቃለል፣ የኦዲት መውጫ ውይይት ላይ መገኘት፣
Θ ከመውጫ ውይይት በፊት የኦዲት ግኝቱን በዝርዝር ማወቅ፣
Θ በኦዲት መውጫ ቃለ-ጉባኤ ላይ አስተያየት መስጠት እና ተጨማሪ ማስረጃዎች ካሉት ማቅረብ፣
Θ በኦዲት ግኝቱ ላይ ጥያቄዎች ማቅረብና ማብራሪያ ማግኘት፣
Θ ዝርዝር የኦዲት ግኝት መረጃዎችን እና ግብርና ታክስ ስሌት የተሠራበትን አሠራር ከኦዲት የሥራ ሂደት ማግኘት ፣
Θ የግብርና ታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ መቀበል፣
Θ እንደ ግብር ከፋዩ ንግድ ሥራ ስፋት፣ የተሰማራበት የንግድ ዓይነት፣ ሠነድ አያያዝና የሥጋት ደረጃ መሠረት በአንድ ወይም በሁለት ኦዲተር የሚሠራ መሆኑን ከኦዲት የሥራ ሂደት ጠይቆ ማወቅ፣
ለ)የሂሰብ መዝገብ ለሚይዙ የንግድ ሥራን ሙሉ በሙሉ ለመዝጋት፣ የንግድ ሥራው ንብረት ከ50% በላይ ለመሸጥ፣ የተወሰነ የንግድ ዘርፍ/የማምረቻ ተቋም/ ቅርንጫፍ ለመሸጥ፣ ከአንድ በላይ ድርጅቶች ለመዋሃድ፣ ስም ለውጥ እና በአጠቃላይ ኦዲት ለሚስተናገድ የቅድመ ግብር ክፍያ ተመላሽ ለማድረግ
Θ በደብዳቤ ጥያቄ ማቅረብ፣
Θ የፀደቀ የባለአክስዮኖች ቃለ ጉባኤ፣ (ድርጅትን ለመዝጋት ብቻ)
Θ ለኦዲት የሂሳብ ሰነዶች፣ መዝገቦችንና ማስረጃዎችን በሙሉ ማቅረብ፣
Θ በኦዲት ሂደት ግብር ከፋዩ የተጓደሉ ማስረጃዎችን ማሟላት፣
Θ የንግድ ሥራውን የሚያቋርጥ ማንኛውም ግብር ከፋይ የንግድ ሥራውን ካቋረጡበት ቀን ጀምሮ በ3ዐ ቀናት ውስጥ ማስታወቅ
Θ የሂሳብ መግለጫዎችና አስፈላጊ መዛግብት፣ (ሙሉ በሙሉ የንግድ ሥራ ለመዝጋት ከሆነ) ለተቋረጠበት ግብር ዘመን በስልሣ ቀናት (60 ቀናት) ውስጥ አዘጋጅቶ ማቅረብ ፣
Θ በሚቀርበው የሂሳብ መግለጫ መሠረት የሚፈለግበት ግብር መክፈል፣
Θ የኦዲት ሥራው ሲጠቃለል፣ የኦዲት መውጫ ውይይት ላይ መገኘት፣
Θ ከመውጫ ውይይት በፊት የኦዲት ግኝቱን በዝርዝር ማወቅ፣
Θ በኦዲት መውጫ ቃለ-ጉባኤ ላይ አስተያየት መስጠት እና ተጨማሪ ማስረጃዎች ካሉ ማቅረብ ፣
Θ በኦዲት ግኝቱ ላይ ጥያቄዎች ማቅረብ ማብራሪያ ማግኘት፣
Θ ዝርዝር የኦዲት ግኝት መረጃዎችን እና ግብርና ታክስ ስሌት የተሠራበትን አሠራር ከኦዲት የሥራ ሂደት ጠይቆ ማወቅ፣ ማግኘት ፣
Θ የግብርና ታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ መቀበል፣
Θ እንደ ንግድ ሥራው ስፋት፣ የንግድ ዓይነት፣ ሰነድ አያያዝና የሥጋት ደረጃ መሠረት በአንድ ወይም በሁለት ኦዲተር የሚሰራ መሆኑን ከኦዲት የሥራ ሂደት ጠይቆ ማወቅ፣
ከላይ ከተገለጸው በተጨማሪ ድርጅቶች (ኃ.የተ.የግል ማህበር፣ አስኪዮን ማህበር፡ የሕብረት ሥራ ማህበር …) ማህበሩን ለማስፈረስ ከሆነ የሚያቀርባቸው ማስረጃዎች
Θ ሂሳብ አጣሪ (Liquidator) የተሰየመበትና በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት የተመዘገበ ቃለ-ጉባኤ ፣
Θ የሂሳብ አጣሪ የሂሳብ ሪፖርት (Liquidation statement) እና የሂሳብ ሰነዶችና ማስረጃዎችን ፣
Θ በቀረበው ማስረጃ መሠረት ተጨማሪ የሚወሰን ግብርና ታክስ ካለ ውሳኔ ማስታወቂያ መቀበል፣
ሐ/ ለንግድ ሥራ የተያዙ የተወሰኑ ካፒታል ንብረቶችን (ለንግድ፣ ለፋብሪካ፣ ለቢሮ የተያዙ ሕንፃዎች እና የኩባንያዎች አክሲዮን) በስጦታ ወይም በሽያጭ ለማስተላለፍ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ ለአክሲዮን/ለንግድ ሥራ ሕንፃ የተሸጠበትን ማስረጃ/ውል፣
Θ የንግድ ሥራ ሕንፃ ሽያጭ ከሆነ፣ የባለቤትነት ካርታ ኮፒ፣
Θ የንግድ ሥራው ሕንፃ የተገዛበትን ዋጋ እና አስከተሸጠበት ጊዜ የታሰበው የእርጅና ቅናሽ ከሌሎች ቀሪ ንብረቶች (ከአንድ በላይ ሕንፃ ላላቸው) ተለይቶ በዝርዝር አዘጋጅቶ ማቅረብ፣
Θ የሂሳብ መዝገብ ያልያዙ ግብር ከፋዮች ወይም ንብረቱ የግዥ ማስረጃ የሌላቸው ከሆኑ የቤት ሥራ ፈቃድ በተሰጠበት ጊዜ አግባብ ባለው መ/ቤት የተመዘገበ የቤቱ ዋጋ፣
Θ የንግድ ሥራው ቦታ/ሕንፃ/ ማምረቻ/ በሚመለከተው መ/ቤት በመሬት አስተዳደር /በከተማ/ ወረዳ/ማዘጋጃ ቤት የቤቱ የዋጋ መረጃ
Θ የተወሰነውን ግብርና ታክስ ስሌት ዝርዝር ፣ የኦዲት መውጫ ውይይት ላይ መገኘት እና በኦዲት መውጫ ቃለ-ጉባኤ አስተያየት መስጠት ፣
Θ ተጨማሪ ማስረጃዎች ካለ ማቅረብ፣
መ/ የሂሳብ መዝገብ ላላቸው ግብር ከፋዮች ዴስክ ኦዲት ለማድረግ
Θ ዴስክ ኦዲት እንደሚደረግ የደረሰ ደብዳቤ ፣
Θ በደብዳቤ ላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎችና ማስረጃዎች ፣
Θ በዴስክ ኦዲት ሂደት የተጓደሉ ማስረጃዎችን ማሟላት፣
Θ የኦዲት ሥራው ሲጠቃለል፣ የኦዲት መውጫ ውይይት ላይ መገኘት፣
Θ ከመውጫ ውይይት በፊት የኦዲት ግኝቱን በዝርዝር ከኦዲት የሥራ ሂደት ጠይቆ ማወቅ፣
Θ በኦዲት መውጫ ቃለ-ጉባኤ ላይ አስተያየት መስጠት እና ተጨማሪ ማስረጃዎች ካሉ ማቅረብ ፣
Θ በኦዲት ግኝቱ ላይ ጥያቄዎች ማቅረብና ማብራሪያ ማግኘት፣
Θ ዝርዝር የኦዲት ግኝት መረጃዎችን እና ግብርና ታክስ ስሌት የተሠራበትን አሠራር ከኦዲት የሥራ ሂደት ጠይቆ ማግኘት ፣
Θ የግብርና ታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ መቀበል፣
ሠ/ በአቤቱታ አጣሪ ኮሚቴ ውሣኔ የተሰጠባቸው እና ውሳኔው የማስተካከያ የኦዲት ሥራ ካለው ይህን የኦዲት ሥራ ለማጠናቀቅ
Θ የኮሚቴው ውሳኔ ከግብር ከፋዩ ማስረጃ ማቅረብ የሚጠይቅ ከሆነ ማስረጃዎችን በሙሉ ማቅረብ፣
Θ የማስተካከያ የኦዲት ሥራው ሲጠቃለል የመውጫ ውይይት ላይ መገኘት
Θ በኦዲት መውጫ ቃለ ጉባኤ ላይ አስተያየት መስጠት፣
Θ የተስተካከለ የግብርና የታክስ ውሳኔ ማስታወቂያ መቀበል፣
ረ)ባለሥልጣን /ቤቱ በየግብር ዘመኑ ልዩ ምርመራ ለሚደረግባቸዉ ግብር ከፋዮች፣ ኦዲት ለማድረግ
ለሀገር ዉስጥ ታክስ አንድ የኦዲት ሥራ
Θ ግብር ከፋዩ ኦዲት እንደሚደረግ ደብዳቤ እንደደረሰው የሂሳብ ሰነዶችን፣ መዘግቦችንና ማስረጃዎችን በሙሉ ማቅረብ፣
Θ የኦዲት መውጫ ውይይት ላይ መገኘት እና በኦዲት መውጫ ቃለ-ጉባኤ አስተያየት መስጠት ፣
የጉምሩክ አንድ የኦዲት ሥራ
Θ ግብር ከፋዩ ኦዲት እንደሚደረግ ደብዳቤ እንደደረሰው የሂሳብ ሰነዶችን፣ መዘግቦችንና ማስረጃዎችን በሙሉ ማቅረብ፣
Θ የኦዲት መውጫ ውይይት ላይ መገኘት እና በኦዲት መውጫ ቃለ-ጉባኤ አስተያየት መስጠት ፣

የክፍያ ማስረጃ የምስክር ወረቀት (የክሊራንስ) አገልግሎት

ሀ)ዓመታዊ የንግድ/ስራ ፈቃድ ለማደስ፣ በጨረታ ለመሳተፍ እና ከባንክ ብድር ለማግኘት የምስክር ወረቀት
Θ የዘመኑን ግብር/ታክስ አስታውቆ መክፈሉን ማረጋገጫ፤
Θ ወርሃዊ፣ ዓመታዊ ግብር ማሳወቂያዎችን በወቅቱ ማቅረቡን ማረጋገጫ፤
Θ የክፍያ ጊዜ ስምምነት የገባ ከሆነ ይህንን የሚገልጽ ማስረጃ፤
Θ በደረሰው ውሳኔ ቅሬታ/አቤቱታ አቅርቦ ሂደት ላይ የሚገኝ ከሆነ ቅሬታ/አቤቱታ መቅረቡን የሚያመለክት ማስረጃ፤
Θ ግብር ከፋዩ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር የደረሰበት ከሆነ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ፤
Θ የግብር እፎይታ/የቀረጥ ነፃ መብት ያለው ከሆነ ይህንኑ የሚገልፅ ማስረጃ፤
Θ በተሰማራበት ንግድ ፈቃድ ምንም ያልሠራ ከሆነ ላለመስራቱ ከሚመለከተው አካል ማረጋገጫ ማቅረብ
ለ) ድርጅትን ለመዝጋት፣ ባለቤትነት ለማዛወር፣የስም ወይም የአድራሻ ለውጥ ለማድረግ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት
Θ ድርጅትን ሙሉ በሙሉ ለመዝጋት
Θ ከድርጅቱ ንብረት ከ50% በላይ ለመሸጥ
Θ የአክስዮን/ንብረት ዝውውር ለማድረግ
Θ ስም ለውጥና ሥራ ላልጀመረ ፈቃድ ለመመለስ
Θ ከአንድ በላይ ድርጅቶች ለመዋሃድ የኦዲት ወይም የአወሳሰን ውሳኔ
ሐ) የወ መጋራት ክፍያ ማጠናቀቅ ማስረጃ
Θ የሚፈለግበት የወጪ መጋራት በክፍያ/በአገልግሎት አጠናቆ መክፈሉን ማረጋገጫ፤

የገቢ/ወጪ ዕቃ ጉምሩክ ትራንዚት

ሀ) ገቢ ዕቃ ትራንዚት
Θ ትራንዚት ዲክለሬሽን (IM8)
Θ የባንክ ፈቃድ
Θ ኮሜርሻል ኢንቮይስ /በባንክ የተረጋገጠ ኘሮፎርማ ኢንቮይስ/
Θ ካርጎ ማኒፌስት (በአጓጓዡ የሚቀርብ)
Θ ትራክ ማኒፌስት /ለጅቡቲ ግዢ/
Θ CIQ Certificate /ለቻይና ግዢ/
Θ የዋስትና ዶክመንት (Regional Custom Transit Gurantee /Insurance/Bond/ moral |Guarantee/
ለ) ወጪ ዕቃ ትራንዚት
Θ ኢንቮይስ
Θ ትራንዚት ዲክለሬሽን (EX8)
Θ የባንክ ፈቃድ
Θ የተቆጣጣሪ መ/ቤቶች ፈቃድ (እንደአስፈላጊነቱ)
Θ የሥሪት ሀገር ማረጋገጫ
Θ የማጓጓዣ መግለጫ/Truck manifest/
Θ አጓጓዡ የትራንዚት ዕቃዎች እንዲያጓጉዝ የተፈቀደበት ሰርተፍኬት፣
Θ የሚወጣው ዕቃ ተሸከርካሪ ከሆነ የሊብሬ ኮፒ
Θ ከሀገር ተመልሶ የሚወጣ ሲሆን 5% ቀረጥና ታክስ የተከፈለበት ደረሰኝ
ሐ) ተላላፊ ዕቃ ትራንዚት
Θ የጉምሩክ ዋስትና ሰነድ በመነሻ ጉምሩክ ጣቢያ ማቅረብ (RCTG/Insurance/Bank guarantee)
Θ የተመዘገበ ትራንዚት ዲክለሬሽን (IM8)
Θ ኮሜርሻል ኢንቮይስ/ፕሮፎርማ ኢንቮይስ
Θ ትራክ ማኒፌስት
) የውስጥ ትራንዚት
Θ ትራንዚት ዲክለሬሽን (EX8)
Θ ትራክ ማኒፌስት
Θ የተረጋገጠ የጉምሩክ ዋስትና ሰነድ
Θ የተረጋገጠ የመንገድ ወረቀት/መድረሻ ጠቢያ ላይ
ሠ) ገቢ ዕቃ ትራንዚት (ዩኒ ሞዳል)
Θ ትራንዚት ዲክለሬሽን (IM8)
Θ ቀረጥና ታክስ ክፍያ የተፈፀመበት መልቀቅያ (Removal)
Θ ኮሜርሻል ኢንቮይስ
Θ Packing List original & copy
Θ ትራክ ማኒፌስት
Θ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
Θ የቀረጥ ነፃ ከሆነ የታደሰ የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና የቀረጥ ነጻ ደብዳቤ
እንደ አስመጪው/ዕቃው ሁኔታ እየታየ የሚጠየቁ ቅድመ ሁኔታዎች
Θ እንደ አስመጪው/ዕቃው ሁኔታ እየታየ የሚጠየቁ ቅድመ ሁኔታዎች
Θ በኢምባሲዎች፣በአህጉራዊና በአለም አቀፋዊ ድርጅቶች እንዲሁም በተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚከፈቱ ሰነዶች/ ዲክላራሲዮኖች የየድርጅቶቹ ማህተም
Θ ለተሸከርካሪ ከመንገድ ትራንስፖርት የማስገቢያ ፍቃድ
Θ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለ ከሆነ የቀረጥ ነፃ ድብዳቤ እንዲቀርብ ይገባል ወይም ሊከፈል የሚገባው የቀረጥና ታክስ መጠን በኢንሹራንስ ዋስትና መያያዝ
Θ በባንክ ፍቃድ(L/C) የሚስተናገዱ Bill of loading/TWB ጀርባ ላይ Verify የተደረገበት
Θ ያለ ውጭ ምንዛሪ/ያለ ባንክ ፈቃድ ለመስተናገድ የተፈቀደበት ደብዳቤ/ሰነድ
Θ ዕቃው ውጭ የሚፈተሽ ከሆነ የውጭ ፍተሻ ፍቃድ
Θ በኮንቴይነር ለሚመጣ ዕቃ የኮንቴይነር ማስያዣ
ረ) ተላላፊ ዕቃ ትራንዚት (ዩኒ ሞዳል)
Θ ዲክላራሲዮን
Θ የኢንሹራንስ ዋስት
Θ ትራክ ማኒፌስት
Θ ኮሜርሻል ኢንቮይስ
Θ Packing List original & copy

የገቢ ዕቃዎች የጉምሩክ መጋዘን

ሀ) ዕቃ ወደ ጉምሩክ መጋዘን ለማስገባት
ወደ ጊዜያዊ የዕቃ ማከማቻ ሲገባ
Θ ትራንዚት ማጠናቀቅ
Θ የጭነት መግለጫ
Θ የአየር ክልል ተቆጣጣሪ ሪፖርት
Θ ካርጐ ማንፌስት
Θ የመንገድ ወረቀት/ ኤርዊይ ቢል
ለ) ወደ ቦንድድ መጋዘን ሲገባ
Θ ትራንዚት ማጠናቀቅ
Θ ካርጐ ማንፌስት
Θ የመጋዘን ማስገቢያ ኤስ /S/ ዲክለራሲዮን
ሐ) ወደ የተተውና የተወረሱ መጋዘን ሲገባ
Θ ውርስ እንዲደረግ ወይም ወደ ተወረሱ መጋዘን እንዲተላለፉ የተወሰነበት ማስረጃ
Θ በኮንትሮባንድ የተያዙ ዕቃዎች ስለመሆናቸው ከሚመለከተው የቀረበ ሰነድ ወይም (ሞዴል 270) እንደ አስፈላጊነቱ
መ) ወደ ተፈቀዱ የፕሮጀክት ሳይቶች ሲገባ
Θ ትራንዚት የተጠናቀቀበት ሰነድ
ሠ) ዕቃዎችን ከመጋዘን ለማስወጣት
Θ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት መጠናቀቁ ተረጋግጦ የተሰጠ መልቀቂያ (በሠነድ ወይም ኤሌክትሮኒክ ማስረጃ)
Θ የመጋዘን ኪራይ የተከፈለበት ደረሰኝ
ረ) ከጊዜያዊ ማከማቻ ለሚወጡ
Θ የመጋዘን ኪራይ የተከፈለበት ሰነድ
ሸ) ከቦንድድ መጋዘን ለሚወጡ
Θ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት መጠናቀቁ ተረጋግጦ የተሰጠ መልቀቂያ
Θ የመጋዘን ኪራይ የተከፈለበት ሰነድ/ለአጠቃላይ ቦንድድ መጋዘን/
) ከተተዉና የተወረሱ ዕቃዎች መጋዘን ለሚወጣ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ በቅደም ተከተል ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ በሽያጭ ሆነ በሌላ አኳኃን ወይም በሌላ በፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲለቀቁ ትዕዛዝ የተሰጠበትና በኃላፊ የተሠራ ሰነድ
Θ ወደ ውርስ መጋዘን ከተላለፈ በኋላ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ለተፈፀመበት ዕቃ
Θ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት መጠናቀቁ ተረጋግጦ የተሰጠ መልቀቂያ
Θ የመጋዘን ኪራይ የተከፈለበት ሰነድ
Θ የመጋዘን ኪራይ ሰነድ
Θ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ተፈፅሞበት እንዲወጣ በበላይ ኃላፊ የተሰጠ ውሳኔ

የጉምሩክ የገቢ/ወጪ ዕቃዎች አወጣጥ ሥርዓት (ክሊራንስ)

ሀ) ቀላል የዕቃ አወጣጥ ሥርዓት
(አምራች ላኪዎች፣ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች፣ ቀጥታ ላኪዎች፣የተመረጡ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ)
Θ የማስጫኛ ሰነድ
Θ ኢንቮይስ
Θ የቀረጥና ታክስ ልክ የተያዘ ዋስትና
ለ) ለሌሎችአስመጪዎች የተጠቃለለ ዲክለራሲዮን አቀራረብ ስርአት ለማስፈፀም የሚቀርቡ ሰነዶች
Θ ኢንቮይስ
Θ የባንክ ፍቃድ
Θ የማስጫኛ ሰነድ
Θ VDD( የእቃ ባህሪ መግለጫ)
Θ የኢንሹራንስ ክፍያ ደረሰኝ (ኮፒ)
Θ የማጓጓዣ ክፍያ ደረሰኝ (ኮፒ)
Θ የስሪት አገር ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት
ሐ) ዕቃ ከመድረሱ በፊት የሚፈፀም የዕቃ አወጣጥ ሥርዓት
(የመንግስት ድርጅት፣አምራች ላኪዎች፣ለሀገር ውስጥ ገበያ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች፣ቀጥታ ላኪዎች፣የተመረጡ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ፣በመልቲሞዳል ትራንስፖርት ሥርዓት ተጠቃሚ የሆኑ ማንኛውም አስመጪ)
Θ ኢንቮይስ
Θ VDD( የእቃ ባህሪ መግለጫ)
Θ ፓኪንግሊስት(እንደአስፈላጊነቱ)
Θ የስሪት አገር የማረጋገጫ ምስክር ወረቀት
Θ የፍሬት ደረሰኝ ኮፒ
Θ የኢንሹራንስ ደረሰኝ
Θ የባንክ ፍቃድ
Θ የማጓጓዣ ሰነድ
Θ ቀረጥና ታክስ የሚከፈልበት ዕቃ ከሆነ ቀረጥና ታክስ የተከፈለበት ማስረጃ ፣ቀረጥ ነፃ ከሆነ የመብት ማረጋገጫ ደብዳቤ
መ) ወደ መድረሻ ቦታቸው ደርሰው ትራንዚት ያጠናቀቁ ዕቃዎች ላይ የሚፈጸም የዕቃ አወጣጥ ሥርዓት
Θ ትራንዚት ማጠናቀቁ፣
Θ ኤሌክትሮኒካሊ የቀረበ በሲስተም የተመዘገበና አሰስ የተደረገ ዲክላራሲዮን
Θ በአካል የቀረበ በሲስተም የተመዘገበና አሰስ የተደረገ ዲክላራሲዮን
Θ ለጉምሩክ ሥነ-ስርዓት አፈፃፀም አስፈላጊ የሆኑ ኦርጂናል ሰነዶች(የአንድ መስኮት አገልግሎት ተግባራዊ እንዲደረግ)
Θ ቀረጥና ታክስ የተከፈለበት ወይም የመብት ማረጋገጫ ማስረጃ፣
ሠ) የወጪ ዕቃዎች ክሊራንስ
Θ ኢንቮይስ
Θ ፖኪንግሊስት /እንደአስፈላጊነት/
Θ የሥሪት ሀገር ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት
Θ የኢንሸራንስ ደረሰኝ /ከኦርጂናል ጋር የተመሳከረ ኮፒ/
Θ የባንክ ፈቃድ
Θ የማጓጓዣያ ሰነድ
Θ የተቆጣጣሪ መስሪያቤቶች ፍቃድ እንደአስፈላጊነቱ
Θ ለምትክነት ለለውጥ/Replacement/ የሚወጣ ዕቃ ከሆነ ቴክኒካል ችግር ያለበት መሆኑን የተሰጠ የባለሙያ ማረጋገጫ
ቀ) ተመልሰው ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች
Θ ቀዳሚ ሰነዶች (ዲክላራሲዮንና አባሪ ሰነዶች)፣
Θ አዲስ የተሞላ ዲክላራሲዮን
Θ ለጥገና ከሆነ የጥገና ደረሰኝ
በ) ተመልሰው ከሀገር የሚወጡ ዕቃዎች
Θ ቀዳሚ ሰነዶች (ዲክላራሲዮንና አባሪ ሰነዶች)፣
Θ የተመዘገበ የወጪ ትራንዚት ዲክላሬሽን፣
Θ የእቃ ዝርዝር መግለጫ፣
Θ የማጓጓዣ መግለጫ/Track/Cargo manifest፣
Θ ከሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት የፈቃድ ደብዳቤ፣
Θ የተመዘገበ ዲክላራሲዮን እና የእርጅና ቅናሽ ቀረጥና ታክስ የተከፈለበት ደረሰኝ
ተ) በጊዜያዊነት ከሀገር የሚወጡ ዕቃዎች
Θ የተመዘገበ የወጪ ትራንዚት ዲክላሬሽን፣
Θ የቀረጥና ታክስ ልክ የተያዘ ዋስትና
Θ የባንክ ፈቃድ፣
Θ የእቃ ዝርዝር መግለጫ፣
Θ የማጓጓዣ መግለጫ/Track/Cargo manifest፣
Θ ከተመዘገበ የወጪ ዕቃ ክሊራንስ ጋር የዕቃ ማስጫኛ ሰነድ፣
Θ ከሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት የፈቃድ ደብዳቤ፣

የታክስ ተመላሽ አገልግሎት

ሀ)የገቢ ግብር ቅድመ ክፍያ ተመላሽ
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ በቅደም ተከተል ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ በውጭ ኦዲተር የተመረመረ የሂሳብ መግለጫ፣ የሚተየው ተከፋይ ኦሪጅናል ሰነድ በታክስ/በግብር አይነቱ ተለያይቶ መቅረብ
Θ ግብር ስለመክፈሉ የሚያሳዩ ኦሪጅናል የ2% ወይም የጉምሩክ 3% ቅድመ ግብር ክፍያ ደረሰኝ፣
Θ የቅድሚያ ግብር ክፍያ በዕቃ ግዢ ዋጋ ውስጥ ያለመካተቱን ወይም በተሰብሳቢ ሂሳብ /Accounts Receivable/ መያዙን ማረጋገጥ፣
Θ በማናቸውም የግብር/የታክስ አይነቶች ላይ ዕዳ የሌለ መሆኑን ማረጋገጥ፣
ለ. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ
የመደበኛ 15%
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ የተመላሽ ጠያቂዎች ከማናቸውም ዕዳ ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ፣
Θ ሊከፈል ከሚገባው ታክስ በላይ እንዲቀነስ የተደረገው ታክስ የሚከፈልበት ከሆነ የተጠቀሰው ታክስ ለቀጣዮቹ አምስት የሂሣብ ጊዜያት እንዲተላለፍ የተደረገ መሆኑ፣
Θ በብልጫ የተከፈለ ታክስ (ቀሪ ሂሣብ) መኖሩ የሚያረጋግጥ፣ደጋፊ ኦሪጅናል የሂሳብ ሰነድ ማቅረብ፣
በዜሮ ምጣኔ
የተፋጠነ ስርዓት (ኤክሳይዝ ታክስን ጨምሮ)
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ በቅደም ተከተል ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ በስርአቱ እንዲስተናገዱ ከኢንዱስትሪ ሚ/ር የተፈቀደለት መሆኑ ማረጋገጫ
Θ ታክስ ስለመከፈሉ የሚያረጋግጥ በግብር/በታክስ አይነቱ ኦሪጅናልደጋፊ ሰነዶች፣
Θ የተመላሽ ጠያቂዎች ከማናቸውም ዕዳ ነፃ መሆኑን ማረጋገጥ፣
ላኪዎች
Θ የአገልግሎት መጠየቂያ ሞልቶ ማቅረብ፣
Θ በአንድ የሂሳብ ጊዜ ከሚከናወን ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ዋጋ ውስጥ ቢያንስ 25% በዜሮ የማስከፈያ ልክ ታክስ የሚከፈልበት፣ በአገር ውስጥ አምራቾች ለኢ/ብ/ባ የሚቀርበውን ወርቅ ጭምር ቀሪ ሂሣብ መኖሩ የሚያረጋግጥ ደጋፊ የሂሳብ ሰነድ ማቅረብ፣
Θ ዕቃው/ አገልግሎቱ ወደ ውጭ ገበያ መላኩን/መቅረቡን የሚያስረዱ ደጋፊ ሠነዶች (የግብይቱ ዋጋ ቢያንስ 25% መሆኑን የሚያረጋግጥ፣ የጉምሩክ ዲ/ን፣ የማስጫኛ የተከፈለ፣የባንክ ፈቃድ ደረሰኝ፣ ያስገኘው የውጭ ምንዛሪ ውል)አያይዞ ማቅረብ፣
Θ በግብዓት ላይ የተከፈለ የተ/እ/ታ ደረሰኝና የድርሻ ስሌት የሚያመለክት ሠንጠረዥ
የባለልዩ መብት
Θ የዲፕሎማቲክና ኮንስለር ሚሲዮኖች እና ተመሳሳይ አቋም ያላቸው ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከወጭ ጉዳይ ሚ/ር እውቅና ማስረጃ፣
Θ የበጐ አድራጎት ድርጅቶች በፍትሕ ሚ/ር የበጐ አደራጎት ኤጀንሲ እውቅና ማስረጃ፣
Θ ግብይት የተፈፀመበት የተ/እ/ታ ደረሰኝ፣
በገዥው ተይዞ የሚከፈል የተ/እ/ታ
Θ ግብይት የተፈፀመበት የተ/እ/ታ ደረሰኝ፣
Θ ደረሰኝ (ቫውቸር) ከመንግስት ተቋም የተሰጠ፣
Θ የተ/እ/ታ ወርሃዊ ማስታወቂያ
ሐ) በማዕድን/ነዳጅ ፍለጋ ሥራ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች
Θ በማዕድን/ነዳጅ ፍለጋ ሥራ ላይ የተሣማሩ ኩባንያዎች የታደሰ ያልተሰረዘ ፈቃዱ፣
Θ የማዕድን ሚ/ር በሚያቀርበው ዝርዝር ውስጥ የተካተተ ኩባንያ ስለመሆኑ ማስረጃ፣
Θ ግብይት የተፈፀመበት የተ/እ/ታ ደረሰኝ
) ሌሎች በማናቸውም ሁኔታ የተከፈለ ብልጫ ክፍያ
Θ በማናቸውም ሁኔታ በብልጫ የተከፈለበት ተያያዥነት ያላቸው ማስረጃ
ሠ)ቀረጥ ታክስ ተመላሽ ሥርዓት(አምራች ላኪዎች፣ቀትተኛ ያልሆኑ አምራች ላኪዎች፣ጥሬ ዕቃ አቅራቢዎችና ላኪዎች)
Θ ከአገር ውስጥ ግብዓት የተገዛበትና ታክስ የተከፈለበት ደረሰኝ ወይም ከውጭ ለገባ ጥሬ ዕቃ ቀረጥና ታክስ የተከፈለበት ደረሰኝ፣
Θ ወደ ውጪ የተላከውን ምርት ለማምረት ሥራ ላይ የዋሉ ከውጪ የገቡ ወይም በአገር ውስጥ የተመረቱ ጥሬ ዕቃዎችና ሌሎች ግብዓቶች ዝርዝርና ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የግብዓት ምርት ጥምርታ፣
Θ ለአምራች ላኪ ወይም ለላኪ በሽያጭ ለተላለፈ ጥሬ ዕቃ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የፀደቀ የሽያጭ ውል ስምምነት እና የሽያጭ ደረሰኝ
Θ ከውጭ ሀገር ለተገዛ ዕቃ የገቢ ዲክለራሲዮን እና ኢንቮይስ
Θ ዕቃው ለውጪ ገበያ መላኩን የሚያሳይ፡-የጉምሩክ ዲክለራሲዮን፣የማስጫኛና /ለትራንስፖርት/ የተከፈለ (Bill of Lading/Air ways Bill) ሠነድ፣
Θ የውጪ ምንዛሪ የተገኘበት የባንክ ሰነድ (Bank Credit Advice)፤ የሚያመለክቱና በባለሥልጣኑ ተቀባይነት ያላቸው ማስረጃዎች፣
Θ የባንክ ፈቃድ ደረሰኝ (Bank Permit)፣
Θ በተጠቀሰው የሂሳብ ጊዜ አገልግሎቱን/ዕቃው ከተቀበለው /ከገዢው/ ጋር የተገባው የውል /ስምምነት/ ሠነድ፣